ላለመላላጥ መንፈራገጥ...የጀርመን ራዲዮ እና ድብቅ ሴራው?ከትላንትናው የቀጠለ

 ላለመላላጥ መንፈራገጥ...የጀርመን ራዲዮ እና ድብቅ ሴራው(ክፍል 2)

መታረም ያለበት ሁሉ በሁላችንም ወገን ባስቸኳይ እንዲታረም እየጠየኩ ይህንን ጽፌአለሁ::
በትላንትናው ብሎግ ፖስት ላይ ራሱን የጀርመን ድምጽ የኣማርኛ ፕሮግራም እያለ ስለሚጠራው እና በሳኡዲ አረቢያ  ስላስቀመጠው እና ወያኔን ያዘለው ነብዩ ሲራክ ስለተባለው የትርፍ ጊዜ ጋዜጠኛ ነው ስለተባሉው አንድ ጹሁፍ ማውጣታችን ይታወሳል ::  http://minilik-salsawi.blogspot.com/2013/02/blog-post_6305.html
የሀው የራዲኦ ጣቢያ ሽብርተኝነትን ለመቆጣጠር በሚለው የጌቶቹ መርህ በመተራስ የወያኔን ድብቅ አላማ መርዝ በመርጨት የሙስሊሙን ህጋዊ የመብት ጥያቄ ላማድበስበስ ሲሞክር በሪያድ በሚገኙ ኢትዮጵያውያን ያላሰለሰ ጥረት ተጋልጧል::
የነብዩ ሲ ራክ  መልስ ያንብቡት
      
ወገኖቸ . . .
በሰበር ዜና በተሰናዳው ከእውነተ የራቀ ወቀሳ ሳልጎሸም በተለያዩ መንገዶች የሚሰነዘርብነኝ ዛቻ መስፈራሪያና ስድብ ይህ ነው ብየ ለመግለጽ ይከበደኛል። ከሁሉም በላይ በማንነታቸው ላየ ጭንብል አጥልቀው የሚያንገላቱኝ ወገኖች ሃሳባቸውን በነጻነተ ለማሰተናገድ ይቻለኝ ዘንድ ያላደረግኩት ሙከራ አልነበረም። የሚያሳዝነው በኔ ላይ የተሰነዘረው ወቀሳ ሳይሆን የጀርመን ራዲዮ ሳውዲ በምንኖር ኢትዮጵያውያን ጉዳይን "ጉዳየ ብሎ አይዘግብም" ተብሎ በገሃድ በማይዳሰሰው "ማህበር "የተሰጠው ስም ከእውንት የራቀ መሆኑን አውቃለሁና አሳዝኖኛለ!የሪያድ ተቃውሞ ያልዘገብኩበት ዋና ምክንያት እንደ ተባለው ሳይሆን በወቅቱ የጀርመን ራዲዮ ቋሚ ተቀጣሪ ባለመሆኔ ለግል ስራ ምክንያት ከአካባቢው ርቄ ስለነበርኩበት እንደሆን አንባቢ ግንዛቤ እንዲያገኝ እዎዳለሁ !
ከመንግስት ደጋፊዎችና ከተቃዋሚዎች ለሚሰነዘረው ወቀሳ ዛቻና ማስፈራሪያ አዲስ ይደለሁም፡፡ ይልቁንም ወቀሳና አስተያየቱ በአግባቡና በስርአቱ እስከቀረበ ድረስ እማርበታለሁና እቀበለዋለሁ ! የምሰራው ለጥቅምና ለማንም ለማጎብደድ ሳይሆን ለህሊናየ አድሬ ነው!የወገኖቸን ድምጽ አሰማ ዘንድ እየከፈልኩት ያለው መስዋዕትነት የዜግነት ግዴታየን መወጣቴን ያመላክተኛልና ነፍሴ ሁሌ ሃሴትን ታገኛለች !
ነቢዩ ሲራክ
ከትላንትናው የቀጠለ

ላለመላላጥ መንፈራገጥ...የጀርመን ራዲዮ እና ድብቅ ሴራው(ክፍል 2)
መታረም ያለበት ሁሉ በሁላችንም ወገን ባስቸኳይ እንዲታረም እየጠየኩ ይህንን ጽፌአለሁ::
በትላንትናው ብሎግ ፖስት ላይ ራሱን የጀርመን ድምጽ የኣማርኛ ፕሮግራም እያለ ስለሚጠራው እና በሳኡዲ አረቢያ  ስላስቀመጠው እና ወያኔን ያዘለው ነብዩ ሲራክ ስለተባለው የትርፍ ጊዜ ጋዜጠኛ ነው ስለተባሉው አንድ ጹሁፍ ማውጣታችን ይታወሳል ::  http://minilik-salsawi.blogspot.com/2013/02/blog-post_6305.html
የሀው የራዲኦ ጣቢያ ሽብርተኝነትን ለመቆጣጠር በሚለው የጌቶቹ መርህ በመተራስ የወያኔን ድብቅ አላማ መርዝ በመርጨት የሙስሊሙን ህጋዊ የመብት ጥያቄ ላማድበስበስ ሲሞክር በሪያድ በሚገኙ ኢትዮጵያውያን ያላሰለሰ ጥረት ተጋልጧል::

