በአንድ ጀንበር አላግባብ በልጽገው የሚገኙ ፖለቲከኞ ፡ “እነድንገቴ!”

“እነድንገቴ!”
በዛሬ ጊዜ በአዲስ አበባ ድንገት በአንድ ጀንበር አላግባብ በልጽገው የሚገኙ ሰዎች አሉ፡፡ “እነድንገቴ!” ይባላሉ በአዲሳባኛ፡፡ በፖለቲካውም ድንገት የሚከሰቱ ፖለቲከኞ አሉ - እነሱም “እነድንገቴ” ናቸው፡፡ ስንቱ የሸቀለበትን ንግድ ከመሸ የሚዳክሩበት እንዳሉ ሁሉ የከሰረ ፖለቲካም የሚሞክሩ አሉ፡፡ የሁለቱም የተበላ ዕቁብ (depleted business) ነው፡፡ምንልክ ሳልሳዊ 
እገሌ ሱቅ ከፈተ ብሎ መክፈት፣ እከሌ ፖለቲከኛ ከሆነ ምን ያንሰኛል? ማለትና የሰሙትን ሁሉ መኮረጅ፤ ማጣፊያው ሲያጥር አደጋ ላይ ይጥላል፡፡ መቼውንም ቢሆን የፓርቲ መንገድ፤ ሲገቡ ቁልቁለት፣ ሲወጡ አቀበት ነው! መንገዶቹ ሁሉ አልጋ በአልጋ አይደሉም እንደማለት ነው፡፡ ምንልክ ሳልሳዊ

ትርፉን ነግሮ መከራውን ሳይነግረኝ የምንልባቸው አያሌ ጉዳዮች አሉ፡፡ የፓርቲም፣ የድርጅትም፣ የማህበርም፣ የቢሮም … የህይወትም፡፡ በተለይ ምርጫው አፋፉ ላይ በደረሰበት በአሁኑ ሰዓት ሁለቴ ሶስቴ ማሰብ ያለብን ነገሮች ቀላል አይደሉም፡፡
በዛሬው የገና በዓል ደስታችንን ብቻ ሳይሆን መከራችንንም እናስታውስ! እያንዳንዱ ስብሰባችን በግራም ቆመን ይሁን በቀኝ፤ እየተንቀሳቀስንም ሆነ ቆመን፤ አንድ ነገር ልብ እንበል፡- በመሰብሰባችን ለህዝባችንና ለአገራችን ምን አፈራን? ነው ወይስ በባዶ ሆዳችን በኢኮኖሚ ጉዳይ ተሰብስበን፤ ህዝቡ ያምነን ይመስል ስለ ህዝቡ አውርተን፤ ምን ፈየደን? ብለን መጠየቅ ተገቢ ነው፡፡ አለበለዚያ፤ “ሞኝ ሸንጐ ተሰብሳቢ አገኘሽ፤ ቁርስ የሌለው ቡና አፈላሽ” መባል ነው ውጤቱ - “ነከብኸም ዮከርያ ጋዋ ሸከትኸም፤ ሳፍራ ኤኖ ቃዋ” ማለት ነው፡፡ምንልክ ሳልሳዊ