በመንግስት የተዘጋጀው ምርጫ ላይ ከመሳተፍ ራስን ማቀብ ባለመመዝገብናባለመሳተፍ ተቃውሞን መግለፅ

ሰሞኑን የታቀደውን ምርጫ ባለመመዝገብናባለመሳተፍ ተቃውሞን መግለፅ 

ዜጎች በመንግስታቸው ላይ ተቃውሞዋቸውን የሚያሳዩበትየተለያዩ ስልቶች የሚገኙ ሲሆን ከነዚህ መካከልም መንግስት
የሚያዘጋጃቸው የተለያዩ ፕሮግራሞች ላይ ከመሳተፍ ራስንማቀብ አንዱ ነው፤ ይህም የሰላማዊ ትግል አንድ መገለጫ
መሆኑ የሚታወቅ ነው። በመሆኑም ፊት ለፊታችን የተደቀነውበመንግስት የተዘጋጀው ምርጫ ላይ ከመሳተፍ ራስን ማቀብአንድ ተቃውሞንየመግለጫ መንገድ መሆኑ ሊታወቅ ይገባል።አንዳድ ወንድሞች ካርዱን ወስደን ተቃዋሚ ፓርቲንበመምረጥ ተቃውሞዋችንን እንግለፅ የሚል ሐሳብ አላቸው፤ይህ ግን ፍፁም የተሳሳተ ተቃውሞን መግለጫ መንገድመሆኑንበሦስት መንገዶች ማሳየት እወዳለሁ።ምንሊክ ሳልሳዊ
 

አንደኛ:- የምርጫ ካርድ ወስዶ መምረጥ መንግስትበሚሰራው ድራማ ላይ ተሳታፊ መሆን ነው!!!
መቼም ከፊታችን የተደቀነው ምርጫ የይስሙላመሆኑንለመናገር የፖለቲካ ምሁር መሆንን አይጠይቅም
በሕገመንግስቱ እንዳይደርስበትየተከለከለውን የመጅሊስንምርጫ ራሱ ተቆጣጥሮ ሙስሊሙ በሩን ዘግቶ
በተቀመጠበትበነቂስ ወጥቶ መረጠ ብሎ ያወጀ መንግስት ራሱበግልፅ በሚሳተፍበት ምርጫ ላይ ፍትህን ያሰፍናል ብሎ
መጠበቅ ከዝንብ ማርለመቁረጥ ከማሰብ ተለይቶ ሊታይአይችልም።በመሆኑ እንዲህ ያለ ዝቅጠት ውስጥየሚገኝመንግስት ያዘጋጀው ምርጫ ላይ መሳተፍ አዳማቂከመሆን በዘለለ የሚፈይደው ተጨባጭጥቅም የለውም::

ሁለተኛ:- የተዘጋጀው የአካባቢ ምርጫ ይህ ነው የሚባል ፋይዳየለውም!!!
ከሰሞኑ በፓርላማ ቀርበው የተናገሩት ሰውዬአቶ ሐይለማርያምደሳለኝ በግልፅ እንዳስቀመጡት የአካባቢ ምርጫ እንዲሁ
ለይስሙላ የሚደረግ እንጂ ይህ ነው የሚባልፋይዳ የሌለውመሆኑን አስምረው ተናግረዋል። በመሆኑም አይደለምና በዚህ
በዘቀጠ መንግስት የተዘጋጀ ምርጫ ይቅርና በዲሞክራሲያዊመንግስት እንኳ ቢካሔድ የአካባቢ ምርጫ ይህ ነው የሚባል
ፋይዳ የለውም። ስለሆነም በ2007 አ.ል የሚካሔደው ሀገራዊምርጫ ላይ ልንወስደው የሚገባው አቋም ጊዜው ሲደርስ
የሚወሰን ሲሆን አሁን ፊትለፊታችን የተደቀነው የአከባቢምርጫ ላይ ተሳትፎ ማድረግ ግን የመንግስት አዳማቂ
ከመሆን በዘለለ ይህ ነው ሚባል ጠቀሜታ ያለው አይደለም።

ሦስተኛ:- እምነት የሚጣልበት ተቃዋሚ ፓርቲ የለም ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ጩኸታችን የፍትህ እጦት መሆኑ
ለማንም ግልፅ ሆኖ በሚገኝበትበዚህ ሰዓት ላይ እንኳ የዜጎችመበደል ሊያስጨንቃቸው የሚገቡት የተቃዋሚ ፖለቲካ
ፓርቲዎች በጣም በሚያሳዝን መልኩ በኛ ጉዳይ ላይ ያሳዩትልስላሴ ከነሱ የማይጠበቅ መሆኑ ለሁላችንም እሙን ነው።
በመሆኑም በአሁኑ ሰዓት ይህ ነው የሚባል እምነት የሚጣልበትተቃዋሚ ፓርቲ እንዳይኖር ሆኗል። ይህ በሆነበት ሁኔታ ደግሞ
የኛ ጉዳይ ያላስጨነቃቸውን አካላት መምረጥ መንግስትንለተጨማሪ ጭቆና ከመምረጥ ተለይቶ አይታይም።
በመሆኑም ከላይ በጠቀስኳቸው ምክንያቶች የተነሳምርጫውን መሳተፍ በአእምሮዋችን ውስጥ ውል ሊልብንም
አይገባም፤ ከዚህ አንፃር ደግሞ ከ”ድምፃችን ይሰማ” ገፅያልዘገየ ማሳሰቢያ እንሻለን አደራ!!!ምንሊክ ሳልሳዊ