የኢቲቪ ዘጋቢ ፊልም እንዲታገድ ፍርድ ቤቱ የሰተው ትእዛዝ ጠፍቷል መባሉ ውዝግብ አስነስቷል፡፡

የተከሳሽ የሙስሊሙ ህብረተሰብ ችግሮች መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎችን ክስ የሚያየው ችሎት እንደወትሮው በጠዋት ተሰይሞ ምስክሮችን መስማት ለመጀመር በዳኞቹ ንግግር ሲጀመር ሁሉም ተከሳሾች ከመቀመጫቸው በመነሳት ኢቲቪ ያስተላለፈው ዘጋቢ ፊልም ላይ እና የፍርድ ቤቱ ትእዛዝ ሆንተብሎ እንዲደናቀፍ መደረጉ ላይ ያላቸውን ተቃውሞ አሰምተዋል፡፡
ፍርድ ቤቱ የተከሳሽ ኮሚቴዎቹ ሰብሳቢ የሆነው ኡስታዝ አቡበከር አህመድ ንግግር ሲያደርግ ቆይ ቆይ በማለት ሊያስቆመው ሲሞክር ንግግሩን ዝምብሎ ቀጥሏል፡፡ ፍርድ ቤቱም ማቋረጡን በመተው ንግግሩን አድምጧል፡፡ ኡስታዝ አቡበከር ሲጀመር ኮሚቶዎቹ የተሰባሰቡት እና የጠየቁት የእምነት ነፃት መሆኑን፤ ይህንን ህገመንግስታዊ መብት መጠየቅ እንደወንጀል ተቆጥሮ መከሰሳቸው አግባብ እንዳልሆነ፤ “በማእከላዊ እስርቤት የሰቆቃ ተግባር የፈፀሙብን ሰዎች(ወደ ኮማንደር ከተማ እየጠቆመ) የሰሩት ወንጀል ምንም ሳይሰማቸው አሁንም በፍርድ ቤት እኛን ወንጀለኛ ለማስባል ከህግ ውጪ ምስክሮችን እያስፈራሩ የሀሰት ምስክርነት ሲያስመሰክሩ ፍርድ ቤቱ ነፃ ሆኖ ይታዘባል ብለን ዝም ብለናል አሁን ግን በህዝብ ፊት ኢቲቪ ወንጀለኛ መሆናችንን አውጇል ስለዚህ ከፍርድ ቤቱ የመንጠብቀው ነገር ምንድን ነው፤ ፍርድ ቤቱ ከዚ በኋላ ምን ይሰራል ውሳኔ እንደሆን ከባለስልጣናት ወርዶ በኢቲቪ ተወስኖብናል፡፡” በማለት ንግግሩን አብቅቷል፡፡ ሎሎችም ለመናገር በከፍተኛ ስሜት ውስጥ የነበሩ ሲሆን ለጥቂት ደቂቃ ችሎቱ በጉርምርምታ ተሞልቶ የነበረ ሲሆን ጠበቆች አረጋግተዋቸው የፍርድ ቤቱን መልስ አድምጠዋል፡፡ ፍርድ ቤቱ በሰጠው ምላሽ ሁላችሁም እንዳያችሁት ጠበቆቻችሁ ባቀረቡት አቤቱታ መሰረት ኢቲቪ በአቤቱታው ላይ ለመጪው አርብ መልሱን እንዲያቀርብ ቀጠሮ ይዘን አቀርበዋለሁ ያለውን ዘጋቢ ፊልም እንዳያቀርብ የእግድ ትእዛዝ ሰጥተናል፤ ዘጋቢ ፊልሙ በምን ሁኔታ እንደቀረበ ለእኛም ግልፅ አይደለም ለአርብ በፍርድ ቤቱ ቀርቦ መልሱን እንዲሰጥ የሰጠነው ቀጠሮ እንደተጠበቀ ነው፤ እናንተ ግን እስከዛው በጀመራችሁት ሂደት እራሳችሁን የመከላከል ሂደታችሁን (ምስክሮችን መስቀለኛ መጠየቅ) ቀጥሉ የቀረበው ዘጋቢ ፊልም የዳኞችን ገለልተኝነት በምንም አይነት የሚነካ አይደለም እኛ ለፍርድ ቤት ያልቀረበ መረጃን መሰረት አድርገን ውሳኔ አንሰጥም ብለዋቸዋል፡፡ የነፃነፃነት እና ፍትህ ምንጮች ዳኞቹ የሰጡት እግድ ተፈፃሚ እንዳይሆን የተደረገበት ሁኔታ በጣም አበሳጭቷቸው የነበረ መሆኑን ገልፀውልናል፡፡
