የመጨረሻው ደውል- የኢህኣዴግ ካድሬዎች ሃይማኖትን በተመለከተ ማብራሪያ መጠየቃቸው ተሰማ::

የኢህኣዴግ ካድሬዎች ሃይማኖትን በተመለከተ እየተወሰደ ያለው እርምጃ በግልጽ ማብራሪያ እንዲሰጣቸው ከፍተኛ አመራሩን መጠየቃቸው ተሰማ::ከባህር ዳሩ ጉባዬ በፊት የተሰበሰቡ መረጃዎች እንደሚያሳዩት የወያኔ ካድሬዎች በእስልምና እና በኦርቶዶስ ሃይማኖቶች ዙሪያ ያለውን ጣልቃ ገብነት እና እየተወሰደ ያለውን እርምጃ በማስመልከት አጀንዳ እንዲያዝላቸው እና መፍትሄ ሊያመጣ የሚችል ውይይት እንዲያደርጉ እና ከመደምደሚያ እንዲደረስ አስፈላጊው ዝግጅት መደረግ አለብት ሲሉ ለነገ መዘዝ እንዳያስከትልብን በሚል መጠቆማቸን የምንሊክ ሳልሳዊ ምንጮች ከኢህኣዴግ ጽ/ቤት የተገኘውን መረጃ ጠቅሰው ተናግረዋል::

ካድሬዎቹ እንደገለጡት ሳይታሰብበት በከፍተኛ አመራሮች እየተሰራ ያለው ስራ ለራሳችን ለቤተሰባችን እንዲሁም (ለሃገራችን?)የማያባራ መዘዝ ነው ሲሉ ተሰሚነት ያማያገኙ ከሆነ ድርጅቱ እንዲያሰናብታቸው የጠየቁ ካድሬዎች እንደሚገኙበት ዘገባው ያስረዳል::
የእስልምና እምነት ተከታዮች ጥያቄያችን ግልጽ ነው እያሉ ከመንግስት መገናኛ ብዙሃን የምንሰማው አደገኛ ፕሮፓጋንዳ እና ጥቂት ካድሬዎቻችንን በመጠቀም የበላይ አካሎች እየሰሩ ያለው ጉዳይ እንደአባልነታችን ሊነገረን ይገባል ሲሉ በምሬት ገልጸዋል::እኛ ያሉት ካድሬዎች እንደ ፓርቲ አባልነታችን መረጃ ሊሰጠን እና በተገባልን ቃል መሰረት አስተያየት ልንሰጥበት ሲገባ ማንኛውንም ነገር የምንሰማው አባል እንዳልሆኑት ህዝቦች ከቤታችን ቁጭ ብለን ከመንግስት መገናኛ ብዙሃን ነው ብለዋል::

የሙስሊሙን ጉዳይ በተመለከተ ከሃገር ቤት በተጨማሪ በአለም አቀፍ ደረጃ ተቃውሞው እየጨመረ የመጣ ሲሆን ከዚህ ቀደም በኢቲቢ የቀረበው ጀሃዳዊ ሃራካት የታሰሩት ግለሰቦች እና ፊልሙ የማይገናኝ ሲሆን የእስረኞችን ነጻነት ያረጋገጠ ስለሆነ አንድ ነገር ከመሰራቱ በፊት ሊታሰብበት ይገባል ብለዋል::ስለዚህ ፓርቲያችን መለስ ብሎ ሊያስብበት እና ከገባንበት ሁኔታዎች የምንወጣበትን መንገድ ማመቻቸት አለበት ብለዋል::
በሙስሊም ባለስልጣናት ላይ አየተደረገ ያለው ተጽእኖ ከጅምሩ ሊቆም ይገባዋል ያሉት ካድሬዎቹ    የህዝብ አቤቱታዎች ችላ የሚባሉ ከሆነ ከገባንበት አጣብቂኝ ሳንወጣ ሌላ ገደል ውስጥ ገብተን መውጫ መንገድ እንዳናጣ ሲሉ ይናገራሉ::
እንዲሁም የኦርቶዶክስ ሃይማኖትን በተመለከት የበላይ አመራሮች እየሰሩ ያለውን ስራ ከተለያዩ መገናኛ ብዙሃን እየሰማን ነው ያሉት ካድረዎቹ ጳጳሳቱን በእደዚህ አይነት ሁኔታ ህዝብ አፍ ውስጥ መክተት ነገን ከተጠያቂነት እንደማያድናቸው እና ዝም ያለ ህዝብ... በማለት የ97 ምርጫን አስታውሰው መናገራቸውንየተሰበሰቡ መረጃዎች ጠቁመዋል:; የፓርቲው አመራሮች በበተክርስቲያን ዙርያ እየደረጉ ያሉት እንቅስቃሴዎች ሊገለጥልን ይገባልም ብለዋል:: እነዚህን እና ሌሎች ጉዳዮች ያሉበትን የተሰበሰበ የመረጃ ሪፖርት ለአመራሩ ቀርቧል:: በደህንነቶች እና በፓርቲው የስለላ መዋቅር እንዲሁ ጥናት እየተደረገ መሆኑን የጽ/ቤቱ ምንጮች ጠቅሰዋል::... ሌሎች ጉዳዮችንም ሪፖርቱ አስቀምጧል:: ዝርዝሩ ይቀጥላል::