የሕግ የበላይነት ወይስ የመሃይሞችና የሕግ የበላይነት

ፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም
የገዢው ፓርቲ ሰዎች በተደጋጋሚና አፋቸው በተከፈተ ቁጥር ምን ያህል ሕገመንግስቱን እንደሚያከብሩትና ለሕግጋቱም የቱን ያህል ታማኞችና ተገዢዎች እንደሆኑ ይቦተልካሉ፡፡ ባለፈው ሴፕቴምበር የፕሮፐጋንዳው ሂትለራዊው ሚኒስቴር በረክት ስምኦን ስለ መለስ መታመምና መሞት በየቀኑ ታላቁን የወቅቱን ውሸት ሲዋሽ ሲዋሽ ደሞ ሲቀላምድ ደሞ ሲቀላምድ፤ ችግር የሌላ መሆኑንና በሕገመንግስቱ መሰረት መተካካቱ እንዳለ ነው የሚለውን ያልተቃኘ ቱልቱላውን ሲነዛ ከረመ፡፡ እንደ መገናኛ  ሚኒስትርነቱ ስምኦን የ‹‹ጂሃዳዊ ሃረካት››ን መተላለፍ ያዘዘው እሱ ነው፡፡ ማንንም ሰው የሚያስገርመው ግን እነዚህ ለሕገ መንግስቱ መከበርና ልዕልና ቆመናል በማለት በየጊዜው ከበሮ የሚደልቁት ማን አለብን ባይ ዲክታተሮች እነዚህን የፈጠራ ክሳቸው በፍርድ ቤት በመታየት ላይ ያሉትን ንጹሃን ዜጎች ከችሎቱ አስቀድሞ እንዲህ አይነቱን ፓርቲያዊ የስልጣን ማክረሚያ ፍርዳቸውን ማስተላለፋቸው መብት መጣሳቸው መሆኑን አንገታቸው ላይ የተሰካው ቅል አያስታውሳቸው ይሆን? ድርጊታቸው የሼክስፒርን አባባል አስታወሰኝ፡፡ ‹‹ዲያቢሎስም ለራሱ መጠቀሚያ መጽሃፍ ቅዱስን ይጠቅሳል›› ያለውን፡፡ እነዚህ ሰዎች ያላዋቂ ሳሚ ናቸው ወይስ የሰይጣን ቁራጮች? ላለፉት በርካታ ዓመታት በተደጋጋሚ እንዳልኩት በኢትዮጵያ ላለው አረመኔ መንግስት ስለ ሕግ የበላይነት ማውራት ለዲያቢሎስ መጽሃፍ ቅዱስን እንደማንሳት ነው፡፡ አይግባቡምና፡፡  ሕገመንግስቱ እግር አውጥቶ እየዳመጣቸው እንዲገባቸው ሊያደርግ ቢሞክር እንኳን ጨርሶ ድንጋያማ ሕሊናቸው ተፈረካክሶ ያልቃል እንጂ አይገባቸውም፡፡
በ‹‹ሽብርተኘነት የተጠረጠሩት›› ሙስሊሞች ጉዳይ እና ‹‹ጂሃዳዊ ሃረካት›› ላይ ቃላቸውን ሰጡ የተባሉት ጉዳይ ሊተኮርበት የሚገባው 3 ነጥብ አለ፡፡ 1) እነዚህ ተከሳሾ ቅድም ችሎት ታሳሪዎች ስለሆኑ በሕገመንግስቱ ላይ በተደነገገውና በሌሎችም ሃገሪቱ ከገባችባቸው ፍትሃዊ ዓለም አቀፍ ድንጋጌዎች አኳያ መብታቸው ሊከበርላቸው ግድ ነው፡፡ 2) እነዚህ ተጠርጣሪዎች ቃላቸውን በፈቃደኝነትና በነጻ አለመስጠታቸውን የሚያረጋግጠው በካቴና ቀርቦ የነበረው ተጠርጣሪ ሲሆን ሌሎችም ቢሆኑ አያያዛቸውና ያሉበት ሁኔታ ሕጋዊ ስርአትን የተከተለ አለመሆኑ ይታወቃል፡፡ 3) ሁሉም 29 ታሳሪዎች