የጀርመን ድምጽ ሬዲዮ ጣቢያው ጀርባ ያለው መጋረጃ ሲገለጥ!!

ከሬዲዮ ጣቢያው ጀርባ ያለው መጋረጃ ሲገለጥ!!
ከጀርመን ቦን ከተማ የሚተላለፈው ዶቼቬሌ የጀርመን ድምጽ የዜና አቀራረብ ሚዛናዊነት አጠያያቂ እየሆነ መምጣቱን የሪያድ እና አካባቢው ኢትዮጵያውያን ወጣቶች ገለጹ ።
የጀርመን ድምጽ ራዲዮ ጣቢያ በአማርኛ ቋንቛ ወደ ኢትዮጵያ በሚያሰተላልፈው ሚዛናዊ ዜናዎቹ እና አዝናኝ ፕሮግራሞቹ የአያሌ ኢትዮጵያውያንን ቀልብ በመሳብ ታአማኝነትን ከማትረፉም በላይ በሚሊዮን የሚቋጠሩ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችንን ጆሮ መሳቡ የማይታበል ሃቅ ነው ።
ዛሬ ይህ ሬዲዮ ጣቢያ ኢትዮጵያ እና ከሃገር ውጭ በመላው አለም ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን አድማጮቹ የሚያስተላልፋቸው የዜና ዘገባዎች ሚዛዊነታቸው አጠያያቂ እየሆኑ በመምጣታቸው አንዳንድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን የዜና ዘገባውን ሃገር ውስጥ ከሚታተመው እና ግንባር ቀደም የህዝብ ጠላት ከሆነው ሪፖርተር ጋዜጣ ጋር ያመሳስሉታል።
ይህ ሬዲዮ ጣቢያ በተለይ በህዝብ ዘንድ እንደቀድሞው ታአማኝነትን ለማግኘት ለይስሙላ በሚያስተላልፋቸው ዜናዎቹ ውስጥ ለእማኝነት በዜና ትንታኔ ክፍለግዜ የሚያነጋግሯቸውን ሰዎች ቃል ለአየር ከማብቃታቸው በፊት የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ መንግስትን የሚያስቀይም መስሎ ከታያቸው እየቋራረጡ አሊያም የድምጽ ጥራት እንዳይኖረው በማድረግ ያዜናውን ትክክለኛነት በራሳቸው የማደናገሪያ የአማርኛ ዘይቤያቸው በመለወጥ፡ ህዝብ መረጃ እንዳያገኝ፡ እያደረጉ ያለው ተራ ሙከራ ከሬዲዮ ጣቢያው ጀርባ ማን አለ የሚለውን ጥርጣሬን በህዝብ ዘንድ የበለጠ አጉሉቷታል።
በሪያድ እና አካባቢው የተቋቋመውን የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ችግር መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ ለሁለት ለመሰንጠቅ ከጀርመን ቦን ከተማ ሳውዲ አረቢያ ሪያድ ዘርግቷት የነበረው የጥፋት እጁ ብለህ በሆኑት ኢትዮጵያውያን ሙስሊም የኮሚቴው ስራ አመራር አባላት ባይገታ ኖሮ ይህ ሬዲዮ ጣቢያ በጌቶቹ የተሰጠውን የቤት ስራ ተግባርዊ ለማድረግ ያደረገው ጥረት በቀላል ታይቶ የሚታለፈ አይደለም።
እራሱን ዶይች እያለ የሚጠራው ይህ ሬዲዮ ጣቢያ ሃገር ውስጥም እያደረገ ባለው እንቅስቃሴ ርቆ ለመሄድ የሞከረበት አጋጣሚ በህዝቡ አስተዋይነት መና ቀርቷል ። ለአብነት ያህል ቀደም ሲል ኢትዮጵያዊ ህዝበ ሙስሊሙ ወገናችን እያካሄዳቸው ያለውን ሰላምዊ የሃይማኖት ነጻነት ጥያቄ ይዘት ሚጢጢ አድርጎ አሳንሶ ለማቅረብ እያደረገ ካለው ሙከራ ባሻገር በኢ.ህ.አ.ዴ.ግ መንግስት በአሸባሪነት የተፈረጀውን የቪኦኤ ያህል የዜና ዘገባዎችን ለመዘገብ ትንፋሽ፡ያጠርዋል።
