የደሴ ከተማ ፖሊስ ጽ/ቤት ሃላፊ ኮ/ር ደረጄ አና ግብርአበሮቹ በህገወጥ የመሳሪያ ዝውውር ተሰማርተዋል ::

ኮማንደር ደረጄ እና ግብር አበሮቹ ተጋለጡ
የደሴ ከተማ ፖሊስ ጽ/ቤት ሃላፊ ኮ/ር ደረጄ፣ የአስተዳደርና ጸጥታ ጽ/ቤት ሀላፊው አቶ ሙሉጌታ እንዲሁም
የሚኒሻ ጽ/ቤት ሀላፊው አቶ ናስር ከደህንነትና ልዩ ሀይል አመራሮች ጋር በመተባበር በህገ-ወጥ መሳሪያ ሽያጭ ላይ
እንደተሰማሩ ምንጮቻችን ገልጸዋል። 


ግለሰቦች የመንግስትአጀንዳ በሙስሊሙ ላይ መሆኑን እንደ ሽፋን በመጠቀምናእነርሱም ከዚሁ አጀንዳ ውጭ ምንም ስራ እንደሌላቸውበማስመሰል ከአፋር ክልል በኩል የሚመጡ ህገ-ወጥ የጦር መሳሪያዎችን ወደ ምእራብ ወሎ በማስተላለፍ ከፍተኛ ገንዘብእያጋበሱ እንደሆነ ታውቋል። 

ከዚህ ህገ-ወጥ ዝውውር ሽራፊ ሳንቲም የማያገኙት በእነዚህ መስሪያቤቶች ያሉ ተራሰራተኞችና የልዩ ሀይል አባላት እነዚህን ወሮበሎችለማጋለጥ ቀን እየጠበቁ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል። ይህተግባራቸው ከተለመደው የኮንትሮባንድ እቃዎችንከማዘዋወርና የኦፓል ማእድንን በህገ-ወጥ መንገድከማስተላለፍ በተጨማሪ የሚያከናውኑት “ንግድ” ነው። 
 
ከዚህበፊት እንደሚታወቀው ኮማንደሩና ግብርአበሮቹ በእስርላይ የሚገኙ ወንድሞቻችንን በመደብደብና የአካል ጉዳትእንዲደርስባቸው ያደረጉ ሲሆኑ ይህም አልበቃቸው ብሎ ያለፍትህ ለረዥም ጊዜያት እንዲታሰሩ [ለ 6 ወር ያክል ያለ ክስ ፍርድ ቤቱንና የፍትህ ስርዓቱን በቀጥታ በቁጥጥራቸው ስርያዋሉ ግለሰቦች መሆናቸው ይታወቃል።
 በየመስጂዶቹየሚካሄዱትን ተቃውሞዎች በአሳዛኝና ኢሰብዓዊ መንገድ የሚጨፈጭፉ አንባገነኖች ናቸው። ሰሞኑንም ብዙወንድሞቻችንን እየደበደቡ አስፋልት ላይ እንዲጣሉከፍተኛውን ድርሻ የወሰዱ ናቸው።እነዚህ ግለሰቦች ስርዓቱ ዴሞክራሲያዊ ቢሆን በሰሩትወንጀል አንድ ቀን እንደማያድሩ ስለሚያውቁት ይህንኑአንባገነንነት እንዲቀጥል እየታገሉ ይገኛሉ።
 ፈጣሪ የጠላቶቻችንን ገመና የአደባባይ ያድርገው። ለእኛየፈተሉት የሴራ ገመድ ለራሳቸው ማሰሪያ ያድርግላቸው።
አሜ ን!!!