አስገራሚው የሪፖርተር ጋዜጣ በሙስሊሞች የመብት ጥያቄ ላይ!

አቶ አማረ አረጋዊበበረሀ እሱና ባልደረቦቹ ሲያፍተለትሉት እና ሲያሴሩበት በነበረው ቤተክርስቲያንን በህወሀት ካድሬዎችየመሙላት እናየሚፈልጉትን ፓትሪያርክ የማንገስ የዘመናት ሴራ ጉዳይ፤ አሁን እንደገለልተኛ ሰው የፒኤችዲ ማሟያ ፅሁፍ እየፃፈነውብለው አስገረሙን፡፡

(ከጫካ የሚጀምረው የህወሀት ፓትሪያርክ የመሾም እቅድ እና ድርጊት- ምንጭ እንቁ መፅሄት ጥር- 2005 )
በሌላ በኩል የሙሰሊሞች የሀይማኖት ነፃነት እና የመብት ጥያቄ ከተጀመረ ጀምሮ ሪፖርተር እጅግየሚዋዥቅና አስመሳይገለልተኛ አቋም በማራመድ ቆይቷል፡፡ የሙስሊሞች የሀይማኖት ነፃነት ጥያቄ በተጀመረበት ወቅት፤ አቶ አማረ አረጋዊየሪፖርተር ጋዜጣ ፀሀፊዎች እና አቀናባሪዎችን ሰብስቦ በሙሰሊሙ ጉዳይ ላይ የሚጽፉበት የመንቀሳቀሻ ትራክ በተመለከተገለፃ ያደረገላቸው ሲሆን፤ በግልፅ ሙስሊሙ ህብተተሰብ እንዲህ አይነት ጥያቄ በመጠየቁ አብዝቶታል መንግስት እርምጃመውሰድ አለበት የሚል አቋሙን ያለ ሀፍረት ለሰበሰባቸው ሰራተኞቹ ተናግሮአል፡፡

ይህንን የአቶ አማረ አቋም ተከትሎበሪፖርተር ጋዜጣ ላይ የወጡ ጽፎች የሙስሊሙን እንቅስቃሴ የሚያጥላሉ እና ሀይማኖት በመንግስት ጉዳይ መንግስትበሀይማኖት ጉዳይ ጣልቃ አይገባም አልገባም የሚሉ ጽሁፎችን አቅርቧል፡፡ ይህም ሆኖ በድረገጾችሪፖርተር በነፃ ፕሬስ ስም እያተመ ያለውን እጅግ ሚዛን የጎደላቸው ጽሁፎች ከፍተኛ የሙስሊሙ ህብረተሰብ ተቃውሞዎችአስተናግዷል፡፡ በዚህም ምንያት የሪፖርተር ጋዜጣ ድረገጽ በውግዘት በመሞላቱ ለተወሰነ ግዜ ጋዜጣው ድረገጹንየማይሰራ(inactive) ለማድረግ ተገዶ ነበር፡፡ ሪፖርተር ጋዜጣን የሀሰተኛ ነፃ የግል ጋዜጣነት የሚያጋልጡጽሁፎች እና ጸረ ሪፖርተር ጋዜጣ የፌስቡክ ግሩፖችም ታይተዋል፡፡

 እንዲሁም ግልጽ ደብዳቤ ለሪፖርተር ጋዜጣ የሚሉጽሁፎች ተለጥፈው አንብበናል፡፡ ይህንን የህዝብ ውግዘት ተከትሎ የሪፖርተር ጋዜጣ በመጠኑ የሙስሊሞችየሀይማኖታዊ መብት ጥያቄዎች መልስ ሊሰጠው ይገባል የሚሉ ፅሁፎችን በማውጠት ሪፖርተር ላይ የተቀየመውን የህዝበሙስሊሙን ልብ የሚያባብሉ ፅሁፎች አስነብቧል፡፡
 ለአብነት ያክልም የመጅሊስ ምርጫን አስመልክቶ ያወጣው ጽሁፍ ተጠቃሽነው፡፡ ይህም ሆኖ አማረ አረጋዊ ሲጀመር የሙስሊሞችን የሀይማኖት ነፃነትና የመብት ጥያቄ የሚያኮስስ አቋም በውስጡየተከለ በመሆኑ በእለት እሁድ የሪፖርተር እትም የተለያዩ ግለሰቦች አመለካከት አስመስሎ የራሱን አቋም‹‹ጅሃዳዊ ሐረካት›› - በጥርጣሬና በጥያቄ መሀል በሚል አውጥቷል፡፡