 ፌብርዋሪ 8 2013 በፍ/ቤት የታገደውን ሃረካቱን ጂሃድ የሚል የፈጠራ ዶክመተሪ ፊልም ያስተላለፈውን ኢቲቪ በመቃወም አደባባይ የወጣውን በሚሊዮን የሚቆጠር ሙስሊም ድምጽ ለአየር ከማብቃት ይልቅ ( ኢቲቪ እና የሙስሊሞች ተቃውሞ ) በሚለው የዜና ዘገባው የሃንስ ገ/ እግዛብሄር ከአዲስ አበባ ያስተላልፈው እና አሱን ተከትሎ የኢትዮጵያዊው ህዝበ ሙስሊም መሪዎች ጠበቃ ክቡር ተማም አባቡልጉ ለዝግጀት ክፍላቸው የሰጡትን መግለጫ ህዝብ እንዳይሰማው በደበዘዘ መልኩ እንዲቀርብ የትደረገበት አጋጣሚ ከሬዲዮ ጣቢያው ጀርባ ማን አለ የሚለውን ለማወቅ የግድ ነብይ መሆን አይጠይቅም።
ከዚህ ባሻገር ይህ ራዲዮ ጣቢያ መቀመጫውን ሳውዲ አረቢያ ጀዳ አድርጎ የመካከለኛውን ምስራቅ ዜና እንዲዘግብለት ያስቀመጠው ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ የሚያስተላልፋቸው ዜናዎች የጋዜጠኝነት ሙያዊ ክህሎትን በወጉ ያልጠበቁ እና ድብቅ አጀንዳ ያላቸው በማር የተጠቀለለ መርዝ ያለው ነው ። ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ የመረጃ እጠረት ያለበት ከመሆኑ አንጻር የሚያቀርባቸው ዜናዎች ከሳውዲ እስርቤት ያልዘለሉ እና ቢትዮጵያውያን የጋራ ጉዳዮች ላይ ከማጠንጠን ይልቅ ጊዜያዊ ባልሆኑ የግለሰብ ጉዳይ ገባ ወጣ የሚቆዝሙ ተራ ወሬዎች ናቸው ።
ቀደም ሲል በሪያድ በተለምዶ መንፉሃ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ አንዳንድ ስረአት አልበኛ የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ መንግስት ፖለቲካ የተጠናወታቸው ወገኖቻችን በብሄር ተደራጅተው እርስ በእርስ በሳንጃ እየተራረዱ የሃገራችንን በጎ ገጻታ ጥላሸት እየቀቡ ያለበትን ሁኔታ የጉዳዩ ባለበቤት ከሆኑት የአካባቢው ሰዎች በመረዳት ትክክለኛ ዜናውን ለአየር በማብቃት ጉዳዩ ትኩረት አጊቶ አልባት እንዲፈለግለት ከማድረግ ይልቅ የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ መንግስትን ክብር ይነካል በሚል መንፈስ በወቅቱ በመረጃ ተደግፎ በፌስ ቡክ ለአየር የበቃውን ሃቅ ለማድበስበስ የተደረገው ጥረት በወቅቱ በየቀኑ 2 እና 3 ዘጎቹን በሰው ሃገር የሚቀብረውን ኢትዮጵያጵያዊ የሪያድ ነዋሪ እጀግ በጣም አሳዝኗል።
ይህ በዚህ እንዳለ ሰሞኑን ፌብሪዋሪ 7 ምሽት 2013 ሪያድ ላይ በኢ.ህ.አ.ዴ.ግ የሚመራው መንግስት አዘጋጅቶ በነበረው የቦንድ ሽያጭ ፕሮግራም ላይ የተነሳውን ህዝባዊ ተቃውሞ ዜና እንዲሰራበት የሪያድ እና አካቢው ኢትዮጵያውያን ወጣቶች ያቀረቡለትን ጥያቄ ጆሮ ዳባለብስ ማለቱ በጥፋት ላይ ጥፋት ከመሆኑም በላይ ይህ ጋዜጠኛ ከሳውዲ አረቢያ አንዳንድ ግዜ የሚያስተላልፋቸው ዜናዎች የማይጨበጡ እና የማይዳሰሱ ከመሆናቸውም በላይ በሳውዲ አረቢያ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያኖች የልብ ትርታ ግንዛቤውስጥ ያስገባ አይመስልም። በአጠቃላይ የአሳ ግማቱ እንዲሉ ይህ ሬዲዮ ጣቢያ እየሰራ ያለው ድራማ ታማኝነቱ የጉዳዩ ባለበቤት ለሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ ሳይሆን በኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ለሚመራው መንግስት መሆኑንን በተጨባጭ በማረጋገጠ ላይ ነው።
በሳውዲ አረቢያ የሪያድ እና አካባቢው ኢትዮጵያውያን ወጣቶች ማህበር