ሰበር ዜና- ከቤት ለቤት ፍተሻ እና ዘረፋ ወደ ኢንተርኔት ካፌዎች

ሰበር ዜና
ከቤት ለቤት ፍተሻ እና ዘረፋ ወደ ኢንተርኔት ካፌዎች

የሙስሊሙን ተቃውሞ ለማኮላሸት የተቋቋመው የአፈና እና የስለላ ግብረ ሃይል ፊቱ ወድ ኢንተርኔት ካፌዎች ሊያዞር መሆኑን አዲስ የደረሰን መረጃ ያመለክታል:: በዚህም መሰረት የመጀመሪያው የደህንነት ቡድን በ22 ማዞሪያ እና ቦሌ አከባቢ; በመሳለሚያ እና በኮልፈ መርካቶን ጨምሮ; በ4 ኪሎ 5 ኪሎ 6 ኪሎ እስከ ቁስቋም ;ቸርቸር ጎዳናን ይዞ በሜክስኮ እስከ ረጲ; ሳሪስ  እና ወሎ ሰፈር ጎተራ እና ቄራ/ጎፋ....በሚል ተከፋፍሎ የተመደበ ሲሆን አትኩሮት የሚደረግባቸው ሙስሊሞች እና የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት የሆኑ ወጣቶች ላይ እንደሆነ መረጃው ሲጠቁም የኔት ቻፌ ባለቤቶች እና ተቀጣሪዎቻቸውም በዚህ ስለላ ላይ እንደሚሳተፉ ታውቋል::

ስለዚህ እያንዳንዳችሁ ይህን ያነበባቹህ የሰማቹህ ሁሉ በሃገርቤትም ያላችሁ እና በውጪ የምትኖሩ መልእክቱን እንድታስተላልፉ እና ወገንን ከአፈና እና ከእስር እንድንታደግ የበኩላችንን አስታውጾ እናድርግ::
ተከታታይ መረጃዎችን እናስተላልፋለን::