የጀርመን ድምጽ ጸረ-ማህበራዊ መገኛኛ (ፌስ ቡክ ) ተጠቃሚዎች ዘመቻ

“የመናገር እና የመፃፍ ነፃነት መቼም ቢሆን ጥያቄ ውስጥ መግባት የማይገባው ተፈጥሯዊ መብት መሆኑ በተናገረበት አንደበቱ ” ሰሞኑንን ሰለፌስ ቡክ አጠቃቀም ሥረዓት ሊያስደምጠን የሞከረውን የ ጩሀት ግለሰብ ማንተጋፍቶ ስለሺ!
 ኢትዮጵያውያን ፌስ ቡክ ተጠቃሚዎች ላይ ያነጣጠር የዶይቼ ቬሌ DW ጩኸት !
የጀርመን ድምጽ  ጸረ-አትዮጵያውያን ዘመቻ
የዶይች ቬለ የጀርመን ድምጽ የአማርኛ ክ/ጊዜ እንደ ፌስ ቡክ ባሉ የማህበራዊ መገናኛ አውታሮች ላይ የማኅበራዊ አውታሮች አጠቃቀም ስነምግባር እስከምን ድረስ መሆን አለበት? በሚል ሰሞኑንን ባዘጋጀው ዘገባ ውስጥ የአያሌ ፌስቡክ ተጠቃሚ ወገኖቻችንን ሞራል ደፍጥቶ ያለፈ ነበር ቢባል ህቅን መስረት ያደረገ እውነታ አንጂ ትችት እንዳልሆነ ወዳጆቻችን በቅድሚያ ሊያጤኑት ይገባል።
ፌስ ቡክን እና መሰል የማህበራዊ መገናኛ አውታሮች አላስፈላጊ ለሆነ ርካሽ ተግባር የሚጠቀሙ ጥቂት ደካማ የህብረተሰቡ ክፍሎች የመኖራቸውን ያህል ዛሬ ይህ የብዙሃን መገናኛ አውታር የአያሌ ሃገራት ነጻነት አልባ ህዝቦች ብቸኛ የትግል ሜዳ እየሆነ የመምጣቱ ሃቅ ህዝቦች በገዥዎቻቸው የሚፈጸምባቸውን ግፍ እና በደል ከልካይ እና ገዳይ በለሌለበት የብሷት መድረክ የሆዳቸውን የሚገልጹበት የነጻት አደባባይ ለመሆኑ አብነት መጥቀስ አያሻም ።
በአጭሩ በዚም አ አለ በዚያ ይህ መድረክ ደስታ እና ሃዘን የሚገለጽበት ድህረ ገጽ ከመሆኑም በላይ በጭቆና ቀምበር የሚሰቃዩ ህዝባች የብሶት አደባባይ የመሆኑ ሚስጥር ለአንባ ገነን መሪዎች እና ተላላኪዎቻቸው እራስ ምታት እየሆነ መምጣቱ አይካድም። የፌስ ቡክ እና መሰል የማህበራዊ መገኛዎች ጥቀሜታ በህዝብ ዘንድ ተፈላጊነቱ ከእለት እለት እየጨመረ በመጣባቸው ባለፉት ጥቂት አመታቶች ውስጥ የአረቡ አለም ህዝቦች በስልጣን የባለጉ አንባገነን መሪዎቻቸውን ሃጥያት ያለምንም ፍረሃት እና ስጋት አደባባይ በመግለጽ አንድነታቸውን ጠበቀው ያለመሪ ለአመታት የታመቀ የብሶት ድምጻቸውን የሚያሰሙበት ብቸኛ የትግል መሳሪያ ለመሆን በቅቷል።
ለዚህም ሊፈነዳ በጣት የሚቆጠሩ ቀናቶች እንደ ቀሩ እሳተ ጎመራ እየተንተከተከ የሚገኘውን የሃገራችንን ህዝባዊ እንቅስቃሴ ጨምሮ በስሜን አፍሪካ እና መካከለኛ ምስራቅ የአምንባ ገነን መሪዎችን መደር እየናጠ የሚገኘው የነጻነት ጥያቄ፡ አብዮት መሰረቱ ፌስቡክ ለመሆኑ አይካድም። በዚህም ማህበራዊ መገናኛ ወጤታማ የሆኑ ህዝቦች ጨቆኝ የሚባሉ መሪዎቻቸውን ከስልጣን ከማስወገድ አልፈው በህግ አግባብ የእጃቸውን እንዲያገኙ ፍ/ቤት ገትረው እስከ መሞገት የሚያበቃቸውን መብት አጎናጽፎቸዋል ። በአጠቃላይ በዚህ ዙሪያ አንድ ታላቅ ኢትዮጵያዊ ለመጥቀስ እንደ ሞከረው ዛሬ “ ለብዙ ወገኖቻችን ይህ ማህበራዊ መገናኛ የጦር ሜዳ አውድማ በመሆን የተጨቆነው ሁሉ በአንድ ጎራ ሆኖ በሃሳብ እና በእውነት ፍላጻ ጨቋኞችንና ጋሻ ጃግሬዎቻቸውን የሚዋጋበት መድረክ ነው።
