ታላቁ ፍቅር-ሙስሊሞች በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ስላት እንዲሰግዱ ተፈቀደ::/Christian Church opens doors to Muslimsበአበርደን የሚገነው የቅዱስ ዮሃንስ ቤተክርስቲያን አጠገቡ የሚገኘው መስኪድ በሙስሊሙ ብዛት የመጣ ለመስገድ ስለማይበቃቸው ከመስኪዱ ውጭ ተሰብስበው ስለሚሰግዱ የህንን ያዩት የጎረቤት ቤተክርስቲያን ቤተ መቅደሳቸውን ሙስሊሞች በቀን 5 ጊዜ እንዲሰግዱበት መልካም ፍቃዳቸውን በማሳየት ለቀሪው አለም ፍቅራዊ ትምህርት እንዲሆን አሳስበዋል ዝርዝሩን ይመልከቱት::
St John's Episcopal Church has opened its doors to Muslims for Friday prayers


በአበርዲን (ስኮትላንድ) ከባድ ቅዝቃዜና የበረዶ ካፊያ በሚዘንብበት ድኅረ ቀትር፣ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሙስሊም ምዕመናን የዕለት ስግደታቸውን ያከናውኑ ዘንድ የቅ. ዮሐንስ ኤፒስኮፓል ቤተ ክርስቲያን በሮች ክፍት ተደርገውላቸዋል፡፡

ባሳለፍነው አርብ ምሳ ሰአት ገደማ ቤተ መቅደሱ ውስጥ ይሰማ የነበረው የወትሮው ክርስቲያናዊ ዝማሬ ሳይሆን ኢስላማዊ ፀሎት እና የቤተ ክርስቲያኗ ካህንና የአጎራባቹ መስጊድ ኢማም ድምጽ ነበር፡፡

ከቤተ ክርስቲያኑ አጠገብ የሚገኘው የሰይድ ሻህ ሙስጠፋ ጃሚዕ መስጂድ አዘውታሪ የሆኑ ሙስሊሞች ቤተ መቅደሱን በቀን አምስት ጊዜ ከክርስቲያን ምዕመናን ጋር በጋርዮሽ እየተጠቀሙበት ይገኛሉ፡፡

እንደ ቤተ ክርስቲያን መሪዎች እምነት በአገሪቱ ውስጥ ክርስቲያንና ሙስሊም ምዕመናን ጎን ለጎን የሚፀልዩበት ብቸኛው ሥፍራ ይህ ሳይሆን አይቀርም፡፡

የቅዱስ ዮሐንስ ቤተ ክርስቲያን ካህን በራቸውን ለሙስሊሞች ክፍት ያደረጉት ሙስሊሞቹ በራሳቸው መስጊድ ውስጥ ሲሰግዱ ቦታ ስላልበቃቸውና ብዙዎቹ ከመስጊዱ ውጪ መንገድ ላይ ለመስገድ መገደዳቸውን በማየታቸው ነው፡፡


Reverend Isaac Poobalan grew up in Southern India surrounded by Islam
Reverend Isaac Poobalan grew up in Southern India surrounded by Islam

በደቡባዊ ህንድ ሙስሊሞች በሚበዙበት አካባቢ ያደጉት ቄስ አይዛክ ፑባላን ሲናገሩ፣ ጎረቤቶቼን ካልረዳሁማ ለሃይማኖቴ አስተምህሮ ታማኝ ነኝ ብዬ ልናገር እንደምን ይቻለኝ ኖሯል ብለዋል፡፡

‹‹ልክ እንደዛሬው ሁሉ፣ ቀኑ በጣም ቀዝቃዛ ነበር፤ በመስጂዱ በኩል ሳልፍ በርካታ ሙስሊም ወንዶች ከመስጊዱ ውጪ ጎዳናው ላይ ከቤተ ክርስቲያናችን አጠገብ ሲሰግዱ አየሁኝ፡፡

‹‹እጆቻቸውና እግሮቻቸው ለቅዝቃዜው የተጋለጡ ነበሩ፣ በዚያ ኃይለኛ ቅዝቃዜ ትንፋሻቸው ይታይሃል፡፡

‹‹ኢየሱስ ‹ጎረቤቶቻችሁን እንደራሳችሁ ውደዱ› ሲል ደቀ መዛሙርቱን አስተምሯል፤ ይህ ለምዕመናን የምሰብከው ነገር ብቻ ሊሆን አይችልም፣ ተግባር ላይ ላውለውም የሚገባኝ እንጂ፡፡››

The mosque is next door to the church  
The mosque is next door to the church


ቄስ ፑባላን አክለው፣ ‹‹ጎረቤቶቼን በዚያ ቅዝቃዜ ውስጥ እየሰገዱ ሳያቸው በጣም የሐዘን ስሜት ተሰማኝ፣ እረዳቸው ዘንድ አንድ ነገር ማድረግ እንዳለብኝም ታወቀኝ፡፡››

‹‹የዓለምን ችግሮች ሁሉ መፍታት እንደማልችል አውቃለሁ፤ እኔ ልፈታው የምችለው ችግር ሲኖር ግን፣ ከመፍታት ወደኋላ አልልም፡፡››

ቄስ ፑባላን የቤተ ክርስቲያኒቱን በር ለሙስሊሞች ክፍት ለማድረግ ክርስቲያን ምዕመናኑን ፈቃድ ጠየቁ፡፡

መጀመርያ ላይ ሙስሊሞቹ ግብዣውን ለመቀበል አመንትተው ነበር፣ አሁን ግን በጥሩ ሁኔታ አዲሱ ቤታቸውን ለምደው ተረጋግተው ይፀልያሉ፡፡

በቤተ መቅደሱ ተጠቃሚ ሙስሊሞች አንዱ ሞህዚድ ሱፍያን፣ ‹‹ሰላታችንን የምንሰግድበት ቦታ ስለሰጠችን ቤተ ክርስቲያኒቱን በእጅጉ እናመሰግናታለን›› ብሏል፡፡

‹‹ከመስጊዱ ውጪ መሬቱ ላይ መስገድ፣ በተለይ ለአዛውንቶች፣ በጣም አስቸጋሪ ነበረ፡፡››
‹‹አባ ፑባላን እኛን ሁላችንን ወደዚህ ቤተ ክርስቲያን ገብተን እንድንሰግድ በመጋበዛቸው ትልቅ ውለታ ነው የዋለሉልን፡፡››

‹‹የእምነት ሥርዓታችንን በሙሉ አክብረውልን፣ ቤተኝነት እንሲሰማን አድርገውናል፡፡›› ….
The Bishop of Aberdeen said it couild be a lesson for the rest of the world  
The Bishop of Aberdeen said it couild be a lesson for the rest of the world