የሙስና አገዛዝ፤ ፍርሃትና ሰም ማጥፋት

ፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም
ወደ ፌብሪዋሪ 2013 ፈጠን ብለን እንሂድ::  በቅርቡ ተጣርቶ በወጣው ባለ 448 ገጾች የዓለም ባንክ ዘገባ እንደሚያሳየው ኢትዮጵያ በዓለም ላይ ካሉት ሀገራት ሁሉ ከአናት እስከ ታች ድረስ በባለስልጣናቱና በአጃቢ አገልጋዮቻቸው ንቅዘትና ሙስና የተዘፈቀች ሃገር ናት ይላል፡፡ በዘገባው መሰረት የኢትዮጵያ ቴሌኮሙኒኬሽን ድርጅት የንቅዘቱ መፈልፈያ ማህጸን ነው፡፡  ገዢው ኣስተዳደር በጣሙን የገዘፈ መዋእለ ንዋይ በማፍሰስ በቴሌ ላይ ኢንቬስት ቢያደርግም፤በአፍሪካ ሁለተኛው የቴሌፎን ስርጭት ዝቅተኛ የሆነበት ሃገር ከመሆን አላዳነውም፡፡ በጣም አናሳ አግልግሎት ሰጪ ድርጅት ከመሆንም አልፎ፤ከተጠያቂነት ነጻ የሆነ የዘረፋ ማእከል ነው፡፡በሃገርም ውስጥ ሆነ በውጭ ታዛቢዎች ድርጅቱ በሙስናና በንቅዘት የተገነባ ለምዝበራ የተጋለጠ መሆኑን ያረጋግጣሉ፡፡ በየትኛውም የአገልግሎት አሰጣጥ መመዘኛ ተጎታችና እርካታ ይሉት አገልግሎት የሌለው በየጊዜው በሚነደፈው የሙስና እቅድ ውስጥ ተውተፍትፎ አገልግሎቱ እርባና ቢስ ነው፡፡ የፍትህ ስርአቱም ቢሆን ሕብረተሰቡን በነጻ እንዳያገለግልና የፖለቲካ መሳሪያ እንዲሆን ተደርጎ በገዢው ኣስተዳደር ንጹሃንን በመወንጀል ፖለቲካዊ እንቅስቃሴን በመግታት አገዛዙ ከመንበሩ ሳይለቅ የሚቀጥልበትን ሁኔታ የሚተገብር የፍትህን ስርአት የጣሰ ነው፡፡ ይህም በህጋዊ ኢፍትሃዊነት ብቻ ጉዳት ከማድረሱም ባሻገር ለጉቦና ለንቅዘት ተጋልጦ ያለ አንድ የገዢው መንግስት የጦር መሳርያ ነው፡፡ ገዢው መንግስት በስልጣን መቆየቱን እንጂ ለሃገርና ለህዝብ እድገትና ልማት ጨርሶ ደንታ የሌለው በመሆኑ ከጉቦ ውጪ አንዳችም ጉዳይ በስርአት አይከናወንም:: የዚህም ሂደት ዋናው አስፈጻሚ ሞተር ገዢው ፓርቲና ጀሌዎቹ ናቸው፡፡
በፌብሪዋሪ 5/2013 ላይ በአዲስ አበባ ያለው ገዢው ኣስተዳደር ‹‹ጂሃዳዊ ሃራካት›› (የቅዱስ ጦርነት እንቅስቃሴ) በሚል ርዕስ አንድ ዘጋቢ (ዶኩሜንታሪ) ፊልም በእኩይ አስተሳሰብና ዲያብሎሳዊ ግንዛቤው የኢትዮጵያ ሰላማዊ ሙስሊሞች ያነሱትን ሃይማኖታችንን ለኛ ተዉልን፤ ሰብአዊ መብት ይከበር፤ በማለቱና በሰላማዊ መንገድ እንሰማ በማለታቸው፤ በየቦታው ካሉና የኢትዮጵያ ሙስሊም ሕብረተሰብ ከማያውቃቸው፤ ተግባራቸውን ከማይቀበለውና ግንኙነትም ከሌለው ጋር ገዢው ኣስተዳደር በተካነበት የቅጥፈት ዘመቻው ጥያቄ  እንዳሰኘው በሚያዝበት ቴሌቪዥን ጣቢያው ላይ አሰራጭቶ ነበር፡፡