በተያያዘ ዜና ከውስጥ ምንጮች መረዳት እንደቻልነው የኢህአዲግ ከፍተኛ ባለስልጣናት በኢቲቪ በተለቀቀው ዘጋቢ ፊልም ምንክንያት ሁለት ቦታ ተከፍለው የአቋም ልዩነቶች እንዳፋጩዋቸው አድርሰውናል፡፡ ሁለቱ ቡድን አንድ ግዜ ፍርድ ቤቱ እግድ ከሰጠ እግዱን ከማስፈፀም ውጪ እግዱ እንዲደናቀፍ የተደረገበት መንገድ የሀገሪቷን የፍትህ ስርአት ወትሮም ከመተቸት ወደኋላ ለማይሉ ድርጅቶ አመቻችቶ ለትችት አጋልጦ መስጠት ነው የሚሉት ሲሆኑ፤ ሌሎቹ የፍርድ ቤቱን ትእዛዝ ሽሮም ቢሆን ዘጋቢ ፊልሙ መታየቱ አግባብ ነበር ነገር ግን የቀረበው ፊልም እጅግ ዝቅተኛ ተቀባይነት እና ተአማኒነት ያለው ሆኖ መሰራቱ አግባብ አልነበረም የሚሉ ናቸው፡፡
በሌላ ዜና የሙስሊም ኮሚቴዎችን ጉዳይ የሚያየው ፍርድ ቤት የሰጠው ትእዛዝ ጠፍቷል መባሉ በጠበቆች፣ እና የፍርድ ቤት ሰራተኞች መሀከል ውዝግብ አስነስቷል፡፡ የከፍተኛው ፍርድ ቤት ትእዛዙ ከኢቲቪ መዝገብ ቤት ወጪ ተደርጎ እንዲመለስ በስልክ ካዘዙ በኋላ፤ የፍርድ ቤቱ ሬጅስትራር የሆነችው ሰው መስመር በመስመር የእግድ ትእዛዙን አንብባ የቃላት ግድፈቶችን ፈልጋ እንድታወጣ የተሰጣት የነበረ ቢሆንም በዛሬው እለት ትእዛዙ ለኢቲቪ ይገባል ተብለው ነበሩ ጠበቆች ሲጠይቋት የፍርድ ቤቱን ፕሬዚዳንት ፀሀፊ ጠይቋት ብላቸው ወደዛ ሲሄዱ ፀሀፊዋ ለሬጅስትራር ከተሰጣት በኋላ የእግድ ትእዛዙ ወደ እሷ እንዳልመጣ ተናግራ መልሳቸዋለች፤ ሬጅስትራሯን መልሰው ሲጠይቋት የፍርድ ቤቱን ትእዛዝ ታይፕ የምታደርገው ታይፒስቷን እንዲጠይቁ ልካቸው፤ ወደ ታይፒስቷ ሲሄዱ ታማ አልመጣችም መባላቸውን ምንጮቻቸችን አስረድተውናል፡፡ በተመሳሳይ የእግድ ትእዛዙን የሰጠው ፍርድ ቤት የችሎት ፀሀፊ የዳኞቹን የእጅ ፅሁፍ ሬጅስትራሯ መልሳለት ከመዝገቡ ጋር እንዲያያይዘው ጠይቋት እሷ እጅ እንደሌለ ገልፃለት በማሀከላቸው ውዝግብ ተነስቶ እንደነበር ምንጮቻችንን አክለው ገልፀዋል፡፡ በሌላ በኩል የፍርድ ቤቱ የእግድ ትእዛዝ በዛሬው እለትም ለኢቲቪ እንዳይደርስ ከላይ በዘገብነው መልኩ የተደረገ በመሆኑ በዛሬው እለት ኢቲቪ በህዝብ ጥያቄ ድጋሚ እንድናቀርበው ስለተጠየቅን በሚል የትላንትናውን የዶክመንተሪ ፊልም ደግመው ለማሳየት በዝግጅት ላይ መሆናቸውን ምንጮቻችን ያላቸውን ጥርጣሬ ገልጠውልናል፡