የወያኔ መንግስት የአልጀዚራን ድህረገጾች ዘጋቸው!!!


የወያኔ መንግስትየአልጀዚራም ድህረገጾች ዘጋቸው!!!አልጀዚራ የአረቢኛው እና እንግሊዘኛው ድህረገጾች መዘጋታቸው የወያኔ መንግስት ከፍርሃት በመነጨ በሚዲያዎች ላይ እየወሰደ ያለው እርምጃ አካል መሆኑን ድህረ ገጾቹ አስታወቁ::የወያኔ መንግስት ባለስልጣናት አስተያየታቸን ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆኑም:: ዝርዝሩን ያንብቡት::

Al Jazeera’s English and Arabic websites are reported to have been blocked in Ethiopia, raising fresh fears that the government is continuing its efforts to silence the media.
Though the authorities in Addis Ababa have refused to comment on the reported censorship, Google Analytics data accessed by Al Jazeera shows that traffic from Ethiopia to the English website had plummeted from 50,000 hits in July 2012 to just 114 in September.

Traffic data revealed a similar drop for the Arabic website, with visits to the site dropping to 2 in September from 5,371 in July.
A blogger, who cannot be identified for his own safety, said Ethiopian censors had been targeting Al Jazeera since the Qatar-based network began airing coverage of ongoing protests against the way in which spiritual leaders are elected in the Horn of African nation.
The steep decline in web traffic began on August 2 last year, the same day that Al Jazeera Mubasher aired a forum with guests denouncing the government's "interference" with Muslim religious affairs, and three days after Al Jazeera English published an article detailing deadly ethnic clashes between two of the country's southern tribes.
Attempts by Al Jazeera to get an official response from authorities failed.

ድምፃችን ይሰማ
አልጀዚራ እንግሊዝኛና አረብኛ ድረ ገጾቹ በኢትዮጵያ እንዳይታዩ መታቀባቸውን ገለጸ
የእቀባው ምክንያት የሙስሊሞችን ተቃውሞ በመዘገቡ እንደሆነ ተገልጿል

የሙስሊሞች ጉዳይን ሽፋን በመስጠታቸው የሚታፈኑ ሚዲያዎች ቁጥር አሻቅበዋል

መሰረቱን ኳታር ዋና ከተማ ደውሐ ያደረገው የአልጀዚራአለም አቀፍ የቴሌቪዥን ጣቢያ የሁለቱም ቋንቋ ድረ ገጾቹ በኢትዮጵያ እንዳይታዩ መታገዳቸውን ገለጸ፡፡ ጣቢያው ከኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት በጉዳዩ ዙሪያ ምልላሽ ለማግኘት ጥረት በያደርግም እንዳልተሳካለት ገልጾ እርምጃው ሚዲያዎችን የማፈን ቀጣይ እርምጃ አካል እንደሆነ አስገንዝቧል፡፡ ጣቢያው ባለሙያዎችን አነጋግሮ ባጠናከረው ዘገባ የጣቢያው ድረ ገጾች ዋነኛ መታፈን ምክንያት ቴሌቪዥን ጣቢያው የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ተቃውሞ በመዘገቡ ምክንያት አንደሆነ ተናግሯል፡፡ ድርጅቱ የጎግልን የመረጃ ትንተና ግራፍን በእማኝነት አቅርቦ ባወጣው በዚሁ ዘገባ የእንግሊዝኛው ድረ ገጽ ባለፈው አመት ሀምሌ ወር ከነበረው 50ሺ ተጠቃሚ ትራፊክ በመስከረም ወር ወደ 114 ወርዷል፡፡ የአረቢኛው ድረ ገጽም ከ5,371 ወደ 2 ዝቅ ብሏል፡፡

እንደጣቢያው የጎግል የትራፈክ ትንተና የድረ ገጹ ትራፊክ ዝቅ ማለት የጀመረው ባለፈው አመት ነሀሴ ወር የአልጀዚራ ሙባሸር ጣቢያ በኢትዮጵያ የመንግስት የሃይማኖት ጣልቃ ገብነትን አስመልክቶ የተዘጋጀ ፎረም ካሰራጨ እለት ጀምሮ ሲሆን ከዚያ ቀጥሎም የአረብኛ ጣቢያው የአርብ ተቃውሞዎችን ማሰራጨቱ የድረ ገጹ አፈና ለሁለቱም ቋንቋዎች እንዲደርሳቸው ምክንያት ሆኗል::

