የ 38 ዓመቱ ሕወሓት የፍጥጫና የርስ በርስ መበላላት

የትግራይ መሳፍንት እርስ በራሳቸው ሲናቁሩና ሲገዳደሉ ያየች አንዲት የጎጃም አዝማሪ ስታንጎራጉር 

ጎጃሜ  ቡዳ ነው ስትሉ ስትሉ
አላያችሁም ወይ ትግሬ አርስ በርስ ሲባሉ ::

በማለት ትልቁ የታሪክ ጠባሳ በአንዲት ዓረፍተ ነገር አጠቃለለች ይባላል። ይህ የትናንት ታሪክ ነው። ዛሬስ ምን እየተደረገ ነው ያለው? የዝንጀሮ መንገድ ቢከተሉት መጨረሻው ገደል ነው እንዲሉ የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ት
ግራይ  የህወሓት ታሪክ ዞሮ ዞሮ  የእርስ በርስ መበላላትና የመናቆር ታሪክ ነው። በገዛ ወንድሙ
ላይ መጨከን፣ የገዛ ወንድሙን ገድሎ አካኪ ዛረፍ ማለት፣ የገዛ ወንድሙን ገድሎ ጀግና ነኝ ማለት፣ በገዛ ወንድሙ ላይ በሐሰት መስክሮ ለጥቕምና ለስልጣን ሲባል አሳልፎ መስጠት፣ በንፁኃን ደም እየነገዱ የግል ስልጣንን ማደላደል የመሳሰሉትን አስነዋሪ ተግባራት ዛሬ ከአቶ መለስ ዜናዊ አገዛዝና አመራር
የወረስናቸው ሰይጣናዊ አስተሳሰቦችና ፓሊሲዎች ናቸው። የሚገርመውና የሚያሳዝነው ደግ ሞ የህወሓት አረሜናዊ ባህርይ እንደ ኤይድስ በሽታ ወደ ሌሎች አካባቢዎች እየተዛመተ መምጣቱ ነው።
አቶ መለስና አቶ ስብሓት ነጋ በህወሓት የጥሎ ማለፍ ጉዞ እስካሁን ድረስ እነማን እያስወገዱ ስልጣናቸውን እንዴት እየገነቡ እንደመጡ ጥቂት ልበል፡
-በመጀመሪያዎቹ አካባቢ በድርጅቱ ውስጥ አውራጃዊነት (ሕንፍሽፍሽ) ተፈጥሯል በሚል ሰ
በብ “አሽዓ” (አክሱም ሽሬ ዓድዋ) ተብሎ የሚጠራ በነ አቶ ስብሓት ነጋ የሚመራ ጠባብ ቡድን አብዛኞዎቹ ከሌላ የትግራይ አውራጃዎች ማለት ከእንደርታ፣ ከራያ አዘቦ፣ ከአጋሜና ከተምቤን አካባቢ የመጡትን ታጋይ ወጣቶ ች እንደመቱዋቸው ታሪክ ይናገራል።
በፈረንጆች አቆጣጠር በ1985ዓ/ም በነ አቶ ግደይ ዘርኣፅዮንና ዶክተር አረጋዊ በርሄ ላይ የተወሰደው እርምጃም ተመሳሳይ ነው። በተለይም አቶ መለስ ሌሎች አስጊ ናቸው የሚላቸውን ሰዎች አፅድቶ ካ
ጠናቀቀ በኋላ በሁለተኛው ምዕራፍ ላይ ጣቱን የቀሰረው በነ አቶ ግደይ ዘርአፅዮን ላይ ነበር። የድራማው ዋና
ተዋናይም አቶ ስብሃት ነበር።
የክሱ ይዘትም “አረጋዊ በርሄ መለስን ለመግደል አሲሮ ነበር” የሚል በአቶ ስብሓት ነጋ የቀረበ የምስክርነት ቃል መነሻ ያደረገ እንደ ነበር ይታወሳል።
