እስከመቼ ተጨቁነን!?? ሃሳባችንን የመግለጽ መብታችንን እናስከብር!!!

እስከመቼ ተጨቁነን!?? ሃሳባችንን የመግለጽ  መብታችንን እናስከብር!!!
‹‹ሐሳብን የመግለጽ ነጻነት ለሁሉም፣ አሁኑኑ!››
‹‹ሐሳብን የመግለጽ ነጻነት ለሁሉም፣ አሁኑኑ!››
‹‹ሐሳብን የመግለጽ ነጻነት ለሁሉም፣ አሁኑኑ!››
‹‹ሐሳብን የመግለጽ ነጻነት ለሁሉም፣ አሁኑኑ!›› የሚለውን ዘመቻ የምደግፈው የዚህኛው ወይም የዚያኛው ርዕዮተዓለም ደጋፊ ስለሆንኩ አይደለም፡፡ በዚህ ዘመቻ ላይ የሐሳብ ነጻነት (Freedom of Expression) ደጋፊ ነኝ፡፡ ሐሳብን የመግለጽ ነጻነት ተፈጥሮ የሰጠን ነጻነት ነው፡፡ ሰው ሁሉ ሐሳብ አለው፤ ሐሳብ ያለው ሁሉ የመናገር ተፈጥሯዊ ተሰጥኦ አለው፤ በሕገ-መንግሥቱ እስከተፈቀደልኝ ድረስ ይህንን ተፈጥሯዊ ስጦታዬን መጠቀሜ እና የሌሎችን ማክበሬ ለማንም ወገንተኛ ብሆንም ባልሆንም የማምንለት እና የምከራከርለት ነው፡፡ ይህንን ነጻነቴን ስጠቀም እና ሳደርግ በእራሴ ማሰብ እና ማድረግ የማልችል ይመስል ‹‹ከጀርባው ማን አለ?›› መባል ሰልችቶኛል፡፡ አገሬን እወዳለሁ፤ የገዛ አገሬን እና ሕዝቤን የሚጎዳ ሐሳብ እና ድርጊት ማፍለቅ አልፈልግም፤ ታዲያ ለምን ሐሳቤ እና ሐሳቤን የመግለጽ ነጻነቴ ይገደባል? የኔ ሐሳብ ከንቱ መሆን አለመሆኑን ገምግሞ የማጽደቅ ችሎታ ያለውስ ማነው? የኢትዮጵያ ሕዝብስ ሰምቶ ሲያበቃ ክፉ እና ደጉን መለየት አይችልምን? ‹‹ሐሳብን የመግለጽ ነጻነት ለሁሉም፣ አሁኑኑ!››
እያንዳንዳችን በየትኛውም አለም ያለን ኢትዮጵያውያን ሃገር ቤት ያለውን ጨምሮ የማህበራዊ ንቃተ ህሊናችን ከማንኛውም አለም የተሻለ መሆኑ ማንም የሚመሰክረው ነው :: ሆኖም ልንጠቀምበት አለመቻላችን ራሳችንን ለግዞት እንድንዳርግ መንገድ ለአምባገነኖች አመቻችተናል::ያለንን እምቅ ሃሳብ ሳንገልጠው ይዘነው መሞት መሰደድ እንደሌለብን የማወቅ ግደታ አለብን :: ስለዚህ እያንዳንዳችን የሃገራችን ጉዳይ ይመለከተናል:: ስለዚህ እያንዳንዳችን ሃሳባችንን በነጻነት እንገልጽ ዘንዳ ወዳፈኑን ሰዎች መጮህ አለብን:: እስከመች ተጨቁነን!!??

ዘመኑ በቴክኖሎጂ በገሰገሰበት እና በሰለጠነበት ግዜ እኛ ግን ተኮራምተን የምንፈልገውን ነገር እንዳናገኝ በጥቂት አምባገነኖች ተቆልፎብን እንገኛለን ::  ከዚህ ጭቆና ነጻ ለመውጣት መጮህ ብቻ ሳይሆን ከድምጽም አልፎ በአምባገነኖች ላይ አስፈላጊውን ግፊት ማድረግ አለብን:: እኛ እስከመቼ በተጭበረበረ ፖለቲካ በተገነባ ኢኮኖሚ መጨቆናችን ሳያንስ እርስ በእርስ እንክኡዋን ሃሳባችንን እንዳንካፈል እንዳናነብ እንዳንጦምር እየተደረግን ነው:: ወገን ታዲያ ምን እንጠብቃለን??

በኑሮ የተጎዳሀው ሳያንስህ መረጃ ማግኘት የተገፈፍከው ህዝብ ሆይ!!!

በህግ የማይከለከሉ ሰብኣዊ መብቶችህ ተግደው እና ተሸራርፈው በተራ ወንበር ላይ ሲወሰንባቸው ፍትህ የማግኘት መብትህ ሲገሰስ ማድረግ የምትፈልገው ህጋዊ ሁነቶን እንዳታደርግ እንዳታይ የዲሞክራሲ እስቲንፋስ በቀጭኑ እንዳትተነፍስ ተደርገሃል:: ማንንም የማትጎዳ ህዝብ መሆንህ እየታወቀ ሃሳብህ ተገድቦ ባላዋጣሀው ህግ እየተገዛህ ትገኛለህ :: አንተና ልጆችህ እስከመች ተጭበርብራቹህ ትኖራላችሁ???

