ሕወሓት እንደፓርቲ-ግብጽ እንደሃገር-/ክፍል 2/


ግብጥ የሃገርዋን ጥቅም ለማስከበር የማትቆፍረው ጓድጓድ እንደማይኖር ወያኔ ሳይረዳው ቀርቶት ሳይሆን እንደአዲስ ለመንግስት ጋር ለመደራደር ያቀረበው ጥያቄ ተቀባይነት ቢያገኝም ።።።።።።።።።።።።።።።።።ካለፈው የቀጠለ
በአሁን ሰኣት በወያኔ ውስጥ እየተከሰተ ያለውን መከፋፈል እኛ ኢትዮጵያውያን ብቻ ሳንሆን የተለያዩ መንግስታት ለብሄራዊ ትቅሞቻቸው ሲሉ በአንክሮ እየተከታተሉት ነው:: አሜሪካ በምስራቅ አፍሪካ እንደ ኢትዮጵያ አይነት ጠንካራ አጋር እንደማታገኝ ስለምታውቀው ብሄራዊ ጥቅሟን ለማስጠበቅ ስትል የአባይ ተፋሰስ አገሮችን ታሾራቸዋለች:: ወያኔ ስንል በዚህ ጹሁፍ የሚወክለው ሕወሓትን ነው:: አዎ ወያኔ በውስጡ የተነሳው ቁርሾ  ለኢትዮጵያ ጥቅም በማያስቡ ሰዎች መካከል የሚደረግ የበላይነት ሽኩቻ ስለሆነ ለእኛ ያለው እደምታ ይህን ያህል ወሬ ከማሟሟቅ በተረፈ ወያኔ ሊወገድ የሚችለው በጦርነት ብቻ እንደሆነ ግብጽ ሳትቀር የደመደመችው ጉዳይ ስለሆነ ወያኔን የምትይዝበትን ነገር ብቻ ነው እያሳሰባት ያለው ወያኔን ከተቆጣጠረች ሌላው ምንም እንደማያመጣ በቂ መረጃ ስላላት ፓርቲውን እንደሃገር እንዲደራደራት አድርጋለች እያደረገችም ነው:; በመንግስት ስልጣን ላይ ያሉ የኢሕኣዴግ ባለስልጣናት ያላቸው መረጃ የዲፕሎማሲ እንጂ እየተሰራ ያለ አጀንዳ ምን እንደሆነ አያውቁትም::

በተለያየ ጊዜ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት የኢሕኣዴግ  አዳዲስ ምሁራን አባላቱ ከግብጽ ጋር ያለውን ግንኙነት በተመለከተ ማብራሪያ አመራራቸን እንደጠየቁ ይታወቃል ሆኖም በደፈናው ዲፕሎማሲያዊ መልስ ማግኘታቸው አላረካቸውም ነበር በአሁኑ ወቅት እየተደረገ ያለው የሙስሊም ወገኖቻችንን ጥያቄ ማብራሪያውን አስታከው ከግብጽ ጋር ሊያያይዙት የሚዳክሩት ወያኔዎች በሳምንት ሁለት ጊዜ ወደ ካይሮ የደህንነት ቢሮ እየበረሩ ከግብጽ የደህንነት ባለስልጣናት ገር እየተደራደሩ እንደሆነ የምናውቀው ጉዳይ ነው;ግብጽ በሃገራችን የምታዘው መንግስት እንዲመሰረትላት በተለያየ ጊዜ አሜሪካንን የጠየቀች መሆኗ እንደተጠበቀ ሆኖ የአረብ አገራት ኢትዮጵያን በተመለከተ የምታስተላልፍላቸው መልእክት በኢትዮጵያ እና በኢትዮጵያውያን ላይ ሃይማኖት ዘር ቀለም ሳይለዩ ከፍተኛ ጥላቻ እንዲያደርጉ እያበረታታች ነው:;ለዚሁም በቅርቡ አንድ የሳኡዲ ሉል የተናገሩት በቂ ማስረጃ ሲሆን ግብጥ ይህን እያደረገች ያለችው ተሰሚነት ያላቸውን የአረብ መንግስታት በመጠቀም ሽብር እንዲያራግቡላት እንጂ::