የሆሊውድ ፊልምሳይቀርተቀንጭቦመኪናሲፈነዳ የታየበት አሳዛኙ ዶክመንተሪ የኢትዮጲያን የፍትህ ስርአት ከናካቴው ሚቀብር መሆኑ ህዝብ ቢስማማበትም አማረ አረጋዊ ግን የከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዚደንት የሦስት ዳኞችን ትእዛዝ ማቆም ይችላሉ በሚል ይሞግታል፡፡ እንደሚሚ ስባቱ ያሉፀረ ህዝብ የስርአቱ አሽቃባጮችን ስሟን ቀይሮ አስተያያቷን የሰጠች ጋዜጠኛ በማለት፤ ኢቲቪ ውሸታምነቱ ግልጽቢሆንም መንግስት ህዝብን የሚያበጣብጥ አላማ ቢኖረውም ዶክመንተሪው እውነት ሊሆን ይችላል ልናምነው ይገባል በማለትይሞግታል፡፡

ለህግ ጥሰቱም የቀድሞ ጠቅላይ ሚ/ር በፓርላማ በወቅቱ በሽብር ተጠርጥረው የነበሩ ሰዎችን ወንጀለኛመሆናቸውን አረጋግጠናል ያሉበትን እና ሽመልስ ከማል በ‹‹ጅሃዳዊ ሐረካት›› ከሙስሊሙ ህብረተሰብ መፍትሄ አፈላላጊኮሚቴዎች ጋር በምንም በምንም አይገናኙም እየተባሉ ያሉትን ሰዎች ክስ ያልተመሰረተባቸው ሰዎች ናቸው ማለታቸውንበመጥቀስ የመንግስትን አቋም የጽሁፉ ማጠቃለያ በማድረግ ያበቃል፡፡

ሪፖርተር እውነተኛ ነፃ የግልፕሬስ ቢሆን ኖሮ የህዝብን ቁጣ በመሸፋፈን ዶክመንተሪው እውነት ሊሆን ይችላል በሚል ካወጣው ጽሁፍ ባልተናነሰየኢትዮጲያ የፍትህ ስርአት አዘቅት እየገባ መሆኑን፤ ኢቲቪ በስህተት ባወጣው የለሊት 7፡00 ስርጭቱ የዜጎች መብትበደህንነቶች የሚጣስ መሆኑን፤ የዳኞች ትእዛዝ በግለሰብ እየተደናቀፈ እንደሆነ ፤ ከህዝብ በሚሰበሰብ ግብርየሚተዳደረው ኢቲቪ የዜጎችን ህገመንግስታዊ መብት የሚነካ ድርጊቱን እንዲያቆም፤ ፖሊስ የዜጎችን ሰብአዊ ክብር እናህገመንግስቱን አክንሮ እንዲሰራ ባያምንበት እንኳን ማሳሰብ ነበረበት አቶ አረጋዊም ሆነ ሪፖርተርጋዜጣ እንደሬዲዮ ፋና ለክፉ ቀን ዘመቻ የተዘጋጁ የአጋዚ ጦር አይነት ፕሬሶች ሲሆኑ፤ በሰላሙ ቀን ግን በአስመሳይባህሪያቸው ህዝብን ለማታለል የሚወተረተሩ በመሆኑ ለህዝብ እንሰራለን የሚሉ ከሆነ የተሸሸጉበትን ደበሎአቸውንእንዲያወልቁ እንጠይቃለን ፡፡