የመጨረሻው ደውል- የወያኔ ጸረ- አስልምና አጀንዳ ሲጋለጥ


ወያኔ አመለካከትን ለማቀጨጭና ለመግደል የሚጠቀማቸው ስትራቴጅዎች ሁለት ናቸው፡፡የመጀመሪያው ስልጣኑን በመጠቀም አደጋ ብሎ የፈረጀውን አመለካከት እንትን የነካ እንጨት አድርጎ ማቅረብ፡፡በመገናኛ ብዙሀንም ሆነ በተለያዩ መድረኮች ሰፊ የፕሮፓጋንዳ ስራ በመስራትና በጥቅም በመደለል ወያኔያዊ ስርዓትን መለኮታዊ አድርጎ ያንኛውን ደግሞ ሰይጣናዊ አድርጎ ጥንብ እርኩሱን ማውጣት ነው፡፡ይህን በፓለቲከኞቹ፣በካቢኔዎቹ፣በቡችሎቹ በሁሉም እስኪሰለችህ ድረስ ያስዘፍንብሃል፡፡ከዚያም አለፍ ብሎ ይህን ለችግር ቀን ብሎ በየቀበሌው በተለያየ ስም ባደራጃቸው የስርዓቱ ፍርፋሪ አጋሳሽ ጀሌዎቸ “ከህዝቡ በተሰበሰበ” አስተያየት ብሎ ማታ ማታ በኢቲቪ ይግትህና የህዝብም አቋም ነው ይልሃል።በዚህች አካሔዱ ተዝቆ የማያልቅ የፓለቲካ ትርፍ አጋብሶባታል።

  አመለካከት-በእርግጥም ሩቅ ነው።ታዲያማ ይህ አመለካከት በኢህአዴግ ቤት ሰፊ መቼት ይሠጠዋል።የኢህአዴግ መድረኮች የ”አመለካከትን” ስም ሳይጠሩ አይጀመሩም አይቋጩምም፡፡በኢህአዴግ ቤት ከ1ለ5ና ህዋስ እስከ መዓከላዊ ኮሚቴ ያሉ የአደረጃጀት መድረኮች በሙሉ የዚህች ቃል ሰገነት ናቸው፡፡ከጠ/ሚኒስቴር እስከ ታችኛው እርከን ያሉ አባላት ይደጋግሟታል፤ያነሷታል ይጥሏታል፣ይገማገሙባታል፣ይጨቃጨቁባታል፣ሌክቸር ይደራረጉባታል፣ኢህአዴግኛ ይማሩባታል።ይህች ቃል ለኢህአዴግ ጥልቅ ናት፡፡የኢህአዴግ መድረኮች የግምገማ ነጥቦች ከዚህ ቃል የተራቡ ናቸው፡፡ ግን ለምን? ለምንስ ይሆን የዚህን ያክል ክብደት የሚሰጧት?
አመለካከት ላይ ኢህአዴግ አይደራደርም! ከሱ መስመር ውጭ ያለን ሁሉ “የአመለካከት ችግር አለበት” ብሎ መፈረጁም አይደለም ክፋቱ ከኢህአዴግኛ አመለካከት ውጭ ያለን ወይም ከኔ አመለካከት ውጭ ያለ በሙሉ ፀረ-ህዝብ፣ፀረ-እድገት፣ፀረ-ህገመንግስት ነው የሚል ጠርዘኛ አመለካከት ላይ የበቀለ ድርጅት መሆኑ ላይ ችግሩ፡፡በመሆኑም ኢህአዴግ አደገኛ አመለካከት ያለውን ለማጥፋት የማይፈነቅለው ድንጋይ አይኖርም።ኢህአዴግ ይህ ነው -በቃ። ”አቢዮታዊ ዴሞክራሲያዊ” ከተሰኘው ወያኔያዊ ሽፋን ውጭ ያለ አስተሳሰብ በሙሉ፣ከወያኔያዊ አምልኮ ውጭ ያለ አምልኮ በሙሉ በአመለካከት ችግር ተበይኖና ተጠርንፎ ለውድቀቱና ለውድመቱ ኢህአዴጋዊ ሀረካት ይታቀድበታል፡፡ኢህአዴግ ቢሮ ውስጥ አንድ ባንክ ብትዘርፍም ወይም የቢሊዮን ዶላር ሙስኛ ብትሆንም እንኳን አመለካከትህ ኢህ-አዴጋዊ ከሆነ ችግር የለውም፡፡በተቃራኒው ደግሞ እንደ አቶ ጁነዲን ሐይማኖትህን እንኳን ክደህ ባሪያ ብትሆነው ኢህአዴግ የአመለካከት ችግር አለብህ ብሎ ካመነብህ ፍፃሜህ ዘብጥያ አሊያም ስደት ይሆናል፡፡ ስለ ኢህአዴግ አቋም ማውጋት አይደለም ነጥቤ ኢህአዴግ “የእስልምና አመለካከት” ስለሚለው ተረኛ አጀንዳ እንጅ!! አዎ! ኢስላም ለኢህአዴጎች አመለካከት ነው-ከኢህአዴግ ውጭ ያለ አመለካከት! ኢህአዴግ ኢስላምን የሚመለከተው እንደ ሐይማኖት ሳይሆን እንደ አመለካከት ነው!! ከወያኔና ከልጁ ከኢህአዴግ ጽንሰ-ሃሳብ ጋር የማይገጣጠም። ይህን ኢህአዴግ ጠንቅቆ ያውቃል! ጠንቅቆም ተረድቷል።
ወያኔ አመለካከትን ለማቀጨጭና ለመግደል የሚጠቀማቸው ስትራቴጅዎች ሁለት ናቸው፡፡የመጀመሪያው ስልጣኑን በመጠቀም አደጋ ብሎ የፈረጀውን አመለካከት እንትን የነካ እንጨት አድርጎ ማቅረብ፡፡በመገናኛ ብዙሀንም ሆነ በተለያዩ መድረኮች ሰፊ የፕሮፓጋንዳ ስራ በመስራትና በጥቅም በመደለል ወያኔያዊ ስርዓትን መለኮታዊ አድርጎ ያንኛውን ደግሞ ሰይጣናዊ አድርጎ ጥንብ እርኩሱን ማውጣት ነው፡፡ይህን በፓለቲከኞቹ፣በካቢኔዎቹ፣በቡችሎቹ በሁሉም እስኪሰለችህ ድረስ ያስዘፍንብሃል፡፡ከዚያም አለፍ ብሎ ይህን ለችግር ቀን ብሎ በየቀበሌው በተለያየ ስም ባደራጃቸው የስርዓቱ ፍርፋሪ አጋሳሽ ጀሌዎቸ “ከህዝቡ በተሰበሰበ” አስተያየት ብሎ ማታ ማታ በኢቲቪ ይግትህና የህዝብም አቋም ነው ይልሃል።በዚህች አካሔዱ ተዝቆ የማያልቅ የፓለቲካ ትርፍ አጋብሶባታል።
ሁለተኛው ስትራቴጅው ደግሞ የአመለካከቱ አቀንቃኞች ናቸው ብሎ ያሰባቸውን የአመለካከቱ ምሁራንን ማሳደድና ማወክ አለፍ ሲልም ማሰር ማሰቃየትና መግደል ነው።ይህን ከደደቢት እስከ ዛሬ ድረስ ተጠቅሞበታል እየተጠቀመበትም ይገኛል፡፡ይህን የሚያደርግበት ዋነኛው ምክንያትም የአንድን አስተሳሰብ ወይም አመለካከት አቢይ አቀንቃኞችና የአመለካከቱ ምሁራኖችን በማጥፋት አመለካከቱን ከተቻለ ማጥፋት ካልተቻለም መልሶ እንዳይቃና በማድረግ ሽባና ልፍስፍስ ማድረግ ይቻላል የሚል የተንጋደደ ፍልስፍናና ፅኑ እምነት ላይ የተመሰረተ ድርጅት በመሆኑ ነው፡፡ወያኔ የራሱን ልጅ እየበላ የመጣና በልጆቹ ስጋ የደለበ ጋኔን ነው፡፡የሙሴም ግድያ ሆነ የሀውዜን ጭፍጨፋ ከወያኔ ቁማሮች ትቂቶቹ እንደሆኑ መረጃዎች ያሳያሉ።
ወያኔ-ኢህአዴግ ታዲያም እንዳልኳችሁ በዚህ ናዚያዊ ቅኝቱ የረጅም ጊዜን ተሞክሮን በማዳበሩ በስተመጨረሻ በኢስላም ላይ የለየለት ጦርነት አውጀና አረፈው። ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ጦርነቱ በእነሱ ላይ እንደሆነ በየዋህነት ይረዳሉ ግና እውነታው ይህ አይደለም፡፡ወያኔ የአሜሪካዊ ዲሞክራትን ወይም ሪፐብሊካን ቢሆን ኖሮ በዓለም ላይ የኢሰላም ስም እንዳይነሳ ለማድረግ የማይጠረው ጥረት አይኖርም ነበር፡፡እያካበድኩም፣እያሳቀልኩም አይደለ እጅህ ከምን ካላችሁ እንሆ በእጅና በኪሴ ሙሉ መረጃ ፡