የፖለቲካ እስረኞች ናቸው፡፡ ሕገመንህስቱን ለማክበር በሱም ለመመራት ጨርሶ ፈቃድ የሌላቸው መሪዎች፤የጣሳሪዎቹን ሰብአዊ መብት ያከብራሉ ማለት የማይሞከር ነው፡፡የሃገሪቱ መሪዎች ባላቸውና በሚያሳዩት ተግባራቸው ምን ያህል ከእውቀትና ከሰለጠነው ፖለተካ ጋር እንደማይተዋወቁ ነው በማሳየት ላይ ያሉት፡፡ እነዚህ ገዢዎች ከመሰረቱ ጀምሮ ከተንኮልና ከግፍ በደል በስተቀር አንዳችም ተግባር አለመፈጸማቸውንና ማንኛቸውንም ጉዳይ ይተገብር የነበረው የሞተው አለቃቸው እንደሆነ ሳያፍሩ በመናገር የራሳቸውን ብቃት የለሽ መሆን አውጀዋል፡፡ ማንም ተከሳሽ በፍርድ ሂደት ወንጀለኛ እስካለተባለና እስካልተፈረደበት ጊዜ ድረስ ነጻና ንጹህ ነው፡፡ በምንም መልኩ በግዳጅ የተገኘ ቃል ለማስረጃነት ሊቀርብ አይችልም፤ ድርጊቱም ዓለማቀፋዊ ድንጋጌዎችን ያልተከተለ ነው፡፡ ሰብአዊ መብትን ይገረስሳል፤ የፍትህን የበላይነት ይቃረናል:: 4) በጣም የሚያሳዝነው ቀልድ ደግሞ ፍርድ ቤቱ በኢቲቪ እና በሬዲዮ ድርጅቶች ላይ ያን የተቀነባበረና ቆርጦ የተቀጠለ የማፍያ አካሄድ ጨርሶ እንዳይተላለፍ ያስተላለፈውን ትዕዛዝ፤ እነማን አለብን ‹‹እኛው የፈጠርነው ዳኛም ሆነ ችሎት ሊከለክለን አይችልም›› በማለት ትእዛዙን ጥሰው ሲያስተላልፉት፤ በፍርድ ቤቱ ትእዛዝ መሰረት ባለመፈጸሙና አግባብም ስላልሆነ የቀረቡትን ማስረጃ የተባሉትን ሁሉ አመኔታ ስለማንሰጣቸው ተቀባይነት አይኖራቸውም›› በማለት እንኳን ዋጋ ቢስ በማድረግ ፈንታ ችሎቱና በችሎቱ ወንበሮች ላይ የተጎለቱት እራሳቸው እርባና ቢስ ሆነዋል፡፡
ተስፋ የቆረጠ አምባገነንነት እና የዕጣቢ መውረጃ ቱቦ ፖለቲካ በዚህ ዶኩመንታሪ በኢትዮጵያ ያሉት ጨቋኝና ርህራሄ ቢስ ገዢዎች ከምንም በታች አዘቅዝቀው ወርደው ውረደታሞች መሆናቸውን ገሃድ ከማውጣታቸውም አልፎ የዝቃጭ መፈሰሻ  ቱቦ ፖለቲከኛነታቸውንም ይፋ አድርገዋል፡፡ አንድ ብቸኛ ሆኖ ሊታይና ሊረጋገጥ የሚችለው በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ሽብርተኛ እነሱ ገዢዎቹ ብቻ መሆናቸው ነው፡፡በ‹‹አኬልዳማ ገዢው መንግስት ሆነ››ባለው መሰረት በአሸባሪዎች 131 ጥቃት ተፈጽሟል፤339 ዜጎች ተገድለዋል፤363 ቆስለዋል፤25 ደግሚ ተጠልፈው ለሞት ተዳርገዋል:፡ ይሁንና በራሱ በመለስ ዜናዊ ይሁንታ የተቋቋመው አጣሪ ኮሚሽን እንዳጣራው  ምርጫ 2005ን ተከትሎ በጥቂት ቀናት ውስጥ በመለስ ዜናዊ አመራርና ትዕዛዝ መሰረት፤ 193 ሰላማዊ ዜጎች