ማርክሰ ለኒን ሊግ ትግራይ (ማሌሊት) ከተመሰረተ ማግስትም “የቻለ ይሩጥ፣ ያልቻለ ያዝግም፣ ያበቃለት ይለይለት” በሚል መሪ መፈክር ፀረ ኮሚኒዝም እየተባለ የተባረረ፣ የተመታ፣ የተሰወረና የታሰረ
ታጋይ ቁጥሩ ብዙ ነው።
ከዚያው ከትግራይ ሳንወጣ የድርጅቱ ማእከላይ ኮሚቴ አባል የነበረው በአቶ ተኩሉ ሃዋዝ ላይ የተወሰደው የግዲያ እርምጃም ፀረ ህወሓት/ማሌሊት አመለካከት ታራምዳለህ በሚል እንደነበር ብዙዎቹ ይስማማሉ። 
 የመንግስት ስልጣን ከያዙ በኋላስ  

የህወሓት መሪዎች አዲስ አበባ ገብተው የመንግስት ስልጣን ከያዙ በኋላም በበረሃ የትጥቅ ትግል ዘመን ድብቅ አጀንዳሆነው ውስጥ ለውስጥ ይሰራባቸው የነበሩት ሶስት ነገሮች ጋሃድ እየወጡ መሄድ ጀመሩ።
አንደኛ በኤርትራ ጉዳይ ላይግልፅ   የሆነ ልዩነት መታየት ጀመረ። ሁለተኛ በድርጅታዊና በመንግስታዊ መዋቅሮች በሚሰሩ ሰዎች መካከል የጥቅም ግጭትና የአመለካከት ክፍተት እየተፈጠረ ሄደ። 
ሶስተኛ በህወሓትና በሌሎች የኢሕአዴግ አባል ድርጅቶች መካከል የሎሌና የጌታ (የሞግዚትነት) ግንኙነት እየተፈጠረ መጣ። እስካሁን ድረስ በህወሓት መሪዎች መካከል እየተካሄደ ያለው የፍጥጫና የርስ በርስ መበላላት ሂደትም በነዚህ ሶስት ነገሮች ላይ የተመሰረቱ ናቸው።
1. በኤርትራ ጉዳይ ላይ በግልፅ በአጀንዳ ተይዞ መነጋገር የተጀመረው ገና ከደርግ ውደቀ
ት ማግስት ነው። አንዴ ሞጎደኞች ሌላ ጊዜ ደግሞ እሳት ጫሪዎች፣ ጦርነት ናፋቂዎች፣ ወዘተ እየተባሉ በተለያየ ስም ሲጠሩ የነበሩት እነአቶ ገብሩ አስራትከኤርትራ ጋር ያለንን ግንኙነት ገደብ ይኑረው የሚል አመለካከት ቢኖራቸውም አቶ መለስ ደግሞ እሳትን አንንካ በማለት ሾላ በድፍን የሆነ አካሄድ ይከተሉ እንደነበር እሙን ነው። በዚሁ ልዩነት እን ዳሉ ሻዕቢያ በኢትዮጵያ ላይ ወረራ ለማካሄድ ምቹ ሁኔታ ተፈጠረለት። ከወረራ በኋላም ልዩነቱ እየሰፋ መጣ። በመጨረሻም 13 ከፍተኛ የህወሓትማ/ኮሚቴ አመራር አባላት ድርጅቱን ጥለው ወጡ። 5 ጀነራሎችን ጨምሮ ብዙ ኰለኔሎችና  ነባር የህወሓት ታጋዮች  ድርጅቱን ጥለው ሲወጡ ብዙዎቹም ታሰሩ። 
 በዚህ ምክንያት እነአቶ መለስና እነ አቶ ኢሳያስ አፈወርቂ ምኞታቸውን ስለተሳካ የልብ ልብ ተሰማቸው። የትግራይ ብሄረተኝነት ጭንቅላቱን ተመታ ተባለ። ህወሓትም ከድርጅትነት ወደ ቤተሰባዊ የግል ኩ