‹‹ጂሃዳዊ ሃረካት›› በሁለንተናዊ መልኩ የ‹‹አኬልዳማ›› ግልባጭ ነው፡፡ መሰረታዊ ልዩነቱ የሙስሊሙን ማሕበረሰብ ለይቶ ለማስፈራሪያነትና ለስም ማጥፊያ ተብሎ በአንድ የሃይሞነት ተከታዮች ተነጣጥሮ መተግበሩ ነው፡፡ በአጠቃላይ ዘጋቢው ፊልም ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች ሰብአዊ መብት እንዲከበር፤ ኣስተዳደሩ በእምነታቸው ጣልቃ መግባቱን እንዲያቆም በመጠየቃቸው፤ ያላለሙትንና ጨርሶ ያላሰቡትን ሕዝቡ ናቸው ብሎ እንዲቀበል፤ እነዚህ ደም የጠማቸው የናይጄሪያው ቦኮ ሃራም፤የማሊው አንሳር ዲን፤ አልቃይዳ አልሻባብ ሃማስ ቅርንጫፍ ተከታዮች  በማለት ያልሆኑትን ናቸው በማለት በተለመደው የፍርሃትና የመደናገጥ ዜማው ታርጋ በመለጠፍ ላይ ያተኮረ ነው፡፡  ዶኩሜንታሪው ተቆቋሪ በመምሰልና አዛኝ ቅቤ አንጓችነቱን በማጠናከር በሙስሊሙ መሃል የተሸሸጉ ጥቂት ሽብርተኞች በማለት ይኮንናል፡፡ ዘጋቢው ፊልም በየትም የአፍሪካ ያልታየ የቂመኝነትና የትእግስት ማጣት እኔ ካልኩት ውጪና ከምፈቅደው ባለፈ ንክች ያባ ቢላ ልጅ ይሉት ዓይነት ድንፋታ ብቻ ነው፡፡
ውሸት ሞልቷል፤ እርቃኑን የቆመ ውሸት አለ፤የጎደፈ ውሸት አለ፤የሆዳሞች ውሸት አለ፤የመልቲዎች ቅጥፈት አለ:: ‹‹ጂሃዳዊ ሃረካት›› ደሞ እነዚህ ሁሉ ውሸቶች የተጠናወቱት ነው፡፡ ይህን የሚያቀለሸልሽ ዶኩሜንታሪ ከተመለከትኩት በኋላ፤ በቅርቡ ያለፈው መለስ ዜናዊ የሜይ 2010ን ምርጫ 99.6 በሌብነት የተገኘ ድል አስመልከተው የአውሮፓ ዩኒየን የምርጫ ታዛቢዎች ስለተከናወነው የድምጽ ሌብነቱ  ፊት ለፊት ሲጋፈጡት የሰጠው ምላሽ ታወሰኝ፡፡ መለስ እጅ ከፍንጅ በመያዙ የአውሮፓ ዩኒየነን የምርጫ ዘገባ በመኮነን ከአንድ መሪ በማይጠበቅ መልኩ ማፈሪያ የሆነውን ‹‹ዘገባው ቆሻሻ ስለሆነ ንብረቱ  ወደሆነው ወደ ቆሻሻ መጣያ ሊወረወር ይገባዋል›› ነበር መልሱ፡፡ ‹‹ጂሃዳዊ ሃረካት›› ደካማ፤ አስቂኝ፤ማሰብ ከተሳነው ህሊና የወጣ፤ማስመሰያ፤ መርዘኛ፤ በጉራ ያበጠ፤ ድንፋታ ነው፡፡ ይህን መሰሉ የመለስ አባባልም የቅራ ቅንቦ ክምር ነውና ‹‹ጂሃዳዊ ሃረካት›› ወደ ቆሻሻ ቱቦ ተደፍቶ ከእጥብጣቢውና ከቆሻሻው ፍሳሽ ጋር ሊቀላቀል ይገባዋል፡፡
ፈጽሙ የተባሉትን ያለ ጥያቄና ስስብእናቸውን ለጥቃቅን ጥቅም በመሸጥ ታዛዥነታቸውን የሚያረጋግጡትን አሰባስቦ ተመረጡ ብሏል፡፡ ቀድሞ ለዘመናት ከመንግስት ተጽእኖና ቁጥጥር ነጻ የነበረው አስልምና ካዉንስል አሁን በገዚዎቹ  የሚታዘዝና የገዚዎቹን ትእዛዝ በመቀበል የሚያስፈጸም የካድሬዎች መጠራቀሚያ ሰፈር ሆኗል፡፡ መያዙ፤በሽብርተኝነት ወንጅላ ካውንስሉን የመቆጣጠር ህልሙን ተግባራዊ ማድረጉ በኢትዮጵያ ውስጥ ገዚዎቹ ሃይማኖቶቹን መጠቀሚያ የማድረጉ ሂደት እየባሰ መሄዱን የሚያረጋግጥ ነው፡፡ በሰላማዊ እንቅስቃሴያቸው ጊዜ በርካታ ሙስሊሞች በመላ ሃገሪቱ ለእስራት እየተዳረጉ ነው፡፡ በኦክቶበር 29 ገዢው የኢትዮጵያ መንግስት 29 ሰላማዊ እንቅስቃሴ ላይ የነበሩ ሰዎችን በሽብርተኝነትና የሙስሊም መንግስት ለማቋቋም ተንቀሳቅሰዋል በሚል ለእስር ዳርጓል፡፡