አቶ መለስ ዜናዊ የ2012 ታላቅ አምባገነናዊ ገዢ ......!!!!

በ2012 በኢትዮጵያውያን ትዝታ ውስጥ በጉልህ የሚታወሰው የአቶ መለስ ዜናዊ ህልፈተ ህይወት ነው። አቶ መለስ በጠና ታመዋል የሚለው ዜና ተንጠባጥቦ መሰማት ከጀመረበት ከጁላይ 15 ጀምሮ በኢትዮጵያ የፓለቲካ ምህዳር ውስጥ ከፍተኛ መናወጥ ተጀመረ። ነዉጡ አላቆመም። አሁንም ቀጥሏል።ምንልክሳልሳዊ
የኢትዮጵያ ፓለቲካ የተዋቀረው በተቋም እና ስርዓት ላይ ሳይሆን በግለሰብ እና በባዕዳን ርዕዮተ-አለም ዙሪያ ነው። ይህ ሁኔታ በኢኮኖሚያቸው ባልዳበሩ አገሮች ሁሉ የሚታይ ክስተት ነው። ስለሆነም የአቶ መለስ በጠና መታመም የገዢውን ፓርቲ ጭንብሉን ገፍፎ እርቃኑን አስቀረው።ምንልክሳልሳዊ
ኢህአዴግ ከተመሰረተ ጀምሮ ሲመሩት የነበሩት አቶ መለስ ናቸው። የአቶ መለስ መታመም ብቻ ሳይሆን ሞተዋል የሚለው ዜና በፍጥነት መናፈስ ሲጀምር የኢህአዴግ ደጋፊዎችና አባላት ምን ያህል በአቶ መለስ ላይ ጥገኞች መሆናቸው ቀስ በቀስ ተጋለጠ።ምንልክሳልሳዊ
በመጨረሻም ህልፈተ ህይወታቸው በኢቲቪ ሲዘገብ ፡ የገዢው ፓርቲ ደጋፊዎች ፥ ጡት እንደተከለከለ ህጻን ፥ ተራወጡ። ተንቀጠቀጡ። ሚሆኑትን አጡ። ምንልክሳልሳዊ
በአቶ መለስ አምባገነናዊ አገዛዝ ለ21 ዓመታት ሲገዛ የኖረው ህብረተሰባችንም ሆድ ባሰው ፡ መለሰ ሞቱበት! ያለቀሰው አለቀሰ ፡ የተከዘው ተከዘ። ግን ለምን ያ ሆነ? ሱስ ነዋ! ሱስ! የመለስ ሱስ። በግድ ለ21 ዓመታት ላዩ ላይ ቁጢጥ ብለው ፡ ከሳቸው ሌላ ሚያየው ፡ ሚያደምጠው ፡ አማራጭ ሳይሆነረው የኖረው ህብረተሰባችን የአቶ መለስ ሱስ ተጠናዉቶት ነበር።
በሌላ መልኩ ፡ የመንግስት መደናበር አሳፋሪ ነበር። አንዴ “ሽርሽር ላይ ናቸው” ሲሉን። ከዛ “ለአዲስ አመት ይመጣሉ” ሲሉን … ኸረ ምኑ ቅጡ። ምንልክሳልሳዊ
ይህ ሁሉ ግን የአቶ መለስ ጣጣ ነው። አቶ መለስ የፈጠሩት መንግስት ምን ያህል ውስጡ ገለባ እንደሆነ ፡ አመኔታም ሆነ ታማኒነት የሌለው ፡ የወመኔዎች ስብስብ እንደሆነ ቀስ በቀስ ራሱን አጋለጠ። ደጋፊዎቹንም አከሰራቸው ፡ አሳፈራቸው ፡ አሸማቀቃቸው።
“ለካስ መንግስት ውሸታም ነው!” አሉ ደጋፊዎች። “ለካስ ተቃዋሚዎች ሚሉት እውነት ነው!” ብለው ናላቸው ዞረ። ኡ!ኡ! አሉ። በሃዘን ላይ ሃዘን። መለስም መንግስትም በድን ሆነው ተገኙ። ምንልክሳልሳዊ
ኢሳት እውነተኛ ሆኖ ተገኘ ፡ ኢሳት ተደማጭነቱ ተስፋፋ ፡ የበላይነቱን ተጎናጸፈ ፡ ታማኒነት አገኘ። ለዚህ ሁሉ አቶ መለስ ምስጋና ይገባቸዋል። መንግስታቸውን አዋርደው ፡ ደጋፊዎቻቸውን አክስረው ፡ ኢሳትን ሸልመው አረፉ።
አቶ መለስ በሞታቸው ከሁለት አስርተ ዓመታት በላይ ሲያስታምሙት የኖሩትን ‘ነቀዝና ሌባ’ መንግስታቸውን ድባቅ መቱልን። ከሞቱም በኋላ መንግስታቸው ‘ታላቁ መሪያችን’ እያለ ውርደቱን አጧጡፎታል።
ታዲያ ከአቶ መለስ ሌላ የ2012 ታላቅ ኢትዮጵያዊ መሆን ሚገባው አለን? ያለ አይመስለኝም።