ህገ መንግስቱ አጎናጽፎሃል የተባለውን መብት እውን ተጠቅመህበታልን?? ሃይማኖትህን በነጻነት እየመራህ ነውን? በነጻነት እየኖርክ ነው?? ከዚህ ጋር ተያያዥነት ያላቸውንጥያቄዎች ራስህን ጠይቀው:: በአሁኑ ሰአት ካለገደብ በነጻነት ሃሳብህን መግለጥ ትችላለህ?? የህን ብታድርግ ግን ከ አሸባሪዎች ጋር ተባባሪ...ወንጀለኞን ያዘለ...ጸረ ህዝብ...ወዘት ታፔላ ተለጥፎልህ ወደ ወያኔያዊ ካንጋሮ ፍርድ ቤት ትሄዳለህ ወደ እስር ቤትም ትወረወራልህ :: ስለዚህ ማንነትህን ሳታስነካ ኢትዮጵያዊ ኩራትህን እንደለበስክ ላንተ እና ለመጪው ትውልድ መስዋእት መሆን ይጠበቅብሃል እኔም እንዳተው:: አውቄ ማሳወቕ ታግየ ማታገል እስከመሰዋትነት ይጠበቅብኛል::

ስለሃገርህ መቼ እና እንዴት በይፋ ማውራት እንዳለብህ ሊነግሩህ የሚፈልጉትን ሰዎች ማስወገድ የሁላችንም ድርሻ ነው :: አንተ ነህ የመረጥከኝ እስካሉ ድረስ ሃስባችንን በገህድ የተሰማንን በይፋ ልንናገር ሌላውም ጋር የለውን መረጃ ልንቀበል ግድ ይለናል ..ይህ ግን ለኔ እና ላንተ ላንቺ አልተፈቀደም ስለዚህ ድምጻችንን ማሰማት አለብን  እንዲ ብለን......
‹‹ሐሳብን የመግለጽ ነጻነት ለሁሉም፣ አሁኑኑ!››
‹‹ሐሳብን የመግለጽ ነጻነት ለሁሉም፣ አሁኑኑ!››
‹‹ሐሳብን የመግለጽ ነጻነት ለሁሉም፣ አሁኑኑ!››
‹‹ሐሳብን የመግለጽ ነጻነት ለሁሉም፣ አሁኑኑ!››
አሁኑኑ አሁኑኑ አሁኑኑ አሁኑኑ አሁኑኑ
አንተ እና እኔ አንቺ እና እናንተ በዉነት ሃሳባችን ገደል ነውን ? የሰፊው ህዝብ ማንነት እየተደፈጠጠ ባለበት በዚህ ወቅት ሃሳባችንን እንድጥ ማሰማት አለብን  ሁላችንም በ‹‹ሐሳብን የመግለጽ ነጻነት ለሁሉም፣ አሁኑኑ!›› በሚለው ዘመቻ የምንሳተፍ ሰዎች መረጃው ላልደረሳቸው የማድረስ ግዴታ አለብን:: በሃገር ቤት ያለ ኢትዮጵያዊ ሁሉ መረጃ ይፈልጋል የተማረውም ያልተማረውም ህብረተሰብ ንቃተ ህሊናው ሰፊ በመሆኑ እያንዳንዱን ነገር ማወቅ ይፈልጋል :: ለዚህ ዘመቻ ስኬት ደሞ ጠንክረን መስራት እና ያምባገነኖችን ጆሮ መስበር አለብን::

ለመጨረሻ ይህንን አባባል ደጋግመን እናንብበው ...ላላነበቡም እናንብብላቸው...
የመንግሥትን አመለካከት ለማንፀባረቅ ፓርላማ፣ የመንግሥት ብዙኃን መገናኛ እና ብዙ መንገዶች አሉ፤ የእኔን ሐሳብ ግን የማቀርብበት መንገድ የለኝም፡፡ የፕሬስ ነጻነት ይከበር፣ የኢንተርኔት ገደብ ይቁም፣ ዙሪያ ገባውን በፍርሐትና በጥርጣሬ ሳልመለከት ሐሳቤን የመግለጽ ነጻነቴ ይከበርልኝ፡፡ ይህ የሚሆነው የታገዱ የሕትመት ውጤቶች እና የኢንተርኔት ብዙኃን መገናኛዎች ሲለቀቁ፣ ሐሳባቸውን በመግለጻቸው የተፈረደባቸው የኅሊና እስረኞች ሲፈቱ፣ የተሰደዱ ጋዜጠኞች ወደአገር ቤት ሲመለሱ ነው፡፡ ኢትዮጵያ የሁላችንም ነች፤ እኔም ለአገሬ የማዋጣው ሐሳብ አለኝ፤ እንድናገረው ይፈቀድልኝ፡፡

ድል ሃሳባችንን በነጻነት መግለጥ እና መረጃ ለማወቅ ለምንሻ ሕዝቦች!!!