እኔ ግንቦት ሰባት…….ይለያል ዘንድሮ የወያኔ ኑሮ።

እኔ ግንቦት ሰባት…….

ሰሞኑን በ እኔም ሆነ ስለ ነጻነት በሚጽፉ ሰዎች የግል ኢ-ሜይል (ጾዳቤ) የግንቦት ሰባት አባላት ስለሆናችን አበክረው ይነግሩናል፣ ያስጠነቅቁናል፣ ሊያስፈራሩንም ይሞክራሉ። እውነቱ ለመናገር በዶ/ር ብርሃኑ የሚመራውን ግንቦት ሰባት ተቀላቅሎ ትግል ማካሄድ መቻል በራሱ ክብር እንጂ ለሰከንድ እንኳን የሚጸጽተኝ አለመሆኑን ስናገር በታላቅ ደስታ ነው። እንደውም አባል መሆን ካለብኝ አባል የምሆነው ከዚሁ ፓርቲ ጋር ስለ መሆኑ እና ዶ/ር ብርሃኑ የሚሰጣቸው ትንታኔዎችን በሚገባ የምጋራ፣ እምነቶቹን የማምን፣ ስነቃሎችን(በተለይ ወያኔን ሲጠራቸው ዱርዮ) የሚላትን ቃል ሳይቀር እንደ ነፍሴ የምወዳት ነኝና በግሌ ለምታስፈራሩኝ ሁሉ ማሪያምን አልፈራም፤ ግንቦት ሰባትንትም አያስፈራም። እንኳን አይደለም ግንቦት ሰባት ሰዎች የዱርዮ እና የወሮበላው ቲ.ፒ.ኤል. ኤፍ. አባል ሆነው የለም እንዴ? እርግጥ ወያኔ አረ ግንቦት ሰባት አይደለምን በማለት ምለን ተገዝተን እንድንጮኽ እና ቃለ መሃላችን እንድንሰጥ ፈልጎ እንደው እውነቱን ፍንትው አድርገን ማስረዳት ይኖርብናል። የሰሞኑ መጠነ ሰፊ ዘመቻ ግንቦት ሰባት ላይ ማነጣጠሩን ወድጄዋለሁኝ ..... ይለያል ዘንድሮ የወያኔ ኑሮ።

ግንቦት ሰባትን እኮ ብርሃን ናት፤ ሕዝቡ ለመጀመሪያ ጊዜ ዲሞክራሲያዊ መብቱን ተጠቅሞ የመረጠበትን እና ወያኔ በጉልበቱ እና በጠመንጃ የሕዝቡን ይውንታ ገልብጦ ተመርጫለሁኝ ብሎ ስልጣኑን አልለቅም ያለበት ቀን ነውና መላው ሕዝብ ግንቦት ነው ሊያውም ግንቦት ሰባት፤ መላው ህዝብ መብቱ ተጠቅሞ የመረጠው መብቱም የተጣሰው መብቱም ዳግመኛ የሚመለሰው በዚሁ በግንቦት ነው ሊያውም በግንቦት ሰባት……. መቼም ወያኔ መጥፊያክ ግንቦት ነው ብሎ የሱዳን ጠንቋይ አመላክቶዋችሁ ከሆነም ንገሩን እንጂ እኛ ሁላችን ግንቦቶች ስለመሆናችን ማወቅ ከፈለጋችሁ መፋቅ ሳያስፈልገን ግንቦት ሰባቶች ነን.....ነጻነት..እኩልነት...ዲሞክራሲ የናፈቀን።

ግንቦት ሰባት..ለነጻነት....ግንቦት ሰባት..ለፍትህ..ግንቦት ሰባት....ለእኩልነት...ግንቦት ሰባት ....ለዲሞክራሲ...ግንቦት ሰባት......ለዜጎች ክብር......ግንቦት ሰባት...ለዘላቂ ልማት እላለሁ። አበቃሁ..ድል ለግንቦት ሰባትነት... ድል ለሰፊው ህዝብ!!!