ሰበር ዜና- ወያኔ በመካነ ኢየሱስ እና በሙሉ ወንጌል ቤተ-ክርስቲያናት ያለብንን የቤት ስራ አላጠናቀቅንም::አለ!!

ሰበር ዜና- ወያኔ በመካነ ኢየሱስ እና በሙሉ ወንጌል ቤተ-ክርስቲያናት ያለብንን የቤት ስራ አላጠናቀቅንም::አለ!!

የወያኔው መንግስት ሚኒስትር የሆኑት ሽፈራው ተክለማርያም መንግስታቸው በኦርቶዶስ ቤተ-ክርስትያን በኩል ያለውን የተጠላለፈ ያሉትን ችግር ባለን ልምድ መሰረት 95% ፈተነዋል ሲሉ የሙስሊሙን ህብረተሰብ ችግር ግን ትንሽ አስቸጋሪ የሆነብንን እና አመራር ብለን  ያመጣናቸው /የሾምናቸው / ሰዎች ማስተባበርም ሆነ ማሳመን ስላልቻሉ በወጣት ሙስሊሞች በኩል በሚደረገው እንቅስቃሴ ራሳቸው ላይ ገመድ እየጠመጠሙ ነው ሲሉ የእስልምና ምክር ቤት አመራሮችን ሲተቹ የሳቸውና የአጋሮቻቸው ገመድ ግን አልታያቸውም::እንደ የምንሊክ ሳልሳዊ ምንጮች::

ሽፈራው ተክለማርያም
አቶ ሽፈራው በአዲስ አበባ የደህንነት ቢሮ ውስጥ በተደረገው እና የሕወሓት አባላትን አና ደጋፊዎችን ከነታማኞቻቸው ብቻ ባሳተፈው በትግሪኛ በተመራው ስብሰባ ላይ እንደገለጡት አብዛኛው ሃይማኖተኛ እያለ ራሱን የሚጠራ አክራሪ ሁሉ በ ወያኔ ላይ ጥርሱን የነከሰ ስለሆነ በእያንዳንዱ በሚጠረጠር ሰው ላይ ሁሉ አስቸኳይ እርምጃ መወሰድ ይኖርበታል ሲሉ አሳስበዋል::የሚገርመው በመካነ እየሱስ ዉስጥ እና በሙሉ ወንጌል ዉስጥ ተሰግስገው ያሉ ቄስ እና ፓስተር ነን የሚሉ ግለሰቦች ሙስሊሙን እና ኦርቶዶክሱን ለመብቱ እንዲዋጋ እያማከሩ እና እየረዱ ስለሆነ ..በነዚህ ቤተ ክርስቲያናት ላይ መንግስት ያልተቋጨ የቤት ስራ ሥላለበት ዛሬ ነገ ሳይባል መንቀሳቀስ ያስፈልጋል ብለዋል::

አሉን ብለን ያስቀመጥናቸው ፓስተሮች እየሸሹን ሲሆን አገር ጥለው እየወጡ በዛው ሲቐሩ ሌሎቹ ደሞ ዝምታን መርጠዋል ብለዋል እንዲሁም የመካነ እየሱስ እና የሙሉ ወንጌል አመራር ፓስተሮች ከመድረክ አመራሮች እና ወጪ አገርም ሲሄዱ በአምልኮ መልክ ከጽንፈኛ ዲያስፖራዎች ጋር እየታዩ ስለሆነ ምን ይዘው ሄደው ምን ይዘው እንደሚመጡ በአፋጣኝ መታወቅ አለበት ብለዋል::

አቶ ሽፈራው በቁጣ የተናገሩ ይምሰላቸው እንጂ ፊታቸው ላይ የመደናገጥ እና የመጠራጠር ነገር ይነበብ ነበ ብለዋል የምንሊክ ሳልሳዊ ምንጮች::
በወቕቱ ተሰብስበው የነበሩት ትግሪኛ ተናጋሪዎች እርስ በርሳቸው እንዲተማመኑ እና እንዲተባበሩ የተነገራቸው ሲሆን ይህን ካላደረጉ ነገ የሚመጣባቸውን ችግር ማለፍ እንደማይችሉ ተመክረዋል..በወቅቱ ብዙ ባይባልበትም በቅርቡ ወደ ዱባይ ለሽርሽር በሚል ሄደው የከዱትን 4 የደህንነት አባላት በተመለከተ ዉይይት የተደረገ ሲሆን መረጃ ከማባከናቸው በፊት እንዲመለሱ እና ሰላማዊ የሆነ ኑሮ እንዲቀጥሉ ካልሆነ በሚሄዱበት አገር እንደ ተስፋየ መረሳ/ምሳሌ ሆነ/ድምፃቸውን አጥፍተው እንዲኖሩ እንዲሁም የፈለጉት ሊደረግላቸው እንደሚችል በቅርብ የምታገኙዋቸው ካላቸሁ ንገሩዋቸው ተብሉዋል::
እንዲሁም የድህረገጽ ስለላን በተመለከተ በውጭ አገር ሄደው መሰልጠን የሚፈልጉ እና ክራይቴሪያውን የሚያሙዋሉ ካሉ ጓድ ደብረጺሆንን ማናገር እንደሚችሉ ማሳሰቢያ ተነግሯል::ምንሊክ ሳልሳዊ