ስምንተኛው የአዲስ አበባ ከንቲባ አዜብ መስፍን ወይስ ድርባ ኩማ?

የቀድሟ ቀዳማዊ እመቤት ወ/ሮ አዜብ መስፍን ከዚህ ቀደም በምርጫ ትወዳድርበት የነበረውን የትግራይ ክልል በመተው በአዲስ አበባ ከተማ ለምርጫ እንደምትቀርብ ከወደ አዲስ አበባ የመጡ ዜናዎች አመለከቱ።

•    የትራንስፖርት ሚኒስትሩ አቶ ድሪባ ኩማ ቀጣዩ ከንቲባ ይሆናሉ ተብሎ ይጠበቃል

ኢሕአዴግ ከእነዚህ አምስት ከፍተኛ ባለሥልጣናት ውስጥ አቶ ድሪባ ኩማን ለከንቲባነት ማጨቱን፣ ነገር ግን አቶ ድሪባ ከንቲባ ለመሆን ብዙም ፍላጎት እንዳላሳዩ ምንጮች ገልጸዋል፡፡

ኢሕአዴግ አቶ ድሪባን ከንቲባ ለማድረግ የፈለገበትን ምክንያት ምንጮች ሲያስረዱ፣ በትራንስፖርት ሚኒስቴርና ተጠሪ በሆኑ መሥርያ ቤቶች ለውጥ ለማምጣት የሚያደርጉትን ትጋት ካጤነ በኋላ ነው፡፡ በተጨማሪም አቶ ድሪባ የኦሕዴድ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልና በኦሮሚያ ክልል ውስጥ የሠሩ በመሆኑም ነው ተብሏል፡፡
 

 “የአቶ መለስ ዜናዊን ሌጋሲ እኔ አስፈጽመዋለሁ” በሚል በአቶ መለስ የቀብር መታሰቢያ ፕሮግራም ላይ በድፍረት የተናገረችው ወ/ሮ አዜብ በአሁኑ ወቅት የፌደራሉ ፓርላማ አባል ብትሆንም ኢሕአዴግን ወክላ በመጪው የቀበሌና የወረዳ ምርጫ ላይ ኢሕ አዴግን በመወከል በበቂርቆስ ክፍለከተማ እንደምትወዳደር የዘ-ሐበሻ የአዲስ አበባ ዘጋቢዎች አስታውቀዋል።

በተለይ “አፍቃሬ ኢሕአዴግ” በመባል የሚታወቀው የአቶ ልደቱ አያሌው ኤዲፓ በዚህ ምርጫ ላይ ሙሉ በሙሉ ሳይሆን በከፊል ብቻ እንደሚሳተፍ ባሳወቀበት በዘንድሮው ምርጫ ከወ/ሮ አዜብ ጋር ይወዳደራል ተብሎ የሚጠበቀው የኢዴፓው ወንድወሰን ተሾመ ነው። አቶ ወንደሰን ተሾመ ኢዴፓ ብቸኛው ያቀረበው እጩ ሲሆን ይህም እጩ ከወ/ሮ አዜብ በሚወዳደሩበት የምርጫ ጣቢያ እንዲወዳደር የተደረገው የፖለቲካ ትርፍ ኢሕአዴግ ለማግኘት አስቦ ነው ሲሉ አስተያየት ሰጪዎች ትዝብታቸውን ለዘ-ሐበሻ ይገልጻሉ።
ባልተለመደ መልኩ ከትግራይ ክልል ተነስታ በአዲስ አበባ ከተማ ለምርጫ የምትወዳደረው ወ/ሮ አዜብ ምርጫው የተበላ እቁብ በመሆኑ በቀጥታ አሸንፋ የአዲስ አበባ ካቢኔ ውስጥ በመግባት የኦሕዴዱን ኩማ ደመቅሳ ቦታ በመቀበል የከተማዋ ከንቲባ እርሷን ለማድረግ የታቀደ ነገር እንዳለ ያስታውቃል ያሉት ታዛቢዎች በተለይም ከሰሞኑ ከወ/ሮ አዜብ ጋር ቅርርብ አላቸው የተባሉ አንዳንድ የአዲስ አበባ መጽሔቶች “የሴት ጠ/ሚ/ር ማየት ናፈቀን” የሚል ጽሁፍ ሁሉ መጻፉን ከወ/ሮ አዜብ ወደ አዲስ አበባ ከንቲባ መምጣት ጋር አያይዘውታል – ታዛቢዎቹ።
አቶ አርከበ እቁባይ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ በነበሩበት ወቅት በአዲስ አበባ የታዩ ለውጦችን ቢያደርጉም የአዲስ አበባ ሕዝብ በምርጫ 97 ወቅት “አርከበ ለከተማዋ እድገት ብትጥርም፤ ኢሕአዴግን ወክለህ ብቻ ስለመጣህ አንመርጥህም” የሚል ምላሽ ከህዝቡ አግኝቶ ኢሕአዴግ በምርጫው በ0 በተሸነፈበት ወቅት ከወ/ሮ አዜብ ጋር እንደማይዋደዱ የሚነገርላቸው አቶ አርከበ በባልየው በአቶ መለስ ዜናዊ “በአዲስ አበባ ላይ ቀለም ከመቀባት በስተቀር ያመጣኸው ለውጥ የለም” በሚል በስብሰባ ላይ በግልጽ ተሰድበው ነበር።
በአሁኑ ወቅት ሕወሃት በክፍፍል ላይ እንዳለ እየተዘገበ መሆኑ ይታወቃል። የአቶ ስብሃት እና የወ/ሮ አዜብ ግሩፕ በየፊናው ተፋጧል። አሁን ወ/ሮ አዜብን በአዲስ አበባ ከንቲባነት አማሎ ድርጅቱን የማዳን ሥራ እየተሰራ ነው የሚሉ የፖለቲካ ተንታኞች አሉ። 

