"የኦርቶዶክስ ስያሜ የተገኘው ከአውሬው(666) ነው:ትርጉሙም ጊዜው ያለፈበት አክራሪ ማለት ነው::"ደቂቀ ኤልያስ የኦ/ተዋህዶ እንቅስቃሴ ያሰጋል::


የወያኔው መንግስት በቅርቡ ወደሃገር ቤት የጋበዘው ዘመናዊው የተዋህዶ ዜጋ "ማኅበረ ሥላሴ ዘደቂቀ ኤልያስ አሐቲ የሰማይ ጉባኤ ዘቅድስት ቤተክርስቲያን ቅድመ መንበሩ ለእግዚእነ ወእመፍጥረተ ወላዲተ አምላክ" በሚል መጠሪያ የሚጠራው እልያስ የተባለው ነቢይ የኦርቶዶክስን እምነት በተመለከት የሰጠው አስተያየት በተዋህዶ አማኞች ዘንድ ቁጣን እየቀሰቀሰ ስለሆን በዋና ከተማይቱ ጨምሮ ከፍተኛ የሆን የተቃውሞ እንቅስቃሴ እንዳይጀመር ያሰጋል ::
ዝርዝሩን ይመልከቱት:-


 https://www.facebook.com/dekikeelias.zethiopia?fref=ts
የቅድስት፡ቤተ፡ክርስቲያን፡ቋንቋ፡ከአርያም፡ከልዑል፡መንበር፡የተገኘ፡መንፈስ፡ቅዱስ፡የፈቀደው፡ሰማያዊ፡ልሳን፡ስለሆነ፡ሰይጣን፡
ባዘጋጀው፡ምንነቱ፡ባልታወቀ፡አነጋገር፡መጠቀም፡ፈጽማ፡አይገባትም፡ነበር፡ነገር፡ግን፡አውሬው፡እረኞችን፡ከተኩላ፡ስንዴን፡
ከእንክርዳድ፡ለመቀላቀልና፡ብዙዎችን፡ግራ፡አጋብቶ፡ለማጥመድ፡ባዋቀረው፡ተንኮል፡ቤተ፡ክርስቲያን፡ኦርቶዶክስ፡በሚል፡
ስያሜ፡ስትጠራ፡ኖራለች፡፡እስቲ፡ኦርቶዶክስ፡ተዋህዶ፡ብሎ፡ከማለትና፡ካቶሊክ፡ተዋህዶ፡ቤ/ክ፡ከማለት፡መካከል፡ምን፡ልዩነት፡አለ?
በእውነት፡የቃላት፡ጉዳይ፡ቢሆን፡ኖሮ፡ቤተ፡ክርስቲያንን፡ለማመስገን፡ከተፈለገ፡ኦርቶዶክስ፡ተዋህዶ፡ብሎ፡ከመሰየም፡ይልቅ፡
ካቶሊክ፡ተዋህዶ፡ቤ/ክ፡ብሎ፡መሰየሙ፡በአስር፡እጥፍ፡የተሻለ፡ነበረ፡ነገር፡ግን፡ሁለቱም፡(ኦርቶዶክስም፡ካቶሊክም፡)የመናፍቃን
፡ማለት፡ክርስቶስ፡ሁለት፡ባህርይ፡ነው፡የሚሉ፡የንስጥሮስ፡ጭፍሮች፡ስያሜዎች፡ስለሆኑ፡ለቤተክርስቲያን፡ፈጽሞ፡አላስፈላጊ፡
ህገወጥ፡ስያሜዎች፡ናቸው፤፡ሰይጣን፡እረኞችን፡ለመቆጣጠር፡በጎችን፡ለመማረክ፡ባቀናበረው፡ረቂቅ፡ተንኮል፡ቤተ፡ክርስቲያን፡
ኦርቶዶክስ፡ተብላ፡እንድትጠራ፡፤የዓለም፡አብያተ/ክ፡ጉባኤ፡መስራች፡የመጽሐፍ፡ቅዱስ፡ማኅበር፡አባል፡እንድትሆን፡
አድርጓል፡፡
በዚህም፡አውሬው፡ባጠመደው፡ወጥመድ፡ብዙዎች፡ለሞት፡ተዳርገዋል፡፡
ዛሬግን፡ከእንቅልፍ፡የምንነቃበት፡የአውሬውን፡ተንኮል፡አውቀን፡የምናመልጥበት፡ደቂቃ፡ላይ፡ስላለን፡የሰው፡ልጆች
፡ሁሉ፡በተዋህዶ፡አለት፡ላይ፡ጸንተን፡ከመናፍቃን፡ጋር፡ምንምአይነት፡ህብረትና፡መቀላቀል፡ሊኖረን፡፡አይገባምና፡እኛ
፡የአንዲቷ፡ቀጥተኛ፡የተዋህዶ፡ሃይማኖት፡ልጆች፡ሁሉ፡ኦርቶዶክስ፡የሚለውን፡ተንኮላዊ፡ስያሜ፡ከራሳችን፡ላይ፡
ማስወገድ፡ይገባናል፡፡

