ይድረስ ለኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች-- ያልተሞከሩ ሶስት የሰላማዊ መንገድ ስትራቴጂዎች

ያልተሞከሩ ሶስት የሰላማዊ መንገድ ስትራቴጂዎች

ስትራቴጂ አንድ፦

በኢትዮጵያ ኢምባሲዎች የየሃገራቱን ዜጋ ያሳተፈ ከባድ ተቃውሞዎችን ማድረግ፦ በተለይ ለኢትዮጵያ ሙስሊሞች ልዩ ስሜት ባላቸው በሱዳን ቢጀመር ውጤት ያመጣል። መጀመሪያ ኢትዮጵያውያን ተሰባስበው በሱዳን የኢትዮጵያ ኢንባሲ ሰልፍ ያደርጋሉ፤ በሰልፉም ዋናውን ጭብጥ ካስረዱ በሁዋላ ጉዳዩ ለኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ካቅም በላይ መሆኑን እና የሱዳኖች ሚና ከታሪክ ጋር በማዛመድ ለቀጣይ እነሱንም ያሳተፈ ከባድ ሰልፍ መጥራት።
አንዴ ሱዳን ችቦው ከተለኮሰ በሁዋላ በቅብብሎሽ መላው አለምን ማዳረስ። እዚህ ላይ በየሃገሩ የሚኖሩ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ከባድ ሃላፊነት ይጠብቃቸዋል።

ስትራቴጂ ሁለት፦

በዩኒቨርስቲዎች ከምግብ አስከ ትምህርት ማቆም አድማ መምታት፦ በዚህ ስትራቴጂ አስካሁን በትግሉ የነቃ ተሳትፎ የሌላቸውን ቁልፍ እና አስፈሪ ክልል ህዝቦች ያንቀሳቅሳል ተብሎ ይታሰባል። በተለይ የጂጂጋ, ሰመራ, ድሬዳዋ, እና መደወላቡ ዩኒቸቨርሲቲ ተማሪዎች ጥያቄው የሙስሊም ተማሪዎች ብቻ ሳይሆን የመላ ሙስሊም ህብረተሰብን የማጥፋት ሴራ መሆኑን በማስረዳት የአካባቢው ህዝብ መሃል ገብተው ትግሉን ማቀጣጠል ይገባቸዋል። ጥያቄው ወደ ህዝቡ ገብቶ ከተንቀሳቀሰ ለቀጣይ ስትራቴጂ ለመንደፍ ጠቃሚ የሰው ሃይል፣ ስትራቴጂካዊ ገዢ መሬት እና የነቃ ተሳትፎ ማትረፍ ይቻላል።

ስትራቴጂ ሶስት፦

ኢኮኖሚያዊ እቀባ፦ ኢኮኖሚያዊ እቀባ ሲባል የግብርና ምርቶችን፣ የሸቀጥ ምርቶችን፣ ወደ ሃገር ውስጥ የሚገቡ ገንዘቦችን፣ የንግድ መተላለፊያ ኬላዎችን፣ መገበያያ ገንዘቦችን ወዘተ በመያዝ፣ በመሰወር፣ በማስተግዋጋል ሊሆን ይችላል። ከኢኮኖሚያዊ እቀባዎች ይበልጥ ውጤታማ ሊያደርጉን የሚችሉና ግልፅ የሆኑትን በመምረጥ አሚሮቻችን ሊያታግሉን ይችላሉ።