በአባይ ግድብ ስም ከኢትዮጵያ ስንዴ በህገወጥ መንገድ እየወጣ መሆኑ ተጠቆመ        
ከባለፈው ወር ጥር 2005 ዓ.ም. መጨረሻ አካባቢ ጀምሮ በርካታ ተሳቢዎችከኢትዮጵያ ስንዴ ጭነው በድብቅ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አቋርጠው ወደሱዳን ሊሄዱ ሲሉ መያዛቸው ተጠቆመ፡፡
እስካሁን ማንነታቸው በትክክል ለመለየት ያልተቻሉት ግለሰቦች ስንዴውን ጭነው ወደ ሱዳን ወስደው ለመሸጥ ሳያስቡ እንዳልቀሩ ግምታቸውን የሰጡን የመረጃ ምንጮቻችን፤ መኪኖቹ በኬላ ጠባቂዎች “ሊፈትሹ ሲሉ ለአባይ ግድብ ሲሚንቶ ጭነን ነው”በማለት ለማታለል ቢሞክሩም የጥበቃ ሰራተኞቹ በመጠራጠር ሲፈትሹ ሁሉም ተሳቢዎች የጫኑት ሲሚንቶ ሳይሆን ስንዴ ሆኖ መገኘቱ ተጠቁሟል፡፡ በመጨረሻም ባልታወቀ ምክንያትበቁጥጥር ስር ውለው የነበሩት ከ15በላይ ስንዴ የያዙ ተሳቢ ተሸከርካሪዎችወደ አዲስ አበባ እንዲመለሱ ቢደረጉምመንገድ በመቀየር በኢሉባቦር በኩል ከሀገር እወጡ መሆኑን ለጉምሩክ
ቅርበት ያላቸው ምንጮች ከስፍራውበተለይ ለፍኖተ ነፃነት ገልፀዋል፡፡ተጭኖ ወደጎረቤት ሀገር እየሄደ ያለውም
ስንዴ በርሃብ ለተጎዱ ኢትዮጵያውያን እርዳታ የመጣ እንደሆነም ተጠቁሟል፡፡
የጋዜጣው ዝግጅት ክፍልም ጉዳዩ የሚመለከተውን የግብርና ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ የሆኑትን አቶ
ታረቀኝ ፅጌን ጠይቀናቸው የሚያውቁት ነገር እንደሌለ በመግለፅ ወደ አደጋመከላከል ቢሮ ሊመሩን ችለዋል፡፡ ነገር ግን የአደጋ መከላከል በበኩሉጉዳዩ ይመለከታቸዋል ወደ ተባሉት የእርዳታ ስርጭት ሎጅስቲክ ክፍልመርተውናል፡፡
የስርጭት ሎጅስቲክክፍል ይመለከታቸዋል የተባሉት አቶደመላሽ እሸቴ በበኩላቸው በዚህ ወቅት ወደ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ የተላከ የእርዳታስርጭት የለም፣ የክልሉ ባለስልጣናትስ ለምን አልያዙም? በማለት ምዕራብኢትዮጵያ እርዳታ ስርጭትን በተመለከተ
በይበልጥ አለቆቼ ዳይሬክተሩን ጨምሮ ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ስብሰባ ላይ ስለሆኑ ስልካችሁን ተውልንና እንደውላለን
ቢሉም ይህ ዜና እስከተጠናከረበት ሰአት ድረስ ሊደውሉልን አልቻሉም፡፡ ይሁን እንጂ እንደ ምንጮቻችን ጥቆማ ከሆነ ከቤኒሻንጉል አሶሳ ኬላ ላይ ተይዘው የነበሩት የእርዳታ ስንዴ የጫኑት ከ15 በላይ ተሳቢ ተሸከርካሪዎችበኢሉባቦር መቱ አቋርጠው እየሄዱ መሆኑን ለፍኖተ ነፃነት ገልፀዋል፡፡