መንግስት የሙስሊሞችን ብሶትና ተቃውሞ የሚዘግቡ በሀገር ውስጥም በውጪም የሚገኙ ሚዲያዎችን ሲዘጋ መቆየቱ የሚታወስ ሲሆን በአገር ቤት ሰለፊያ እና ሰውቱል ኢስላም ጋዜጦችን፤ ከመጽሄት የሙስሊሞች ጉዳይ፣ አል ኢስላም እና መርየምን መዝጋቱ ይታወሳል፡፡ እነዚህ ሁሉ እትሞች የተዘጉት ባለፈው አመት ሀምሌ 13 ሲሆን በሙስሊሞች ጉደይ ሰፊ ሽፋን ሲሰጥ የነበረው ፍትህ ጋዜጣም ኮሚቴዎቻችን ከመታሰራቸው ከጥቂት ሰአታት በፊት የሰጡትን ልዩ ቃለ መጠይቅ አትሞ ይዞ ሊወጣ ሲል በዚያው እለት ሀምሌ 13 በመንግስት መታፈኑ ይታወቃል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ታዋቂው ኦንኢስላም ድረገጽ ከዚሁ ተቃውሞ ዘገባው ጋርተያያዞ በኢትዮጵያ እንዳይታይ መደረጉ የቅርብ ጊዜ ትዝታችን ነው፡፡

ድንበር የለሹ የጋዜጠኞች ቡድን ባወጣው የሚዲያ ነጻነት ጠቋሚ ኢትዮጵያ ከ179 አገሮች 137ኛ ደረጃን አግኝታለች፡፡ እነደቡድኑ ሪፖርት የጸረ ሽብር ሕጉ ሚዲያዎችን ለማፈንና ጋዜጠኞችን ለማሰር ሁነኛ መሳሪያ ሆኖ እያገለገለ ነው፡፡ የጋዜጠኖች መብት ተሟጋቺ ሲፒጄ የምስራቅ አፍሪካ ቢሮ ተጠሪ ቶም ሩድስ የጸረ ሽብር ሕጉ ሕገ ወጥ ከመሆኑም በላይ ተቃውሞ የሚያነሱን ሁሉ ለመቅጫነት ተግባር እየዋለ ነው ይላሉ፡፡ ጨምረውም ‹‹አሁን ደግሞ የጸረ ሽብር ህጉ መንፈሳዊ መሪዎቻቸውን ለመምረጥ በሰላማዊ መንገድ መብታቸውን ለማስከበር የሚታገሉ ሙስሊሞችን ለመወንጀል ጥቅም ላይ እየዋለ ነው›› በማለት የሁኔታውን አሳሳቢነት ያሳያሉ፡፡ የጸረ ሽብር ህጉ ሕገ መንግስቱንና አለም አቀፍ ሕግጋትን ይጻረራል በማለት ኮሚቴዎቻችን ሕጉ ላይ ጥያቄ አስነስተው በመንግስቱ ፍ/ቤት ውድቅ እንደተደረገባቸው የሚታወስ ነው፡፡

(በምስሉ ላይ የጎግል የትንታኔ ጠቋሚ በኢትዮጵያ የአልጀዚራ የእንግሊዝኛው ድረ ገጽ ትራፊክ በሀምሌ እና መስከረም መካከል ያለውን ለውጥ ያሳያል)


(በምስሉ ላይ የጎግል የትንታኔ ጠቋሚ በኢትዮጵያ የአልጀዚራ የእንግሊዝኛው ድረ ገጽ ትራፊክ በሀምሌ እና መስከረም መካከል ያለውን ለውጥ ያሳያል)


Attempts by Al Jazeera to get an official response from authorities failed.
Poor track record
Ethiopia is ranked 137 out of 179 surveyed nations on the latest Press Freedom Index of Reporters Without Borders (RSF), an international advocacy group for press rights.
Both RSF and the Committee to Protect Journalists (CPJ) have tied Ethiopia's deteriorating media environment, in part, to a 2009 anti-terrorism law that has been used to jail 11 journalists since its ratification.
"The usage and practice of this law is illegal. It has a clause that makes whoever writes about so-called terrorist groups, which are mostly normal opposition groups, a terrorist," CPJ's East Africa Consultant Thom Rhodes told Al Jazeera.
"Now it's got to the point that the law is being used to label those in the Muslim community conducting peaceful protests to defend their right to choose their spiritual leaders as terrorists. It's a sad state of affairs."
CPJ says Ethiopia is the second-highest jailer of journalists in Africa after neighbouring Eritrea, were seven journalists are currently detained.
Both the RSF and CPJ have expressed concern over reports that the country has begun using much more sophisticated online censorship systems over the last year, including ones that can identify specific internet protocols and block them.
Since Ethiopia's government owns the sole telecommunications provider in the country, Ethio Telecom, it allows authorities to tightly control internet freedom.