ሰበር ዜና አዲስ ጸረ-ሙስሊም ሀሰተኛ ፊልም ኢቲቪ ማክሰኞ ይለቀቃል ::

ኢቲቪ ለረጅም ወራት የተዘጋጀበትን ሀሰተኛ ዶኩመንተሪ ፊልም“ጂሃዳዊ ሃረካት”የፊታችን ማክሰኞ ሊያቀርበው ነው፡፡
 

ጂሃዳዊ ሃረካት በሚል ኮሚቴዎቻችን ላይ መርዙንሊረጭ ነው፡፡ሙስሊሙን ከክርስቲያኑ ጋር ለማጋጨት የታለመ
ዶክመንተሪ ፊልም ነው፡፡


እስከ ዛሬ በሙስሊሙ ኅብረተሠብ ላይ በጥላቻ የተለወሠውን ጥይት ዘውትር ይቶክስ የነበረው ETV በመጪው ማክሰኞ የመጨረሻው ሚሳይል ሙስሊሙ ላይ ሊቶክስ ነው

ሀቅን በዶዘር ቆፍራቹህ አርቃቹህ ብትቀብሮዎት በአካፋም ቢሆን ቆፍራ አንድ ቀን መውጣትዎ አትቀርም

 

ኢቲቪ ከዚህ ቀደም ያሰራጫቸውና በዛሬው ዕለትም በመጪው ማክሰኞ ይቀርባል ብሎ ያስተዋወቀው “ጂሃዳዊ ሃረካት” የሚል ርዕስ የተሰጠው አዲስ “አኬልዳማ” በኢቲቪ ቢሰራጭም፣ የድራማው ስክሪፕት የሚጻፈውና የምስክር ተብዬዎቹ ቀረፃ የሚካሄደው ወዘተ. በብሔራዊ መረጃ እና ደኅንነት ኤጀንሲ አማካይነት እንደሆነ ከታመነ ምንጭ ማረጋገጥ ተችሏል፡፡ … የሆነው ሆኖ ለማክሰኞ የተደገሰው መንግሥታዊ ድራማ ዓላማው ህዝብን ሐሰት በታጨቀ የተቀናበረ ድራማ፣ የአገሪቱን ህዝብ ማታለል፣ ማሸበር፣ ሙስሊሙ እና ክርስቲያኑ በጥርጣሬ እንዲተያይ ማድረግ፣ በህዝበ ሙስሊሙ ጥያቄዎች መፍትኄ አፈላጊ ኮሚቴ አባላት ላይ የክስ ሒደት ላይ ፍፁም ሕገ ወጥ በሆነ መንገድ ተጽዕኖ በማድረግ ከወዲሁ ከፍርድ ቤት ውጪ በተከሳሾች ላይ ለመፍረድ … እና ሌሎችም ብዙ ሰይጣናዊ ዓላማዎችን ለማሳካት ነው፡፡ … የማክሰኞው ድራማ ማስታወቂያ ላይ ከሰማሁት የገረመኝ “ኢስላማዊ መንግሥት ለመመሥረት …” የምትለው እና በፍርድ ቤት እንኳ ውድቅ የተደረገው ክስ በስክሪፕቱ ውስጥ መካተቱ ነው፡፡ …

… ግዴላችሁም ወንድሞቼ እና እህቶቼ … በአላህ ፈቃድ ይህኛውም ቀሽም ድራማ የመንግሥታችንን እውነተኛ ማንነት ይበልጥ በማጋለጥ ህዝበ ሙስሊሙ መብቱን ለማስከበር የጀመረውን ትግል ይበልጥ አጠናክሮ እንዲያፋፍም ተጨማሪ ምክንያት ከመሆን በቀር ምንም እንደማያመጣ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ … ይህ እንዳለ ሆኖ ግን ድራማው ከመቅረቡ በፊትም ሆነ ከዚያ በኋላ አጠናክረን በምንቀጥለው ትግል የድራማውን ዕኩይ ዓላማዎች ለማክሸፍ፣ በተለይም ክርስቲያን ወገኖቻችን በመንግሥት ፕሮፖጋንዳ እንዳይሸበሩ ከእኛ የሚጠበቀውን ሥራ በሁሉም የሀገራችን ክፍሎች የምንገኝ ሙስሊሞች በጣም ተግተን መሥራት ይጠበቅብናል፡፡ ለዚህም እጅግ ወሳኝ ሥራ በፍትኅ ራዲዮ ከቁጥር 1 እስከ 10 የተካተቱትን የውድ ኮሚቴዎቻችን ንግግሮች በሞባይላችን አማካይነት ለክርስትና እምነት ተከታይ ወገኖቻችን ብናሰማቸው መልካም ይመስለኛል፡፡ አላህ (ሱ.ወ.) ሐቅን በባጢል (ሐሰት) ላይ የበላይ የሚያደርግበት ጊዜ ሩቅ አይደለም፡፡ ኢንሻአላህ፡፡ አላህ ይህን ወንበዴ መንግሥት ከአገራችን ኢትዮጵያ እና ከህዝቧ ጫንቃ ላይ አሽቀንጥሮ ይጣልልን፡፡ አሚን፡፡

በቀን 25/05/2005 ማታ 2 ሰአት ዜና መሀልላይ አሸባሪ መንግስታችን ሁለተኛ ሃሰተኛድራማውን ማክሰኞ ምሽት እንደሚያሳይ
አስታወቀ፡፡ ከማስታወቂያውም መካከልአቡበከር አህመድ የተናገረውን አሸባሪ፣ አክራሪ…እያሉ የሚለውን ንግግሩን ቆርጠው
አቅርበውታል፡፡ እንዲሁም ግንባራቸው ላይ ኑርያለባቸውን ሙስሊሞች ፎቶ እያሳየ ጉድጓድሲቆፍሩ፣ መሳሪያ ሲቀብሩና ሲያወጡ እንዲሁምእስላማዊ መንግስት ለመመስረት የሚያስችልቅድመ ዝግጅት እንዳደረገ የሚገልጽ ….በማሳየት ማክሰኞ ማታ እንደሚያሳይ
አስታወቀ፡፡ 

ያ ጀመአ አሁን ጊዜው ደርሷል ምንማድረግ እንዳለብን ሹራ እናድርግ አስታያየት ስጡበት::