የፓርቲዎቹ መሰባሰብ ለነፃነት ትግሉ ምን ይፈይድ ይሆን?

በዴሞክራሲያዊ መንገድ በሚደረግ ምርጫ ስልጣን እንይዛለን በሚል እምነት ከ70 የሚበልጡ ፓርቲዎች    በኢትዮጵያ ውስጥ ይንቀሳቀሳሉ፡፡ የፓርቲዎቹ ቁጥር መብዛት ለሀገራችን የነፃነት ጉዞ የሚፈቅደው ባይኖርም፣ የቁጥር መብዛቱ በራሱ የስርዓቱን አምባገነንነት የሚያሳይ ነው፡፡ አንዳንዶቹ ፓርቲዎች ስርዓቱ በሚከለተው ዘርን መሰረት ያደረገ ፖለቲካ  የሚወክሉት ብሔር መጨቆኑን በመግለፅ በየአካባቢው የተቋቋሙ ናቸው፡፡ ሌሎቹ ደግሞ ሰላማዊ ትግሉን ለማቀጨጭና የኢህአዴግ አምባገነናዊ ስርዓት እንዲቀጥል እንዲረዱ በስርዓቱ ተለጣፊነት የተፈለፈሉ ናቸው፡፡ ኢህአዴግ አምባገነን ባይሆን ሀገሪቱ ውስጥ ይህን ያህ ቁጥር ያለው ፓርቲ ባልተፈጠረ ነበር፡ 

ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ አንድ ተስፋ ሰጪ ፖለቲካዊ እርምጃ ተስውሏዋል፤ ምርጫ ቦርድ የጠራው ስብሰባ አጋጣሚውን ፈጥሮላቸው የተቋውሞ ፊርማ በማሰባሰቡ ጉዟቸውን የጀመሩት 33ቱ ፓርቲዎች እነሆ ከምርጫ ባለፈ የጋራ ትግል ለማድረግ ፊርማቸውን አኑረዋል፡  ዲፕሎማቶች ታዋቂ ፖለቲከኞችናጥሪ የተደረገላቸው ሌሎች እንግዶች በተገኙበት በተደረገው የፊርማ ስነ- ስርዓት የየፓርቲዎቹ መሪዎች በግልፅ እንደተናገሩት አምባገነን ስርዓት ለመታገል በጋራ ከመሰባሰብ የተሻለ አማራጭ የለም፡

 ኢህአዴግም የፓርቲዎቹ ከምርጫ ውጪ በሆኑ ጉዳዮችም በጋራ ለመስራት መንቀሳቀሳቸው ስጋት ሳይፈጥርበት አልቀረም፡፡ ለዚህ ሁነኛ ማሳያ የሆነው ፓርቲዎቹ ለፊርማ ስርዓቱ ማስፈፀሚያ 11 አዳራሾችን ጠይቀው አስራ አንዱም ጋር እንዳይሰበሰቡ የተለመደው የኢህአዴግ ክልከላ መፈፀሙ ነው፡፡ የኢህአዴግ ተለጣፊ ፓርቲዎች፣ ፎረሞችና ሊጎች እንዳሻቸው የሚጠቀሙባቸው የህዝብ ንብረት የሆኑ የመሰብሰቢያ አዳራሾችን 33ቱ ፓርቲዎች እንዳይጠቀሙ መከልከሉ የኢህአዴግን ስጋት ከማረጋገጥ ባለፈ የስርዓቱ  የጭቆና ልክ ገደብ እንዳጣም አመላካች ነው፡፡ ሌላው የገዢውን ፓርቲ ስጋት ማሳያ ኢህአዴግ ጥቂትየማይባሉትን የስብስቡ አባል የሆኑ ፓርቲዎችን በመከፋፈል መሞከሩ ነው፡፡ ከአዳማው የተቃውሞ ፊርማ በኋላስብስብ እንዲወጡና በምርጫ እንዲሳተፉጫና የተደረገባቸው ፓርቲዎች የምርጫቦርድን ፉከራና የኢህአዴግን ማስፈራሪያ ተቋቁመው ከምርጫ ባለፈ አብረው ለመስራት የስምምነት ፊርማቸውንማኖራቸው ትልቅ ተስፋ ነው፡፡በእስከ ዛሬቹ የፓርቲዎች ስብስቦችእንደተስተዋለው በጋራ ለመስራትየሚሰባሰቡት ተመሳሳይ ፕሮግራምያላቸው ፓርቲዎች ብቻ ነበሩ ፡፡ሆኖም የኢህአዴግን አምባገነናዊ አፈናለማስወገድ ከፕሮግራም መመሳሰልያለፈ መሰባሰብ አስፈላጊ ነው፡፡ በዚህረገድ አዲስ ጅምር ያሳየው መድረክ ነው፡፡ መድረክ በህብረብሔራዊ አደረጃጀትናበብሔር አደረጃጀት ውስጥ ባሉ ፓርቲዎችነበር የተመሰረተው፡፡ መድረክ ያሳየውበጎ ጅምር ለ33ቱ ፓርቲዎች ስብስብያበረከተው አስተዋፅኦ እንዳለ ግልፅ ነው፡፡በኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ ፓርቲዎቹ በተለያየ የፕሮግራምና የአደረጃጀትየሚከተሉ መሆኑ ሳያግዳቸው እነዲሰባሰቡሊያደርግ የሚያስችሉ በርካታ መሰረታዊችግሮች አሉ፤ የትኞቹም ፓርቲዎችየብሔር እኩልነት እንዲኖር፣ የህግየበላይነት እንዲከበር፣ የሃይማኖትነፃነት እንዲከበር፣ ሀሳብን የመግለፅናየፕሬስ ነፃነት እንዲከበር፣ የመደራጀትነፃነት እንዲከበር እንደሚታገሉ ሲናገሩይደመጣል፡፡ በመሆኑም እነዚህን መሰረታዊመብቶች ለማስከበር የሚደረገውን ትግልበጋራ እንዳይታገሉ የሚያግዳቸውአንድም ምክንያት መኖር የለበትም፡፡ፓርቲዎቹ በአደረጃጀት እና በፕሮግራምልዩነት ግድግዳ ተከልለው ያባከኗቸውን 21ዓመታት በኢህአዴግ አምባገነናዊ ስርዓትስር የሚማቅቀውን የኢትዮጵያ ህዝብመከራ ከማባባስ እና የገዥውን መደብአባላት በእብሪት ተወጥረው እንዲከርሙከማድረግ ያለፈ ውጤት አላመጣም፡፡