http://www.unwater.org/የመንግስታቱን ማህበር የውሃ ኮንቬ. በፊርማዋ ያላጸደቀችው ኢትዮጵያ እንዲፈርም ለወያኔ ቢነገረውም ከግብጽ መንግስት የሚደረግበት ጫና እንዳይፈርም ሲያደርገው የራሳችንን መፍትሄ እንዳናበጅ ሃገራችንን ወያኔ ጠፍኖግ ይዟታል::በየወቅቱ ለግብጽ የሚሸጡ ሃገራዊ የምስጢር ዶክመንቶች ወያኔን ድንጋጠ ውስጥ የከተተው ሲሆን ግብጦች የተለያዩ የወያኔ ሰዎችን በገንዘብ በመግዛት ራሳቸውን እንዲሰልሉ እያደረገ እንደሆን በቅርብ ግዜ የደህንነት ሃላፊው አቶ ኢሳያስ ወልደጊዮርጊስ ሲናገሩ እና በአየር መንገድ በኩል ወደ ካይሮ በሚደረገው በረራ የሃገሪቱን የውሃ  እና የመከላከያ እቅዶች የያዙ መረጃዎች ሲወጡ መያዛቸውን ጠቅሰው የውስጥ አዋቂ ምንጮች ይናገራሉ::ይህን ተከትሎ አሁንም ግብጽ የፖለቲካ ማጭበርበር ከወያኔዎች ቅጥረኞቿ ጋር በመሆን እየፈጸመች ነው::
ግብጽ በኢትዮጵያ ያለን የሙስሊም እንቅስቃሴ ትደግፋለች የሚለው ወያኔ ይህንን በይፋ ለአባላቶቹ ያወጀ ሲሆን በአሁን ሰአት ያለውን የአባላቶቹን የውስጥ ጥያቄ በዚህም ለመሸፈን እየሞከረ እንደሆን ሲታወቅ ግብጽ የራስዋን አይነት አስተዳደር በኢትዮጵያ ላይ ለመጫን ትፈልጋለች የሚለውን አቋም ራሱ ያመጣው ችግር መሆኑ እየታወቀ በሙስሊሙ ጥያቄዎች ዙሪያ ሊላክከው ስለፈለገ ራሱን ለመደበቅ መፈለጉ አጋልጦታል::ወያኔ ከግብጽ ባለስልጣናት ጋር በተለያየ ጊዜያት ህዝብ በማያውቀው ሁኔታ እየተነጋገረ እየተደራደረ ሲሆን ይህም ሊያዛልቀው ባለመቻሉ በራሱ ላይ ሞት እያፋጠነ መሆኑን ሊረዳው ይገባል::ብሄራዊ ጥቅማችንን በገንዝብ እየተሸጠ ስለሆነ ልናውቀው የሚገባን ጉዳይ ነው::ከራሱ ላይ ያለበትን የህዝብ ደም እና እዳ ለማራገፍ ወያኔ እስካሁን መሰልጠን አለመቻሉ ከተጠያቂነት አያድነውም::
የኢትዮጵያ ሙስሊም ወገኖቻችንን ጥያቄ ወደ ግብጽ መውሰድ አሁንም  በውስጡ ያለውን ቅራኔ እና በአባል ድርጅቶች መካከል ሙስሊሙን በተመለከተ የሚጠየቁ ማብራሪያዎችን ለመድፈን እየተደረገ ያለ ሙከራ እንደማያዋጣ ደግመን ልንነግረው እንወዳለን:: የውጭ መንግስታት እርዳታ ሙስሊሞችን እያበረታታ ነው ከጀርባ የግብጽ እስላማዊ መንግስት እና አንዳንድ እስላማዊ ምሁራን አሉ በማለት የአባይን ግድብ ላይ ያለውን ደካማነት ለመሸፈን ግብጽን እወነጅላለሁ ባለበት አንደበት ከፖለቲካ ቋንቋ ተሳስሮ የራሱን ዜጎች መከራ እና የግፍ እጽዋ እንዲጎነጩ እያደረገ ያለው ወያኔ አሁንም መለስ ብሎ እያንዳንዱን ጉዳይ ሊያጠናው እና ሊያስተካክለው ይገባል::
እየሰራ ያለው ስራ ለስልጣን ማራዘሚያው መሆኑ ስለሚታወቅ ደም መፋሰሶች ሳይከተሉ በፊት ለኢትዮጵያ ህዝብ ስልጣን ማስረከብ አለበት::
የመጨረሻው ክፍል ሰፋ ብሎ የደህንነት ምስጢራቱን ይዞ ይቀጥላል::