ሀገር የጋራ ነው ሃይማኖት የግል ነው።

The Ethio-Canadian Forum for Democracy Ottawa, Canada
የIትዮ-ካናዳዊያን የዲሞክራሲ መድረክ በOታዋ ካናዳ

ሀገር የጋራ ነው ሃይማኖት የግል ነው።
ይህንን ጥንታዊ የAባቶች ብሂል የሚያናውፀው ምንም ሃይል የለም Aይኖርምም። ማሸበር፣ ማፈራረስ የዘወትር ተግባሩ የሆነው የወያኔ Aምባገነን መንግስት በባህል፣ በታሪክ፣ በቋንቋና በደም የተሳሰሩ ሕዝቦችን በሃይማኖትና በጎጥ በመከፋፈል Iትዮጵያውያን ለሠላም፣ ለፍቅር፣ ለAንድነትና ለወንድማማችነት ያላቸውን የቃል ኪዳን ትስስር ለመበጣጠስ ሌት ተቀን ይማስናል።የወያኔ Aምባገነን መንግስት ሁለቱን ታላላቅ ሃይማኖቶች ክርስትናውና Eስልምናው ተከባብረውና ተሳስበው በመኖር ለዘመናት ያስቆጠሩትን ትስስር ለመናድና ብጥብጥ ተነስቶ ደም Eንዲቃቡ፣ በዚህም Aጋጣሚ የስልጣን ዘመኑን ለማራዘም Eንቅልፍ Aጥቶ የተንኮል ሴራውን Eየቀፈቀፈ ነው።
የወያኔ Aምባገነን መንግስት የAንድነት መሰረት በሆነችው በIትዮጵያ Oርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ውስጥ ሠርጎ በመግባት ሕጋዊውን ፓትርያርክ ብፁE ወቅዱስ Aቡነ መርቆርዮስን ከመንበር Aውርዶ ፓትርያርክ በሕይወት Eያለ ሌላ ፓትርያርክ Aይሰየምም የሚለውን ቀኖና ቤተክርስቲያን ጥሶ የራሱን ካድሬ Aባ ገ/ መድህንን በመሾም በቤተክርስቲያኗ ታሪክ ላይ ጥቁር ጠባሳ ጣለ። ሕገ ቤተክርስቲያንን Aቆሸሸ። በዚህ Eኩይ ተግባሩም ታላቅ ብሄራዊ ወንጀል ፈፀመ።ጎጠኝነትን ፈጽሞ በማታውቀው ቅድስት ቤተክርስቲያንና ክቡር በሆኑት ገዳማት ዘረኝነትን Aስፋፋ፤ ቤተርስቲያኒቱን ለማውደም ምEመናን ልጆቿን በመንፈሳዊ ሕይወት ለማዳከም ቆርጦ የተነሳው ዘረኛና Aምባገነናዊው ስርዓት “Aላማችን የIትዮጵያ Oርቶዶክስንና የAማራውን ዘር Aከርካሪ መስበር ነበር ይህም ተሳክቶልናል” በማለት መረን የለቀቀ ድንፋታ Aሰማ።
የይስሙላው የወያኔ ሕገመንግስት ስርዓቱ በሃይማኖት ጣልቃ Aይገባም ቢልም ፈሪሃ EግዚAብሄር የሌላቸው ባለስልጣናት ከEንቅልፋቸው በባነኑ ቁጥር Aዋጁን ለEነሱ Eንዳመቻቸው በመተርጎም በሃይማኖት ውስጥ ጣልቃ በመግባት የክርስትና Eና የEስልምና Eምነት ተከታይ የሆኑ Iትዮጵያውያንን ለመከፋፋል በጠነሰሷቸው ሴራዎች ህዝቦች Eንዳይቀራረቡና የጋራ ችግሮቻቸውን በጋራ ለመፍታት Eንዳይችሉ Aድርገው Eነሱ ሀገርን የማፍረስ ተልEኳቸውን Eያከናወኑ ነው።Eነዚህ ማፈሪያዎች የሁለቱ ታላላቅ Eምነት ተከታዮች Eንዳይተማመኑና በAንድነት Eንዳይቆሙ ተደጋጋሚ ሙከራ ቢያደርጉም ምንም Aልተሳካላቸውም። Eናት ሀገራችን Iትዮጵያ የክርስቲያኑ፣ የሙስሊሙ፣ የተለያየ Eምነትን የሚከተሉና ምንም Eምነት የሌላቸው ሕዝቦች የጋራ መኖሪያችን መሆኗን በማይታጠፍ ቃላችን ደግመን ደጋግመን Eንገልጻለን።
Eኛ የIትዮጵያ ክርስቲያንና ሙስሊሞች የሃይማኖታችንና የምናፈቅራት Eናት ሀገራችን ባላንጣ የሆነውን የወያኔ Aምባገነን ሥርዓት ለመገርሰስ ከምን ጊዜውም በላይ Eጅ ለEጅ ተያይዘን ተነስተናል። ወያኔ በቤተ Eምነት ውስጥ የሚያደርገው ጣልቃ ገብነት በክርስቲያኖች ብቻ Aልቆመም፤ በሙስሊሙ ሕብረተሰብ ውስጥም ‘Aህባሽ’ የሚል በሀገራችን ያልተለመደ Eስላማዊ Aስተምህሮ
