በነጻ ፕሬስ ስም የተጀመረ ጸረ እስልምና ዘመቻ

በመንግስት አይዞህ ባይነት እየትልፈሰፈሰ በድጎማ ገበያ ላይ ያለው የ”ሎሚ” መጽሔት አደርባዮች በቅርቡ እትማቸው የሙስሊሙን ያልጻረ ቁስል እና ያልተመለሰ ጥያቄ ለመበረዝ ከጌቶቻቸው በታዘዙት መሰረት በመጽሄቷ ጎላ አድርገው “የኢትዮ ሳኡዲ የፖለቲካ ውጥረት የተድበሰበሱ እውነታዎች ” በማለት በአንድ ርእስ ስር ሃይማኖታዊ የፖለቲካ ትንታኔ የሰጡ በማስመሰል ሙስሊሙን ህብረተሰብ ሊወነጅሉ ሲፈልጉ ይታያል:: እስልማዊ መንግስት ለመመስረት የምትለዋን ወያኔያዊ ነጠላ ዜማ የለቀቁልን ልማታዊ(ሽብራዊ) ጋዜጠኞች ምንም ጭብት ያሌለው መርዛቸውን መርጨት ቢፈልጉም እንደማይሳካላቸው ከወዲሁ ሊረዱት ይገባል::ምንሊክሳልሳዊ
እነዚህ አደርባዮች በነጻ ፕሬስ ስም የሙስሊሙን አለም እና ኢትዮጵያዊውን ሙስሊም በአሸባሪነት ለመፈረጅ የተጠቀሙበት ዘዴ እና ስልት የሳኡዲ ልኡል በግብጽ ያደረጉትን ንግግር ተመርኩዘው ለመተቸት ዳድቷቸዋል:: የማይገደበው እና የፖለቲካ ፍጆታ ማሟያ/የስልጣን ማስረዘሚያ/ የሆነው የህዳሴ ግድባቸውን ምስጢራ ያልተረዱት ሎሚዎች ብስባሽ መሆናቸውን አሳይተውናል::ምንሊክሳልሳዊ
የተጣሉ ጋዜጠኞች ሰብስበው በድጎማ የሚያሰሩት የበረከት ሹባሾች “የህዳሴው ግድብ;የምስኪድ እርዳታ የጁነዲን ስደት;ዉሃቢዬ አልአህበሽ የባለስልታኑ ዛቻ ” በሚል ንኡስ ርእስ የሙስሊም ህብረተሰብ በሳኡዲ አረቢያ እርዳታ መስኪዶችን በመስራት ስም አክራሪነትን እና አሸባሪነትን እያስፋፋ እንደሆነ እና አደጋ እንደሆነ በዉስጠ ወይራ ሊነግሩን ይፈልጋሉ:: እ4ንዚህ የመንግስት ሆድ አደር ማህበራት ሰዎች የሙስሊሙ ጥያቄ ግልጽ እና ግልጽ ሆኖ እያለ ስለ መስኪድ እርዳት ምን አመጣው የሳኡዲ እርዳታም ሆነ መስኪድ መገንባት ዛሬ በወያኔ አልተጀመረም:: ሙስሊሙ ህብረተስብ መስኪዴን እገነባለሁ እርዳታ ይፈልጋል ሳይሆን ያለው መጅሊሱን እኛው እንምረጥ መንግስት እጁን ያውጣልን ነው;መስኪዳችንን ከአሕበሾች እንከላከል ነው ያለው:: ማንም አብሮ የኖረበትን እምነት ከራሱ ፍቃድ ዉጭ ሌላ ሃራጥቃ መቶ ሊያስጥለው አይችልም:: ሱሬውንም አሳጠረ ጺሙንም አስረዘመ ኢትዮጵያዊ ሙስሊም የማንንም መብት ያልነካ ታላቅ አማኝ ነው:: ሱሬ ባሳጠረ ጀለቢያ በለበሰ ጺም ባስረዘመ ከሆነ የሌሎች እምነት የሃይማኖት መሪዎችም አሸባሪ ናቸው ማለት ነው:: የወያኔ ጁንታ ለራሱ የስልጣን እድሜ ጊዜ መግዣ እርስ በርስ በማባላት የማይፈልገውን ቡድን ለማፈን እና ለማሰር የሚጠቀምበት ዘዴ እንጂ ኢትዮጵያዊ ሙስሊም አሸባሪ የለም!! እደግመዋለሁ… ኢትዮጵያዊ ሙስሊም አሸባሪ የለም!!
