ታላቅ የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ኡለማ ማህበር ሪያድ ላይ ተመሰረተ ።

ሰበር ዜና
ታላቅ የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ኡለማ ማህበር ሪያድ ላይ ተመሰረተ ።
ዛሬ በኢትዮጵያ ሰአት አቆጣጠር 10 ሰዓት ጀምሮ በህዝበ ሙስሊም ወገናችን ኮሚቴዎቻችን ይፈቱ ፤ አሸባሪዎች አይደለንም ፤ ጭቆና ይብቃ ፤ ድምጻችን ይሰማ በሚሉ ቢጫ እና ነጭ ካኔቴራ በለበሱ ወጣቶች እና አረጋውያን እናት እና አባቶች የተጨናነቀው የሰደቃ ፕሮግራም በአሁኑ ሰአት በደማቅ ሁኔታ በመካሄድ ላይ ነው።

በዚህ ታላቅ ህዝባዊ የሰደቃ ፕሮግራም ላይ ለመሳተፍ ከመካ ፤ከ መዲና ፤ከጅዳ ፤ከጣይፍ ፤ ከደማም እና ከኮበር ከተለያዩ ሳውዲ አረቢያ ከተሞች በመጡ ሙስሊም የሃይማኖት አባት ኢትዮጵያውያን ኡለማዎች ሃገር ውስጥ የሚደረገውን ሃይማኖታዊ በደል ግፍ እና ጭቆና በመቃወም በኢትዮጵያ ሰላማዊ የሃይማኖት ነጻነት ትግል እያደረጉ ያሉ ወገኖቻችንን ትግል ለማጠናከር የሚረዳ የኢትዮጵያ ሙስሊም ኡለማዎች ማህበር መመስረቱ ተበስሯል።

ሃገራችን ውስጥ በህዝበ ሙስሊሙ ወገናችን እይተካሄዱ የሚገኙትን ሰላምዊ የሃይማኖት ነጻነት ትግሎች በሚያመላክቱ ስ ዕላዊ የፊልም መግለጫዎች የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ስረዓት እየፈጸመ ያለውን ግፍ እና በደል ህዝብ የተሰበሰበብት አደባባይ ላይ በተለጠፍ አስክሪን በማሳየት እና የተለያዩ የዳዎ ፕሮግራሞችን ለታዳሚው በማሰማት እስካሁን በዘለቀው በዚህ ታላቅ የሪያድ የሰደቃ ፕሮግራም ላይ የህዝበ ሙስሊሙን አንድነት ለመበተን ከመንግስት ጎን ቆመው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ አንዳንድ ወገኖች በሰሩት ስራ ተጸጽተው በዚህ አጋጣሚ ህዝቡን በይፋ ይቀርታ ይጠያቅሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ምስጢራዊ ምንጮቻችን ከስፍራው ገልጸዋል።

ዛሬ እስከ ግማሽ ለሊት በሚዘልቀው በዚህ የሰደቃ ፕሮግራም ድምጻችን ይሰማ ተቃውሞ ላይ እስከ 45 ሺህ ህዝብ ይገኛል ተብሎ ይጠበቃል። ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ግዜ ድረስ በአካባቢው የሰደቃው ፕሮግራም ላይ ፎቶ ማንሳት በጥብቅ የተከለከለ በመሆኑ የሰደቃ ፕሮግራሙ አዘጋጆች በይፋ አስኪፈቅዱ ድረስ በእጃችን የሚገኙትን ምስሎች እዚህ ገጽ ላይ ለመለጠፍ የምንቸገር መሆኑንን እንገልጻለን።
በሳውዲ አረቢያ የሪያድ እና አካባቢው ኢትዮጵያውያን ወጣቶች ማህበር