በሀይል ለመጫን ያልሸረበው ተንኮል የለም። መላው የሀገሪቱ ሙስሊሞች መንግሥት በሃይማኖታችን ጣልቃ Aይግባብን በማለት ሠላማዊ ጥያቄ በማቅረባቸው Aቤቱታቸውን የAሸባሪነት ታርጋ በመለጠፍ ጽንፈኞችና Aክራሪዎች በሚል ማስፈራሪያ ፈርጆ ፈጽሞ ከEውነት የራቀ የቅጥፈት ፕሮፓጋንዳ Eያሰራጨ ነው። የሙስሊሙን ማህበረሰብ Eውነተኛ የመብት ጥያቄ ለመመረዝና ከክርስቲያን ወገኖቹ ጋር ለማቃቃር፣ ብሎም የIትዮጵያን Aንድነት ለመሸርሸር “ጀሀዳዊ ሃረካት” በሚል መጠሪያ ከየቦታው በተቀነጫጨበ ፊልም የተሠራው Aሳፋሪ ድራማ በውሸት ላይ የተመሰረተ ሙያዊ ስነምግባርና ሃላፊነት የጎደለው ርካሽ ፕሮፓጋንዳ በወያኔ የዜና Aውታሮች በተደጋጋሚ ሲሰራጭ ሰንብቷል። ይህ ቅጥፈት የማንንም Aስተያየት ሊለውጥ ባለመቻሉ የወያኔ መሪዎች ተደናግጠዋል።
የሃይማኖቱን መደፈር በፀጋ የማይቀበለው ክርስቲያኑም ሆነ ሙስሊሙ የዚህን መሰሪ መንግስት የከፋፍለህ ግዛ ተንኮል ጠንቅቆ ያውቀዋል። ለዘመናት የተሳሰረበትን የፍቅር ሰንሰለት የሚበጥሰው ሃይል Eንደሌለም በተደጋጋሚ Aስመስክሯል። ክርስቲያኖች የሙስሊም ወንድሞቻቸውንና Eህቶቻቸውን የመብት ጥያቄ ምላሽ Eንዲያገኝ የግትል Aጋርነታቸውን Aሳይተዋል። ሙስሊሞችም የታሪካዊ ገዳማት ሕልውና በተደፈረበት ወቅት የድጋፍ ድምጻቸውን ከፍ Aድርገው Aሰምተዋል። EግዚAብሄር የተመሰገነ ይሁን!!!
ሁለቱም ታላላቅ ሃይማኖቶች የገጠማቸውን የወቅቱን ፈተና በሚገባ ለመረዳትና Aስፈላጊውን ግንዛቤ ለመጨበጥ Eንዲረዳ የሕጋዊው ቅዱስ ሲኖዶስ የሕዝብ ግንኙነት ተጠሪና የመላው ካናዳ የIትዮጰያ Oርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የበላይ Aስተዳዳሪ የሆኑትን ሊቀ ካህናት ምሳሌ Eንግዳንና ከቤተ Eስልምናውም ከAክቲቪስትና ጋዜጠኛ ሳዲቅ Aህመድ ጋር ሰፊ ውይይት በማድረግ ሁለቱም ቤተ Eምነቶች ዛሬ በወያኔ መሰሪ ደባ ያጋጠማቸውን መሰናክል ለመቋቋም የሚያደርጉትን Eንቅስቃሴ ለማገዝ ጥሪያቸውን በመቀበል ከጎናቸው በመቆም Aስፈላጊውን ሁሉ ለማድረግ ስብስባችን በAንድ ድምጽ ተስማምቷል። ሌሎችም መሰል ስብስቦች፣ ሕዝባዊ ድርጅቶችና የፖለቲካ ድርጅቶችም ቤተ Eምነቶችን ማዳን Iትዮጵያን ማዳን መሆኑን ተገንዝበው በጋራ በመቆም ትግላቸውን ወደ Aንድ Aቅጣጫ በማድረግ ይህንን የመከባበርና የAንድነት መንፈስ ለመናድ የተነሳውን የህልውናችን ፀር ለማስወገድ “ሀገር የጋራ ነው ሃይማኖት የግል ነው” በሚለው የAባቶች መርህ ስር Eንድንሰባሰብ በOታዋ የIትዮ- ካናዳውያን የውይይት መድረክ ጥሪውን ያቀርባል።
ለሀገራችን Aንድነት፣ ለሕዝባችን ልEልና ባደረጉት ያላሰለሠ ጥረት በወያኔ Eስር ቤት የሚማቅቁትን ጋዜጠኞች፣ የፖለቲካ መሪዎች፣ የክርስትናውና የEስልምናው Eምነት ተጠሪዎች በAስቸኳይ Eንዲፈቱ ድምጻችንን Eናሰማለን።
EግዚAብሔር Iትዮጵያን ይባርክ !!!!! February 13, 2013
ottawa.forum@gmail.com