ይህንን ተከትሎ በዛሬ ዘገባው ላይ ከጀርባ ያለበትን ተጽእኖ ለመሸፋፈን "ወቀሳ እና ዶቼ ቬለ" በሚል ርእስ  ወሸከቴ ወያኔያዊ ሃራካት ሊደምርብን በመሻት ማንነቱን ለመሸፋፈን ደፋ ቀና ሲል ተስተውሏል::
ድሮም የተቋቋመበት አላማ የምእራባውያኑን ፍላጎታ ማስተላለፍ መሆኑ ሲታወቅ ምእራብያውያኑ ደሞ በራሳችን ሆድ አደር ራሳችውን በሸጡ ዜጎች ያላቸውን ጸረ እስልምና ድብቅ አቋም ያራምዱባቸዋል::

በቦንድ ስም ገንዘብ ስብስቦ ስልጣኑን ማራዘሚያ ሊያደርገው ያሰበው የወያኔ መንግስት በሪያድ ኢትዮጵያውያን በደረሰበት ተቃውሞ  ተልእኮው ከሽፎ መበተኑ የታወሰበትን እለት እንዲመለከት የተጠራው ሰው ባገኘው ወያኔያዊ ጉርሻ ከነመቅረጸ ድምጹ ተደብቆ ዉሎ በቴክኒክ እክል ማሳበብ ላለመሞት መንደፋደፍ ነው::
አስቀድሞ የደረሰኝ ጥቆማ የለም በማለት ለማድበስበስ መሞከር ራስን ለመደበቅ በሚደረግ ሩጫ ዉስጥ መጋለጥ እንዳለ እያሰቡ መኖር ያስፈልጋል::

ከጀርባቸው በወያኔ ጉርሻ የሚንቀሳቀሱት የጀርመን ራዲዮ ጋዜጠኞችነብዩ ሲራክ የግድ ፎቶ ላንሳችሁ ድምጻችሁን ካልቀረጽኩ ዜና መስራት ይሳነኛ ብሎ የምስክርነት ቃሉን የሰጠበት አካሄድ ማንነቱን የበለጠ ያጎለዋል:: ከዚህ የበለጠ ራስን ማጋለጥ ሚን አለ??  ደሞ የህ ነብዩ የሚባል የወያኔ ሹባሽ ሚንዲነው እና ፎቶ የሚአነሳው? ለማንስ ለማስተላለፍ  ፈልጎ ነ? ሀዶ በ አይኑ የተመለከተውን አይዘግብምን? የአህያ ገለብ.....እንደተባለው...

እንደ ሳኡዲ ኢትዮጵያውያን  አባባል :-
""ብዙ አባሎቻችን ዛሬ ሃገር ሄደው ሳይመጡ የቀሩበት አጋጣሚ ወያኔ ንብይ ሆን ሳይሆን በ1997 እስከ አዲስ አበባ ዘልቀን ባደረግነው ትግል የተንግበግቡት ወያኔዎች ማህበራችን ውስጥ ዘልቀው በመግባታቸው ነው ዛሬ ግን ሁሉም ነገር ተዘግቷልወረቅት በየግድግዳው እየለጠፉ አብዩት ቀርቷል::
እነ ነብዩ ይህን ሃቅ መጋት ተስኖቸው ዛሬ የማህበራችን ስራ ለማግኘት የቆጥ የባጡን የቀባጥራሉ ጽ/ቤታችንን ይጠይቃሉ የኛ ነጻ መሬት እና ቤሮ የእያንዳንዱ እውነተኛ ልብ ነውግብጽ ላይ የፈነዳው አብዮት ቢሮ ኖሮት አሊያም
የወጊያ ነጻ መሬት ኖሮት አይደለም እኛ ሳንገል እየሞትን ነጻነታችንን ለማወጅ የተዘጋጀን ሰላምዊ የነጻነት አርበኞች ነንን !!ትግሉ ይፋፋም""
እስኪ ከዚህ በላይ ሚን እስከምትባሉ ነው የምትጠብቁት....
እናንተ የተቃውሞውን ይዘት ከመዘገብ ይልቅ የነብዩ ማንነት መደፈር አንገብግቧቹዋል...እውነት ሲነገር እኮ አይዋጥላችሁም የሚያጎርሳቹህ ወያኔ ነዋ::
ስለ ማህበሩ ምንም እውቅና የለለው ሰው እየፈለጋችሁ ከምትጠይቁ አርፋችሁ ብትቀመጡስ ለራስዋ የላወቀች ነው የሆናችሁት የሙስሊም ህዝብ ህጋዊ ጥያቄ እንዳትቀበሉ የሚያደርጋችሁ የጀርመን መንግስት ወያኔ በሚልክለት ሃሰተኛ መረጃ አሸባሪነት እንዳይስፋፋ በሚል አባዜ ታሽጋቹህ ከወያኔ በሚሰጣቹህ ጉርሻ ተጀቡናቸሁ እውነትን ብታድበሰብሱም ሙስሊሙ ወገናችን ነጻ ይወጣል !!ኮሚቴዎቻችን ይፈታሉ!! እኛም ኢትዮጵያውያን አቡበከር ...ነን!!!!
ድል ፍትህ እና ነጻነት ለተጠሙ ሙስሊም ወገኖቻችን ይሁን!!!
ይቀጥላል::