አንዳችም መሳርያ ያልነበራቸው 193 ሲገደሉ፤763ቱ ደግሞ ለከፍተኛ ቁስለት ተዳርገዋል፡፡ ኮሚሽኑ ባረጋገጠው መሰረት የስለላ ሰራተኞችና የመንግስት ጦር አባላት አተኳኮሳቸው ሰልፉን ለመበተን ሳይሆን ለመግደል በመሆኑ ሁሉም አናታቸውንና ደረታቸውን እየተመቱ ነው የሞቱት፡፡ በሴፕቴምበር 2011 ዓለም በሙሉ የኢትዮጵያ የደህንነት ሰዎች፤ በሴፕቴምበር 16 2006 በአዲስ አበባ ከተማ 3 ቦምቦች አጥምደው ካፈነዱ በኋላ ፍንዳታውን የፈጸሙት ኤርትራዊያንና የኦሮሞ ነጻ አውጪ ድርጅት አባላት ናቸው በማለት ሰበብ አድረጓቸዋል:: በዚህም ፍንዳታው የአፍሪካ ሕብረት መሪዎች ለስብሰባ በመጡበት ወቅት መከናወኑ የጉዳዩን ተአማኒነት አጣጥሎታል፡፡  አዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካን ኤምባሲ ጉዳዩን በራሱ ባለሙያዎች ካስመረመረውና ካጣራ በኋላ ጣቱ የጠቆመው ወደ ኢትዮጵያ መንግስት ሆኗል፡፡ ገዢዎቹ ስልጣን ወንበር ላይ ከተፈናጠጡ ጀምሮ የተካሄዱት ግድያዎች ቢቆጠሩ ከብዙ ሺሆች በላይ እንደሚሆኑ ጥርጥር የለውም፡፡ መንግስት ነኝ ባዩ በራሱ አፈንድቶ፤ አጥምዶ፤ ደብቆ፤ አግኝቶ ያፈነዳውን አድራጊዎቹ ሌሎች ናቸው ብሎ አመልካች ጣቱን ወደ ሌሎች ሰዎች ሲዘረጋ ሌሎቹ ሶስቱ ያቶች ወደ ራሱ ማመልታቸውን መገንዘብ አልቻለም፡፡
ጂሃዳዊ ሃረካት የኢትዮጵያን ሙስሊሞች ስም ለማጥፋት፤ለመኮነን፤ለማዋረድ፤ለመከፋፈል፤ ሆን ተብሎ የተፈበረከ ነው፡፡ ለዘመናት ጸንቶ በፍቅርና በመተሳሰብ የኖረውን የሁለቱን ሃይሞኖቶች ሂደት ለመበጥበጥ የተቀመመ መርዝ ነው፡፡ እዚህ ግባ የማይባል ፕሮፓጋንዳ ነው፡፡ በዚህም ሊፈጠር የተሞከረው በሙስሊሙና በእስልምና ሃይሞኖት ተከታዮች መሀላ መለያያት ለማስረጽ ነው፡፡ ከዚህም ሙስሊሙን ዳግም ወደ ፖለቲካና መብት ጥየቃ እንዳይነሳ፤ በፍርሃት ለማሰር፤ለመወንጀልና ለማሰር መንገድ ለመክፈት ከኤኮኖሚ፤ ህብረተሰባዊ ግንኙነት፤ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ለመለየት የታቀደ ማስደንበሪያ ነው፡፡‹‹ጂሃዳዊ ሃረካት እስልምናን የመፍራትና ደንብሮ የማስደንበር፤ ፈርቶ የመስፈራራት፤ ያለቀንና የበቃውን የገዢነት ስልጣን የማቆያ ዘይቤ ነው፡፡ አይሆንም አልሆነም ይልቅስ ሁሉንም ያስተባበረ የገዢዎች ግፍ ሆኗል!
በኢትዮጵያ ያሉ የፖለቲካ እስረኞች ሁሉ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ይፈቱ!