ባንያነት ተለወጠ። መለስም ነባሩ የህወሓት ታጋይ እያፀዳ ቁልፍ የሆኑ ቦታዎችን በታማኞቹ በኤርትራውያን እንዲ ያዙ አድርጓል። አቶ በረከት ስምዖንና ቴድሮስ ሐጎስ ሙሉ በሙሉ ኤርትራውያን ቢሆኑም ከመለስ ቀጥለው ስልጣን ያላቸው እነሱ ናቸው።
የህወሓት ማ/ኮሚቴና በሚኒስትር ማዕረግ የመለስ አማካሪ ሆኖ ሲሰራ የቆየው ሃለቃ ፀጋይ በርሄ ግማሽ ጎኑ ኤርትራዊነው። ሌላው በሚኒስትር ማዕረግ የመለስ አማካሪ ሆኖ ሲሰራ የነበረው ሂያብ ሱራፌኤልም
ሙሉ በሙሉ ኤርትራዊ  ነው። የትግራይ ፕረዚዳንት የአባይ ወሉ ሚስት ወ/ሮ ትርፉ የህወሓት ማ/ኮሚቴ አባል
ትውልድዋ ሙሉ በሙሉ ኤርትራዊት ናት። የህወሓት ማ/ኮሚቴ የአቶ አባዲ ዘሞ ሚስት ወ/ሮ ሂሪቲ ሱራፌኤል የትግራይ የዳኝነት ሃላፊ ሙሉ በሙሉ ኤርትራዊት ናት።
2. ሌላው በህወሓትና በሌሎች የኢሕአዴግ አባል ድርጅቶች መካከል ያለው የስልጣን ክፍፍል አለመመጣጠን ነው።መለስ እነ ስየና እነ ገብሩ ለመምታት የብሄረ አማራ ድርጅት F ብአዴንን እንደ መሳሪያ
ተጠቅሞበታል። የህወሓት ለሁለት መሰንጠቅና መከፋፈል ከማንም በላይ ያስደሰተው እነ አዲሱ ለገሰንና በረከት
ስምዖንን ነው። መለስ ከማንም በላይ እንደ ትልቅ አደጋ ሲያይ የነበረው የፓለቲካ ተቃዋሚ ድርጅቶች ሳይሆን በህወሓትና በሌሎች የኢሕአዴግ አባል ድርጅቶች ያለው ውስጣዊ ሽኩቻ ነው። ህወሓት በስልጣንም፣ በሀብት ክፍፍልም ሆነ በመከላኪያ አካባቢ የአንበሳ ድርሻ ይዟል የሚል ለረጅም ጊዜ ውስጥ ለውስጥ ሲብላላ የቆየ አመለካከት እንዳላቸው ማንም ያውቃል። መለስምይህን አደጋ በማጤን የየድርጅቶቹን መሪዎችና ካድሬዎች ያጠመዳቸውና የተቆጣጠራቸው በስኳር (በሙስና) ነው።
እያንዳንዱ የህወሓት/ኢሕአዴግ አመራር በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በሙሱና የተዘፈቀ ስለሆነ አፉን ሞልቶ መቃወም አይችልም። 
 ከመለስ ህልፈት በኋላ
ከመለስ ህልፈት በኋላ በህወሓት/ኢሕአዴግ አካባቢ አስደንጋጭ ክስተቶች ተፈጠሯል። አንድኛ የመንግስት ስልጣን ክፍተት ነው። በእውነት በአሁኑ ጊዜ አገሪትዋን እየመራ ያለው ማን ነው? የሚለው በትክክል
የተመለሰ አይደለም። በአንድ በኩል የመለስ ራእይ ወራሾች ነን የሚሉ በበረከት ስምዖንና በወ/ሮ አዜብ የሚመራ ቡድን እንዳለ ይታየኛል። 
በሌላ በኩል ደግሞ የሁሉም ጥበብ፣ የዕድገት ምንጭና የትኩረት ማዕከል ተደርጎ እየተወሰደ ያለው መከላኪያ