በዚሁ መጽሄት ለላው ተጠቃሽ ሰው ባለቤቱን እስር ቤት ከቶ ሮጦ ያመለጠው ጁነዲን ነው:: ሎሚዎች ሳቶኑ ኮምጣጤዎች ልንነግራቹህ የምንፈልገው ነገር የዚህ ሰው ባለቤቱ የታሰረችበት እና የሙስሊሙ ጥያቄ የማይገናኝ አራባና ቆቦ መሆኑን ነው::ሴትዮይቱ ከሳኡዲ ኤምባሲ ገንዘብ ተቀብላ ስትወጣ ተያዘች ይሉናል አላየንም::ሚናልባት የሳኡዲ ዲፕሎማቶች በግል ለጁነዲን ሳዶ የ እናቱ ማስታወሻ መስኪድ ግንባታ ረድተውት ይሆናል እንጂ ኮሚቴዎቹ በርግጠኝነት ስለዚህ መስኪድም ሆነ ሌላ ወያኔያዊ ዝብርቅርቅ አያውቁም :: ወያኔ የህዝበ-ሙስሊሙን ጥያቄ መልሻለሁ ብሎ ካወጀ ጀምሮ መልሱ ያልተመለሰለት መላው ኢትጵያዊ ሙስሊም “ድምፃችን ይሰማ” በማለት በሰላማዊ ትግል መብቱን ለማስከበር በአደባባ ከወጣ ከዓመት በላይ ሆኖታል፡፡በዚህም በጣም የተደናገጠው እና የፈራው ወያኔ ሰላማዊ ትግሉን ለማኮላሸት
ያልፈነቀለው ድንጋይ ፤ያልቆፈረው ጉድጓድ የለም፡፡ኮሚቴዎቻቸውን ከማሰር አንስቶ ከሙስሊሙ ማህበረሰብ ፈቃድ ውጭ ምርጫ አካሂዷል፤የአንድነት እና የሰደቃ ፕሮግራሞችን እንዳይካሄዱ አግዷል፡፡ምንሊክሳልሳዊ
ኢቲቪ የተለያዩ ቅጥረኛ ሀባሾችን ሰብስቦ ውይይት በሚል ስም የህዝበ-ሙስሊሙን ሰላማዊ ትግል ጥላሸት ለመቀባት ጥፘል፡፡ከዚህም አልፎ በመላ ሀገሪቱ የሰላም ድምጽ በሚያሰማው ህዝብ ላይ የዱላ እና የጥይት ናዳ አውርዶበታል፡፡በዚህ ድርጊቱ በአሳሳ፣በሀረር፣ እንዲሁም በደሴ የንጹሀንን ህይወት ቀጥፏል፡፡ ይህ ሁሉ ጥረት ውጤት ያላስገኘለት ወያኔ ሌላ አማራጭ ብሎ የያዘው ሙስሊም ያልሆኑ ወገኖች ሙስሊሞችን በጥርጣሬ እንዲመለከቱ ማድረግ ነው፡፡”ሙስሊሞች አክራሪ በመሆን እስላማዊ መንግስት ሊያቋቁሙ ነው፣ክርስቲያኖችን ለማጥፋት እየሰሩ ነው”በማለት አደገኛ ፕሮፖጋንዳ በአደባባይ አሰራጭቷል፡፡ለዚህም ማረጋገጫ ከሚሆኑት መካከል በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን የተላለፈው “ጀሀዳዊ ሀረካት” የተሰኘው በሀሰት የተቀነባባረ ዘጋቢ ፊልም ይጠቀሳል፡፡ይህ ፊልም የወያኔ ጭካኔ የተሞላበት የእስረኞች አያያዝ እና የምርመራ ሂደት የተጋለጠበት እንዲሁም ፍርድ ቤቶች ለወያኔ ያላቸው ታዛዥነት እና በሀገሪቱ የህግ የበላይነት አለመኖሩ በግልጽ የታየበት ነው፡፡ የሙስሊሙ ጥያቄ ኮሚቴዎቻችን ይፈቱ ጥያቄያችን ይመለስ እንጂ በደም የታጠበው ጁነዲን ሙስና ወንጀል ኖሮበት የሸሸውን ሰው ከሙስሊሙ እና ከስኡዲ ጋር ማገናኘት የውሸት ዲስኩር ነው::
አህበሽ ሃራጥቃ በተመለከተ በተለያየ ጊዜ ሙስሊሙ ህብረተሰብ የተናገረው ጉዳይ ነው ይህን ያህል ባንልበትም ከቅዱስ ቁርኣን ትእዛዛት ውጭ ፈጣሪ እንደት ሊመለክ ይችላል?/ የአህበሽ ሰዎች አንዳንድ ሙስሊሞችን በጥቅም በመደለል እና የመንግስት ባለስልጣናት የሆኑ ጸረ እስልምና አቋም ያላቸው እንደ ሽፈራው ያሉ ግለሰቦች የወያኔን የበረሃ ግብ ለማስፈጸም እየሰሩ ነው :: የባለስልጣኑ ዛቻ በተመለከት ብዙ የተባለለት ስለሆነ መናገር አያስፈልግም:: አሁን የምታራግቡት የሙስሊሙን ጥያቄ ላለመመለስ የማይፈልገውን የጥቂቶች አምባገነን ጁንታ ዲስኩር መሆኑን አትዘንጉ በሙስሊሙ ጉዳይ ላይ እናንተም ሎሚ ነን የምትሉ እየቆመጠጣችሁ ያላችሁ ከተጠያቂነት አትድኑም::