ከዚህ አንጻር ይህ የህዝብ መገኛ አውታር በግንባር ቀደም ግፍ እና በደል ለሚፈጸምበት ህዝብ ጥሩ አንደምንታ እንዳለው በፌስ ቡክ ዙሪያ ቅን አመለካከት ያላቸውን ሁሉ እንደ ማያከራከር ግልስ ነው።ይህ በዚህ እንዳለ በዚህ ዙሪያ የዶይቼ ቬሌ የአማርኛው ድምጽ ሰሞኑንን ሰለፌስ ቡክ አጠቃቀም ሥረዓት ሊያስደምጠን የሞከረውን ጩሀት ! ለመዳሰስ አቶ ማንተጋፍቶ ስለሺ ለዝግጀቱ መሳካት ግባት ያደረጋቸውን የሃሳብ ተጋሪዎቹን ተቀብሎ ከማስተናገዱ በፊት “የመናገር እና የመፃፍ ነፃነት መቼም ቢሆን ጥያቄ ውስጥ መግባት የማይገባው ተፈጥሯዊ መብት መሆኑ በተናገረበት አንደበቱ ” በፌስ ቡክ ተጠቃሚዎች ላይ ጣቱን በመቀሰር ዘግናኝ፡የሆነ ጩሃቱን ከጀርመን ቦን ሊያሰደምጠን የሞከረበትን ዝግጅቱን መነሻ ማድረግ ግድ ይላል ።
ዶይቼ ቬሌ ራዲዮ የማኅበራዊ አውታሮች አጠቃቀም ስነም ግባር እስከ ምን በሚል ረዕስ ከወጣቶች አለም ፕሮግራሙ ላይ የፌስቡክን ጠቀሜታ በአንድ አቅጣጫ ብቻ ለማየት የሞከረበት “እይናችሁን ጨፍኑ “ አይነት ግንዛቤ ማስጨበጫ ድራማው ላይ የፌስ ቡክ ተጠቃሚውን ወገን በጅምላ በስረአት አልበኝነት ይፈርጃል። በድፍረት ማህበራዊ የመገናኛ አውታሮች ስነምግባር ላይ ያተኮረ ጥንቃቄ ማድረግ እንደ ሚገባን አጽኖት ሰቶ ለመምከር የሚሞክረው ዶይቼ ቬሌ በኑሮ ውድነት ለነፈረው ህዝባችን ዘመናዊው አለም የፈጠረለትን ሃሳብን በነጻ የመግለጽ ዴምክራሲያዊ መብት ሊነጥቁት በቢሊዮን የሚቆጠር ባጀት በጅተው በዚህ ማህበራዊ መገናኛ አውታር ላይ የስለላ መረባቸውን ከመዘርጋት አልፈው ለማህበራዊ መገናኛ ጠቀሜታ አላቸው ተበልው የሚገመቱትን እንደ ላፕቶብ (ኮፒተር )እና ተንቀሳቀሽ የስልክ ቀፎችን ለመዝረፍ ጭምብል አጥልቀው በድቅድቅ ጨለማ አጥር ለአጥር እየዘለሉ ተራ የሌብነት ተግባር እየፈጸሙ የሚገኙትን የታጠቁ የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ጀሌዎች ውሎ ዶይቼ ቬሌ መስማትም ሆነ ማየት አለመፈለጉ ነው ክፋቱ።
በአንድ እራስ ሁለት ምላስ እንዲሉ ዶይቼ ቬሌ ለፕሮግራሙ ስኬት በዚህ ዙሪያ አጊኝቶ ካነጋገራቸው ወጣቶች መሀከል ስሙ እንዳይጠቀስበት አደራ ያለው የስረአቱ ካድሬ በነዚህ አምዶች ላይ እያደረገ ያለው ተሳትፎ በስሙ እንዳልሆነ በማስገንዝብ በነዚህ ማህበራዊ መገናኛ አውታሮች ላይ አንድ ሰው ስሙን ስይለውጥ ሃስቡን በአደባባይ መጀመሪያ መግለጽ እንዳለበት ያስቀመጠውን ምክር የሚጋራው የፕሮግራሙ አዘጋጅ አቶ ማንተጋፍቶት ስለሺ ይህን አስመልክቶ ዝግጀት ለማሰናዳት ለፕሮግራሙ ግበአት የሚሆኑ አስተያየት የጠየቃቸው የፌስ ቡክ ተጠቃሚ ወጣቶች በተለያየ ምክንያት ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ማዘኑንን በመግለጽ ወጣቶቹን በማህበራዊ ገጾች ላይ ንቁ ተሳታፊ መሆናቸው ነገሩን የበለጠ አስገራሚ እንደሚያደርገው በመወቀስ ወጣቶቹ የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ስረአት ሰለባ ሊሆኑለት አለመቻላቸውን በግልጽ ይቃወማል።
