ጀርመን ራዲዮ እና የወያኔ ሴራ በፈስ ቡክ ኢትዮጵያውያን ላይ

ጀርመን ራዲዮ እና የወያኔ ሴራ በፈስ ቡክ ኢትዮጵያውያን ላይ


በሃገራችን ታሪክ ታይቶ እና ተከስቶ የማያውቅ የሽፍቶች አሸባሪ መንግስት በተለያየ ስልት ኢትዮጵያውያንን መከራቸውን እያሳየ ይገኛል:: ይህ ወንበዴ መንግስት ማፊያዊ ስልቶችን በመጠቀም የተለያዩ ሽብሮችን እየፈጸመ ነው:; መውደቂያው የደረሰው እና በቋፍ ላይ ያለው ይህ መንግስት ስለ ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያውያን የሚያስቡ ሰዎችን የሚዋጋበት ስልቱ የህዝብ ንብረት እና ገንዘብ በመጠቀም ስልጣኑን ላለማጣት እየተራወጠ ይገኛል::ይህንንም ለመዋጋት ድፍን ኢትዮጵያዊ ዘር ሃይማኖት ቀለም ወ.ዘ.ተ. ሳይለይ በአሁን ሰአት በጋር ድምጻችን ይሰማ እያለ ለመብቱ እና ለነጻነቱ እየታገለ ነው:: ይህንን ትግል ለማኮላሸት ሴራ ከሸረቡት አንዱ ከዚህ አሸባሪ መንግስት ጋር በማበር እየሰራ የሚገኘው የጀርመን ድምጽ አንዱ ነው ::

ይህ የራዲዮ ጣቢያ ከቀድሞው ጀምሮ ከወያኔ ጋር በመመሳጠር በኢትዮጵያ እና በዜጎችዋ ላይ የምእራባውያኑን ጥቅም ሲያራምድ ቆይቷል:: ምእራብያውያኑ በተለይ ጀርመን አጋርዋ የሆነው አሸባሪ የማፊያ ቡድን እንዳይቐየማት እና አስልፎ የሚሸጥላት የኢትዮጵያውያንን ጥቅም በማግበስበስ ለብሄራዊ ጥቅሟ ስትል የሃገሪቱ ህዝቦች ድምጽ እንዳይሰማ የህን የራዲዮ ጣቢያ እየተጠቀመች ነው::

ከዚህ በዘለለ በኢትዮጵያ አንጡረ ሃብት የተማሩ ያደጉ የት እንደደረሱ እንኩዋን ራሳቸውን የላዩ የራዲዮው ጋዜጠኞች የእናት ጡት ነካሾች ኢትዮጵያዊ የሚል ዜግነታቸውን አስረክበው ጀርመን የሚል ዜግነትን በመጎናጸፍ/ለነሱ ይመስላቸዋል/ በኢትዮጵያ እና በኢትዮጵያውያን ላይ እጅ አዙር ወያኔያዊ ዘመቻ ከፍተዋል::

ይህንን ዘመቻቸውን የከፈቱት በሃገራቸው መኖር መናገር መስራት በተከለከሉ ዜጎች ላይ ነው:: ይህ ደሞ እጅግ አስቀያሚ ምግባር እና ወያኔያዊ ሃራካት መሆኑን እንገነዘባለን::ወያኔ በምትሰጣቸው ጉርሻ የሚፎልሉብን እነማሙሽ ስብሃቱ ዛሬም ወሬያቸውን ይዘው እንደውሻ መጮህ ጀምረዋል::
በዚህም መሰረት አድርገው የወያኔ ተሊኮዋቸን በማማሰል ፌስቡክ በአሸባሪ እና በወንጀለኛ የተሞላ ነው እያሉን ነው ይህን እኛ ኢትዮጵያውያን በነዚህ ሰዎች ላይ ዘመቻ እንድናደርግ አስገድዶናል:: እንደዚህ አይነት ጩኸታቸውን የጀመሩት ወያኔ ከተዋረደበት የሳኡዲ አረቢያ የቦንድ ስብሰባ ጊዝይ በሁዋላ ነው ::ከዛ ቀደም ብሎ የሚሰሩትም ስራ ለማንም ኢትዮጵያዊ አይጥመውም የቦንድ ሽያጭ ስብሰባ  የኢትዮጵያውያን ተቃውሞ በራዲዮናቸው ላለመናገር ሲዘባበቱ ነር ይባስ ብለው ወኪላቻው በዛ ምሽት ከወያኔ ዲፕሎማቶች ጋር ሲያሽካካ እንደነበር በሳኡዲ የሚገኘው የወጣቶች ማህበር ጠቁሟል:; ዛረ ይህንኑ የተመሸጉበት የወያኔ ምሽግ ለምን ተደፈረ ሊናድ ነውን ባማለት ፌስቡክ ላይ ያሉት ኢትዮጵያውያን ኢላማ አድርገው ተነስተዋል::

በፈስ ቡክ ያሉ እትዮጵያውያንን ለመታገል እነዚህ የወያኔ ጀሌዎች እኛ ታዋቂ ነን የእከሌ ወንድም ነን እኛ ኦዲየንስ አለን በሚሉ...አነጋገሮች በመኮፈስ የተለያዩ መላምቶችን በመሰንዘር እየተራወጡ ሲገኙ የተለያዩ የፈስቡክ አካውንቶችን ለማዘጋት ሪፖርት እያደርጉ ነው ለዚህም የሚጠቀሙበት  አሸባሪ እና ወንጀለኛ የሚል የወያኔ ቋንቋ ነው::አሸባሪነትን ለመከላከል እየሰራን ነው የሚል ፕሮፖዛል ለነጭ አለቆቻቸው እስከማቅረብ ደርሰዋል::

እለት እለት እየተጠናከረ በመጣው አፈና ምክንያት ፌስቡክን እንደመተንፈሻ እና መንግስትን ለመታገል እንደዋነኛ መደራጃ እያገለገለ እንደሚገኝ ግልፅ ነው ታዲያ ሁሉንም ነገር ካላፈኑ እንቅልፍ የማይወስዳቸው ወያኔዎች የፌስቡክ ነገር ከቁጥጥራቸው እንደወጣ ስለተገነዘቡ ፌስቡክ የሚፈጠሩ ግሩፖቹን፥ገፆችንና የግለሰብ ፕሮፋየሎችን እየተከታተሉ ከመዝጋት ባሻገር ፀረ-ፌስቡክ የሆነ ዘመቻ ከጀመሩ ውለው አድረዋል እስከአሁን ፀረ-ፌስቡክ የሆኑ
የፕሮፓጋንዳ ስራዎች በኢቲቪ፥ በሪፓርተር እና በዛሚ ኤ.ኤፍ.ኤም ጀርመን ራዲዮ ቀርበዋል።ከሆድ አሳዳሪዎቹ ጋር እንዘጭ እንዘጭ ያበዛው የጀርመን ራዲዮው ማንተጋፍቶት ስለሺ (ማሙሽ ስብሃቱ) በወያኔ እየተካሄደ ያለው ፀረ-ፌስቡክ ዘመቻ እራሱን አካል ስለአደረገ ይመስለኛል ከመስመር በወጣ መልኩ ፌስቡክና ፌስቡካውያንን በአንድ ከረጢት አጭቆ የዘለፈው።