ሰበር ዜና ሳውዲ አረቢያ የኢትዮጵያ ቆንስላ በር ላይ 1 ወጣት ረዳት አጥቶ ህይወቱ አለፈች።

ሰበር ዜና ሳውዲ አረቢያ ጅዳ ከተማ የወያኔ ዲፕሎማቶች የመሸጉበት የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽ/ቤት በር ላይ ወድቆ የወገን ያለህ የሚል የሲቃ ድምጽ ሲያሰማ የነበረው ወጣት ረዳት አጥቶ ህይወቱ አለፈች።

በመካከለኛ የእድሜ ክልል ውስጥ እንደ ሆነ የሚገመተው ይህ ወጣት ወገን አለኝ ብሎ ጅዳ በሚገኘው የኢትዮጵያ ቆንስል ጽ/ቤት በር ላይ ትላንት ወድቆ ጣረሞት ሲያሰማ እንደነበር ከጅዳ በሳውዲ አረቢያ የጀርመን ድምጽ ራዲዮ ፕሮግራም ዘጋቢ አቶ ነብዩ ሲራክ በወቅቱ ጉዳዩን ሰምቶ እንደነበር ይግለጽ እንጂ አቶ ነብዩን ቦታው ላይ በካላል ያዩት አንዳንድ በጅዳ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን ለማህበራችን በላኩት መለዕክት ገልጸውልናል።

አቶ ነብዩ በወቅቱ የዚህን ወጣት ህይወት ከሞት ለመታደግ ህክምና ማግኘት የሚችልበትን መላምት በመፍጠር ወገናዊ ነት እና ረህራሄ ያልፈጠረባቸውን የወያኔ ጀሌዎች አስተባብሮ የዚህን ኢትዮጵያዊ ወጣት ችግር ቀርቦ መረዳት ሲቻል ወጣቱ በዚህ ፎቶ ላይ እንደተገለጸው ወድቆ ብርድ እና ጸሃይ ሲፈራረቅበት አይቶ ማለፉ የሚያሰተዛዝብ ከመሆኑም በላይ እራሱን የጀርመን ድምጽ ራዲዮ ጣቢያ ዘጋቢ ነኝ ብሎ የሚጠራውን የአቶ ነብዩ ሲራክ ልብ እንደ ወያኔዎቹ በኢትዮጵያውያን ላይ ምን ያህል እየደነደን መምጣቱን ያሳያል።

በአጠቃላይ ኢትዮጵያዊ ወጣት በንጋታው ሞቶ ማየቱን የገለጸው አቶ ነብዩ ሲራክ በወጣቱ ሞት የተሰማውን ሃዘን በፌስ ቡክ ገጽ ላይ ለማስነበብ የሞከረው ሙሾ ከተለመደው አስመሳይ የአዞ እንባው እንደ ማይለይ አያሌ የጅዳ ነዋሪዎች ያወጋሉ።
በሳውዲ አረቢያ የሪያድ እና አካባቢው ኢትዮጵያውያን ወጣቶች ማህበር