 አዲስ አበባ ሙሉ በሙሉ ከኦሮሚያ ክልል ጋር የምትዋሰን በመሆኑና ከተማዋ በርካታ ጥቅሞችን ከኦሮሚያ ጋር የምትጋራ በመሆኑ፣ በቀጣዩ የሥራ ጊዜ ስለሚኖረው የተቃና አፈጻጸም የአቶ ድሪባ አስተዋጽኦ የተሻለ ይሆናል የሚል ታሳቢ ተደርጎ መሆኑን ምንጮች ይጠቁማሉ፡፡

የተቀሩት ከፍተኛ ባለሥልጣናት በዕጩነት የተያዙት በተለያዩ ምክንያቶች መሆኑን ምንጮች ይገልጻሉ፡፡ ምንጮች እንደሚሉት፣ ኢሕአዴግ ምርጫውን እንደሚያሸንፍ ከወዲሁ አመላካች ሁኔታዎች ቢታዩም አማራጮችን ለመያዝ ሲል ነው ይላሉ፡፡ በሌላ በኩል ኢሕአዴግ አዲስ አበባ ላይ ትልቅ ሥራ እንደሚጠብቀው በማመን በየመሥርያ ቤቶቻቸው ጥሩ የሥራ አፈጻጸም ያላቸውን ባለሥልጣናት ወደ አዲስ አበባ ማዛወር ፈልጓል፡፡

ኢሕአዴግ እነዚህን ባለሥልጣናት ካሉበት መሥርያ ቤት ማዛወር ባይፈልግ እንኳ፣ ለከተማው አስተዳደር ቅርብ ሆነው ሥራዎችን እንዲያግዙ ያደርጋል ይላሉ ምንጮች፡፡ በሚያዝያ ወር አዲስ አበባንና ድሬዳዋን ጨምሮ በሁሉም ክልሎች የአካባቢና የማሟያ ምርጫዎች ይካሄዳሉ፡፡

ኢሕአዴግ ሙሉ በሙሉ ዕጩዎችን ቢያስመዘግብም፣ መድረክና መኢአድ ከምርጫው ውጭ በመሆን ላይ ናቸው፡፡ ‹‹ኢሕአዴግ በምርጫው ላይ የተቃዋሚውን ሚና ትርጉም አልባ ቢያደርገውም ኢዴፓ በተፅዕኖ ከምርጫ ሥርዓቱ ተገፍቼ ላለመውጣት ስል ብቻ በአንድ ዕጩ ብቻ እወዳደራለሁ፤›› ሲል ኢዴፓ ሰሞኑን አስታውቋል፡፡

በአገሪቱ የምርጫ ፖለቲካ ተሳታፊ ሲሆኑ የቆዩት እነዚህ ፓርቲዎች ምርጫውን በአብዛኛው ለኢሕአዴግ በመተው አፈግፍገዋል፡፡

ምርጫውን ኢሕአዴግ ካሸነፈ ኢሕአዴግ ኢትዮጵያን ከተቆጣጠረ በኋላ ስምንተኛው ከንቲባ አቶ ድሪባ ኩማ ይሆናሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ምክንያቱም አቶ ድሪባ ለጊዜው ከንቲባ ላለመሆን ቢያንገራግሩም ከፓርቲያቸው ውሳኔ ውጪ ስለማይሆኑ ነው ይላሉ ምንጮች ምክንያታቸውን ሲያስረዱ፡፡ ምርጫው ከመድረሱ በፊት በአሁኑ ወቅት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ መሬት ልማትና ማኔጅመንት ሥራ አስኪያጅ አቶ ጌታቸው አምባዬ ከንቲባ ይሆናሉ የሚል መረጃ ወጥቶ ነበር፡፡

ነገር ግን ያገኘነው መረጃ እንደሚያስረዳው አቶ ጌታቸውና ከንቲባ ኩማ ደመቅሳ በሚያዝያ 2005 ዓ.ም. ምርጫ ተወዳዳሪ አይደሉም፡፡  

  ኢሕአዴግ በቀጣዩ ምርጫ አዲስ አበባ ላይ እንዲወዳደሩ አምስት ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናትን በዕጩነት አቀረበ፡፡