አዲስ መልክ ያለው ህወሃት ብቅ ይል ይሆን?በተስፋዬ ገብረአብ/የወያኔ ኤክስፐርት

በ ምንሊክ ሳልሳዊ
የመለስ ዜናዊ የእረፍት ዜና ከተሰማበት ጊዜ አንስቶ በህወሃት ካምፕ ከፍተኛ ውጥረት ተከስቶአል። ከኮሎኔል በላይ ማእረግ ያላቸው የህወሃት መኮንኖች ልጆቻቸውን ወደ ውጭ ሃገር እያሸሹ ሲሆን፣ በገንዘብ ዝውውር ባንኮችን ሲያጨናንቁ ሰንብተዋል። መንገዱ ወዴት ያደርሳል?

· ከህወሃት አባልነት ገለል ብለው የቆዩ ነባር የፖለቲካ ሰዎች በድርጅቱ ዙሪያ መሳባሰብ ጀምረዋል። ህወሃትን ለማዳን ከተንቀሳቀሱት መካከል ጄኔራል ፃድቃን እና አማረ አረጋዊ እየተጠቀሱ ነው። አዲስ መልክ ያለው ህወሃት ብቅ ይል ይሆን?

· በስብሃት ነጋ እና በበረከት ስምኦን መካከል ልዩነቶች ተከስተዋል። ስብሃት ነጋ የህወሃትን የበላይነት ለማረጋገጥ ህወሃትን መዋቅር በማንቀሳቀስ ላይ ሲሆን፣ በረከት ስምኦን የብአዴንን በላይነት ለማረጋገጥ ይዳክራል። የህወሃት እና የብአዴን የስልጣን ሽኩቻ ኢህአዴግን ሊያፈራርሰው ይችል ይሆን?

· የሳሞራ የኑስ ስልጣን ከመለስ እረፍት ጋር አብሮ መሞቱ ግድ ነው። ሰአረ መኮንን እና ታደሰ ወረደ የተባሉት ጄኔራሎች ስልጣን የተረከቡ ይመስላሉ። ሰአረ መኮንን ከስዬ ጋር ካለው ቅርበት አንፃር፣ መፈንቅለ መንግስት ለማድረግ ይሞክር ይሆን?

· አሜሪካኖች በኢትዮጵያ አዲስ የጥምር መንግስት እንዲቋቋም ውስጥ ውስጡን ጥረት እያደርጉ መሆኑ እየተሰማ ነው። ግንቦት7 እና ኦነግ ጠመንጃ አስቀምጠው ወደ ጥምር መንግስት ምስረታ እንዲገቡ ይጠየቁ ይሆናል። ለዚህ ምላሻቸው ምን ይሆን?

· በኢትዮጵያ እና በኤርትራ ድንበር አካባቢ ከፍተኛ ውጥረት መኖሩ ይሰማል። ሻእቢያ መለስ እንደሚሞት ያወቀው ሙሴቪኒ አስመራ ሄዶ ከኢሳይያስ ጋር በተገናኘ ጊዜ መሆኑ ይነገራል። መለስ በሙሴቪኒ በኩል ለኢሳይያስ የላከው መልእክት ምን ነበር?ምንሊክ ሳልሳዊ