1. የኢስላም ምሁራኖችን እያሰቃየ፣ በአሸባሪነት እየከሰሰና እያሰረ የቻለውንም እየገደለና እያሳደደ ይገኛል፡፡ ይህንንም የሚያደርገው ግለሰቦቹን ለማሰር ወይም ለመግደል አይደለም የያዙትን ኢስላማዊ እውቀት ለመገደብና ለማሰር ከቻለም ይዘውት እንዲሰደዱና እንዲገደሉ በማድረግ ኢስላምን መገደብ በሱ ቋንቋ አመለካከቱን ማጥፋት ወይም ሺባ ማድረግ ይቻለል ብሎ በማመኑ ነው፡፡
2. ኢስላማዊ ሚዲያዎችና ሀይማኖታዊ መፅሀፍቶችም ታርጌቶቹ ናቸው፡፡ቁርዓንን በሌሊት ከሙስሊሞች ቤት በሽፍቶቹ አማካኝነት ለመስብሰብና ስርጭቱን ለመቀነስ ያደረገውም መፈራገጥ የዚሁ አስተሳሰብ ውላጅ ተግባር ነው፡፡ቁርዓንን ለማጥፋት ከተሞከሩ የታሪካችን ትቂት ሙከራዎች የወያኔ ሙከራ አንዱ ነው፡፡
3. ኮሚቴዎቹ ከተከሰሱባቸው በርካታ የክስ ነጥቦች በርካቶቹ ቁርዓናዊ ወይም ሀድሳዊ ንግግሮችና ጭብጦች ናቸው፡፡ይህም አክራሪ ወይም አሸባሪ ማለት የፈለገው ዲኑን እንጅ ያስተጋቡትን ግለሰቦች አይደለም፡፡
4. ለዋነኛው ሸህ ይልቅ ለድቢ አንጋች ሙሪዱ ክብርና ሞገስን እየሰጠ መሐይማንንና ሸህ-ሞገሴዎችን እየሰበሰበ በሸሆቹ ላይ ፈትዋ በማሰጠት ሸህየውን ወደ ዘብጢያ የሚያወርደው ሸህየው የያዙትን እውቀት ከመጥላትና ለማጥፋት እንጅ ግለሰቦቹማ ግለሰብ ናቸው፡፡
5. ሙስሊም ምሁራን በተለይም በሟች ጠ/ሚኒስቴሩ ቋንቋ “የነቁት” አደገኛ የወያኔ ጠላት ሙስሊሞች ናቸው፡፡ለምን? ኢስላምን (በእሱ ቋንቋ አመለካከቱን) ጠንቀቀው ስለሚያውቁ፡፡ኢህአዴግ ጃሂልን ወይም ማሐይማንን ይሾማል ያሞግሳል እንጅ በአንድ ዓመት የትግል ታሪክ ማሃይማን በስህተት ተቀላቅለው እንጅ በኢህአዴግ ክፉ ዓይን አልታዩም፣አልታሰሩም፣አልተገደሉም…
6. በአንድ በኩል ሙስሊሙ ሀይማኖቱን ሲያውቅ አክራሪነትን ያወግዛል የሚል ሽፋን እየሰጠ ፀረ-እውቀት እንቅስቃሴውን በማጠናከር መርከዞችን፣መድረሳዎችን፣ኢስላማዊ አብያተ-መፃህፍትንና የእወቀት ማህበራትን እንደ አይ አር ሲ ሲ(IRCC) ያሉትን ደግሞ ያሽጋል፣ይከረችማል፡፡
ከላይ ኢህአዴግ ከደደቢት እስከ ቤተ-መንግስት ጸረ-ኢህአዴግ ተብሎ የፈረጀውን አመለካከት ለመምታት የተጠቀመባቸው ስትራቴጅዎች በሙሉ ሁሉንም ተግባራዊ እያደረጋቸው ይገኛል፡፡ ይህን ሁሉ ያልኩትን ከዚህ በፊት የወያኔ አባል ሆኖ የሚያውቅና አሁንም የሆነ ካለ ጠንቅቆ የሚያውቀውን ያውቀዋል፣አመለካከትን በየ ግምገማው ስላሰለቸችው ይረዳታልማል፡፡ለዚህም ነው “ኢስላማዊ አመለካከት” ላይ ኢህአዴግ የሞት የሽረት ትግሉን የሚያደርገው
;ኢብኑ ተይሚያህ አልሀበሽ፡፡