በአባይ ግድብ ሸፋን ህዝበ ሙስሊሙ ወገናችን ተደናግሮ እንዳይጠለፍ

ልብ ይበሉ !
በሳውዲ አረቢያ ሪያድ ኢትዮጵያ ኤንባሲ ውስጥ የመሸጉት ወያኔዎች ፌብሪዋሪ 7 2013 በአባይ ግድብ ሸፋን በህዝበ ሙስሊሙ ወገናችን ተቃውሞ ውጥረት ውስጥ የገባውን የወያኔን ስረአት ማጠናከሪያ ገንዘብ ከሪያድ ህዝብ ለመሰብሰብ በየጠጋጥጉ የሚለጥፉት ወረቀት በህዝበ ኢትዮጵያውያን ነዋሪ በመገንጠል ላይ መሆኑንን የሪያድ እና አካባቢው ኢትዮጵያውያን ወጣቶች ማህበር አባላት አረጋገጡ።

ይህንንም ተከትሎ በሳውዲ አረቢያ የሪያድ እና አካባቢው ኢትዮጵያውያን ወጣቶች ማህበር በወያኔ ላይ የጀመረውን ትግል በማጠናከር በአባይ ግድብ ሽፋን ህዝቡ ተደናግሮ እንዳይጠለፍ ወጣቶቹ ሰሞኑንን መንፉ እና አካባቢው ፡ ነስሪያ ነሲም እና በተለምዶ ኡመል ሃማም እየተባሉ በሚጠሩ ኢትዮጵያውያን በብዛት በሚኖሩባቸው መንደሮች በራሪ ወረቀቶችን በመበተን ለኢትዮጵያዊው ነዋሪ ሰፊ ግንዛቤ በማስጨበጥ፡ላይ መሆናቸውን የግበረ ሃይሉ አስተባባሪ ዛሬ በሳውዲ አረቢያ የሪያድ እና አካባቢው ኢትዮጵያውያን ወጣቶች ማህበር መደበኛ ስብሰባ ላይ ባቀረበው ሪፖርት ገልጾል። ቅስቀሳው አሁንም በተለያዩ ስልቶች እንደሚቀጥል ለመረዳት ተችሏል።

በሳውዲ አረቢያ የሪያድ እና አካባቢው ኢትዮጵያውያን ወጣቶች ማህበር ።