በነዚህ ማህበራዊ መገናኛ አውታሮች ስምና አድራሻን ለጥፎ ለኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ስረአት የስለላ መረብ ሰለባ ላለመሆን በዚህ ማህበራዊ መገናኛ አውታር ስማቸውን እና አድራሻቸውን ሳይገልጹ በፌስ ቡክ ብቻ መረጃ በመለዋወጥ ላለፉት 14 ወራት ድምጻችን ይሰማ በሚል መሪቃል ስረአት ጠብቀው ብሶታቸውን በመግለጽ ላይ የሚገኙ ወገኖቻችንን ጥራዝ ነጠቅ ግለሰባዊ ትችቶችን ከሚለቁ እና ጸያፍ ሰዕላዊ መግለጫዎችን ከሚለጥፉ ወገኖች ጋር ለማነጻጸር ይቃጣዋል።
ዛሬ ዛሬ ሚናቸው ያለየው ዶይቼዎች ባል እና ሚስት ከአንድ ወንዝ እንዲሉ ስሞኑንን ኢቲቪ የፌስ ቡክ ተሳታፌዎችን አስመልክቶ በአንድ ወቅት ምሽት በዜና ሽፋኑ የማህበራዊ መገናኛ ተሳታፊዎችን ከአይምሮ አደንዛዥ እጽ ተጠቃሚዎች ጋር ለማመሳሰል የሞከረበትን ዘለፋን በማስተጋባት ማንነታችንን እዝህገጽ ላይ ለጥፈን በመንቀሳቀስ ለስነምግባር ተግዢ መሆን እንደሚገባን ዶይቼዎች በአሮቆ አስተዋይነታቸው ሊመክሩን ይቃጣቸዋል።
በስተመጨረሻ አቶ ማንተጋፍቶት የአሰተሳሰብ ልዩነቶችን ኢዞ መጓዝ ለእደገት ወሳኝ መሆኑንን የሚጠቅሰውን ሌላ ተጋባዥ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የስነ-ጥበባት ኮሌጅ የቴአትር ክፍል ውስጥ ኮሚኒኬሽን መምህር የሆነውን ወጣት እንግዳ ተብዬ ለአብነት በመጋበዝ የአስተሳሰብ ልዩነቶችን አስመልክቶ ሊያስደምጠን የሞከረበት አጋጣሚ ዛሬ እነ እስክድር ነጋን የመሳሰሉ አያሌ አንጋፋ ጋዜጠኞች ለወህኒ ተዳርገው ባሉበት የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ግፍ አገዛዝ እንዴት ተደርጎ እራስን በማህበራዊ መገኛኛ ገጾች ላይ አሳልፎ በመስጠት ሃስብን በነጻ ማሸራ ሸር እንደሚቻል ባናውቅም ? ዶይቼ ቬሌዎች ግን አማራጭ የሌለው የስነምግባር መለኪያ መሆኑንን ሊጠቁሙን ይሞክራሉ።
መቸም ዶይች ቬሌ የረጅም አመታት የኢትዮጵያ ህዝብ ወዳጅ መሆኑ ባይዘነጋም አሁን አሁን ግን አፉ ከኛ አይነት የአየር ላይ ጫወታው በብዙ ወገኖቻችን ዘንድ የነበረው ፍቅር እና እምነት ተሸርሽሮ እንደ በርሊኑ ግብ ተንዶ በህዝብ ሊተፋ በጣት የሚቆጠሩ ቀናቶች እንደቀሩት የሚናገሩ የዝግጅቱ ወዳጆች ከሬዲዮ ጣቢያው ጀርባ ሆነው የዝግጀት ክፍሉን በተሳሳተ አቅጣጫ የሚነዱት መሰሪዎች ከወዲሁ ሃይ ሊባሉ እንደሚገባቸው በአጽኖት ይገልጻሉ። ይቀጥላል
በሳውዲ አረቢያ የሪያድ እና አካባቢው ኢትዮጵያውያን ወጣቶች ማህበር
http://www.dw.de/popups/mediaplayer/contentId_16620210_mediaId_16620204