ም በመንግስታዊ አመራሩ ውስጥ ትልቅ ድርሻ እንዳለው ቁልጭ ብሎ እየታየ ነው። በሶስተኛው ረድፍ ደግሞ አቶ ሀይለማሪያም ደሳለኝ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው መቅረባቸው ምን ያህል መፍትሄ ሊያመጣ ይችላል? የሚለው ነው። ይህ ሁሉ ሁኔታ ተደማምሮ ወዴት ሊወስደን ይችላል? ብሎ መጠየቅም የግድ ይላል።
ከመለስ ህልፈት በኋላ የተፈጠረው ሌላው ክስተት መደናገጥን ነው። በአቶ መለስ ሞት ከማንም አባል ድርጅቶች በላይ መደናገጥና አጣብቅኝ ውስጥ የገባው ህወሓት ነው። ምክንያቱም ህወሓት እንደ ድርጅት
ሳይሆን እንደ ግል ኩባንያ ተይዞ ፓለቲካዊ ካፒታሉ በልቶ የጨረሰ፣ ዘመን የጣለውና በቁሙ
የሞተ ድርጅት ሆኖ ስለተገኘ ነው። ስለሆነም የመለስን ቦታ ለመተካት ቀርቶ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርነት ደረጃም ቢሆን ብቁ ሰው ለማቅረብ አል ቻለም ነበር። አሁንም ገናያልተረጋጋና በሽኩቻ ላይ ያለ ድርጅት ነው።
ሰሞኑን እንደሚወራው ህወሓት አሁንም ለሁለት ቡድን ተሰንጥቀዋል ይባላል። አንደኛውቡድን በነበረከት፣ አዜብ፣ እነ አባይ ወሉና ሌሎች ያካተተ ሲሆን ሁለተኛው ቡድን ደግሞ በነአቶ ስብሃት ነጋ የሚመራ
ነው። አቶ ስብሃት ነጋ “ህወሓትን እናጠናክር” የሚል መፈክር የያዘ ቢሆንም ግልፅ ራዕይና ፓለቲካዊ መስመር የሌለው የጎበዝ አለቃ እንቅስቃሴ እስከሆነ ድረስ ሩቅ የሚሄድ አይሆንም። በኤርትራ ጉዳይ ላይ ያለው አመለካከትም ከነበረከት ስምዖን የተለየ አይደለም። አቶስብሃት ቀደም ሲል ከነ አዜብ ጋር በነበረው የግል ቅራኔ ምክንያት ከህወሓት ጋር አብሮ የተጣለ ብቻ ሳይሆን በታሪኩምሆነ በፓለቲካዊ አመለካከቱ ኢፍትሃዊና ኢዲሞክራሲያዊ ሰው ነው። ስብሃት ህወሓትን ከአዜብና ከበረከት እጅ ፈልቅቆለማውጣት ቀርቶ ለራሱም መከላከል የማይችል ጥርስ እንደሌለው ጅብ ሜዳ ላይ የወደቀሰው ነው። ስብሓት በትግራይ
ዘንድ የሚታወቀው እንደ ነፃ አውጪሳይሆን ነገር አመንጪ፣ ቂመኛ፣ አውራጃዊ፣ ስነ ምግባርና ሃላፊነት የጎደለው አውቆ አበደ ሽማግሌ እየተባለ ይጠራል። ስብሓትን በማየት ህወሓት ምን ዓይነት ድርጅት መሆኑ
ን መገንዘብ ይችላሉ የሚል አባባልም አለ። ስለዚህ ሌላ ዓይነት መንገድ ካልመጣ በስተቀር ህወሓት/ኢሕአዴግ ከበረከት፣ ከአዜብና ከቴድሮ ሓጎስ እጅ ይወጣል ብሎ ማሰብ አይቻልም። ትእዝብት አድማሱ