ኢትዮጵያ ውስጥ ሰላማዊ ትግልንመርጠው የሚንቀሳቀሱ ፓርቲች በርካታውስጣዊና ውጫዊ ፈተናዎ አሉባቸው፡፡ ውስጣዊ ፈተናቸው መካከል የገንዘብእጥረትና ብቃት ያላቸው አባላት እጦትየጎላውን ስፍራ ይይዛል፡፡ ይህን ችግርለመፍታት ፓርቲዎቹ ከሚያደርጉትጥረት ጎን ለጎን የገንዘብ አቅም ያላቸውናየተማሩ ዜጎች ወደ ትግሉ ጎራ መምጣትአማራጭ የሌለው መፍትሔ ነው፡፡ሌላው የፓርቲዎች ፈተና ውጫዊሲሆን በዋነኝነት ከአምባገነኑ የኢህአዴግመንግስት የሚመነጭ ነው፡፡ ይህንፈተና ለማለፍ ፓርቲዎች በቁርጠኝነትወደተግባራዊ ሰላማዊ ትግል መግባትይኖርባቸዋል፡፡ ኢህአዴግ አዳራሽበመከልከል፣ አባላትን በማሰር እና ህዝብንማሸበር የሚጓዝበት ጎዳና ፓርቲዎችበህዝብ ፊት አቅመ ቢስነታቸው እንዲጎላአደርጓል፡፡ 

ፓርቲዎቹም ይህን ለመገዳደርይሄነው የሚባል ጥረት አድርገዋልለማለት አይስደፍርም፡፡ ከእንግዲህ ግንአዳራሽ ሲከለከሉ ‹‹ተከለከልን›› ብለውስሞታ ከማሰማት ባለፈ በየአደባባዩስብሰባዎችን በድፍረት ማድረግ፤አባሎቻቸው ሲታሰሩ “ታጋዮቻችንን ፍቱ”በማለት በተከታታይ ተግባራዊ ሰላማዊ tግል ለማድረግ ይገባቸዋል፡፡ ከሙስሊምኢትዮጵያውያን ሰላማዊ የትግል መንገድብዙ ሊማሩም ይገባል፡፡ ተግባራዊ ሰላማዊትግሉ በአዲስ አበባ ብቻ የተወሰነእንዳይሆን በተለያዩ ክልሎች እንዲሰፋማድረግም ይገባቸዋል፡፡ የፓርቲዎችስብስብ ከቢሮ ከታጠረ ‹‹ትግል›› ወደተግባራዊ ሰላማዊ ትግል መግባት አለበት፡፡ 

http://www.fnotenetsanet.com/wp-content/uploads/2013/03/fnote-newsletter-67.pdf