ነገር፡ግን፡ኦርቶዶክስ፡የሚለው፡ስያሜ፡ለቤተ፡ክርስቲያናችን፡መቼ፡እንዴት፡በእነማን፡ለምን፡አላማ፡ሊሰጣት
፡ቻለ፡የሚሉትን፡መጠይቆች፡ስንመረምር፡በቤተ፡ክርስቲያን፡ላይ፡ሰይጣን፡የቀመመው፡መርዛማ፡ተንኮል፡
አውሬው፡ያቀናበረው፡ስውር፡ደባ፡መኖሩን፡እናስተውላለን፡፡በእርግጥ፡ይህ፡ኦርቶዶክስ፡የሚለው፡ስያሜ፡
ብዙዎች፡በየዋህነት፡አሜን፡ብለው፡እንደተቀበሉት፡“ርትዕይት፡ቀጥተኛ፡ሃይማኖት፡”ብሎ፡ቤተ፡ክርስቲያንን፡
ለማመስገን፡የተሰጠ፡ስያሜ፡አይደለም፡፡
እንደሚታወቀው፡ማንኛውም፡ቃል፡በመዝገበ፡ቃላት፡ውስጥ፡ከተመዘገበለት፡ፍቺ፡ይልቅ፡በህብረተሰብኡ፡
ውስጥ፡የሚፈጥረው፡ስሜትና፡የሚሰጠው፡መልእክት፡ታላቅ፡ተጽእኖ፡እንዳለው፡የቋንቋ፡ጥናት፡ባለሞያዎች
፡እንኳ፡የሚመሰክሩት፡እውነታ፡ነው፡በእርግጥ፡ኦርቶዶክስ፡የሚለው፡ቃል፡በግሪክ፡ቋንቋ፡መዝገበ፡ቃላት፡
ውስጥ፡ቀጥተኛ፡ሃይማኖት፡የሚል፡ፍቺ፡ቢሰጠውም፡በዓለም፡ሕብረተሰብእ፡ዘንድ፡ግን፡”አክራሪ፡አውቃለሁ፡
ባይ፡ጊዜው፡ያለፈበት፡የቆየ፡ወዘተ፡የሚል፡አሉታዊ፡ትርጉም፡ያለው፡ቃል፡ነው፤ዓለም፡ለማናቸውም፡አክራሪ፡
ተመጻዳቂ፡ናቸው፡ብሎ፡ለሚፈርጃቸው፡ጎራዎች፡ሁሉ፡”ኦርቶዶክስ፡ክርስቲያን፤ኦርቶዶክስ፡እስላም፤
ኦርቶዶክስ፡ይሁዲ፡…ወዘተ፡እያለ፡ነው፡የሚሰይማቸው፡፡ሌላው፡ቀርቶ፡በአውሮፓ፡የገበያ፡አዳራሾች፡
ውስጥ፡እንኳ፡ትኩስ፡ባልሆኑ፡በጥራጥሬዎች፡በፍራፍሬዎች፡ላይ፡ኦርቶዶክስ፡የሚል፡ማስታወቂያ፡
የሚነበበው፡ኦርቶዶክስ፡የሚለው፡ቃል፡በህብረተሰብኡ፡ዘንድ፡ጊዜው፡ያለፈበት፡ከንቱ፡ማለት፡መሆኑን፡
ያስረዳናል፡በአጭሩ፡ኦርቶዶክስ፡የሚለው፡ስም፡የሮም፡መናፍቃን፡ለራሳቸው፡ካቶሊክ፡ማለት፡አንዲት፡
ሐዋርያዊት፡ዓለምአቀፋዊት፡ቤተ፡ክርስቲያን፡የሚል፡ስያሜ፡ወስደው፡ከእነርሱ፡የተለዩትን፡ምስራቅ፡
አውሮፓውያንን፡ለመንቀፍ፡የተጠቀሙበት፡ስያሜ፡መሆኑን፡እናስተውላለን፡፡
ዋናው፡ቤተ፡ክርስቲያን፡ኦርቶዶክስ፡ተብላ፡እንድትሰየም፡ሰይጣን፡ያደረገበት፡ተንኮል፡ግን፡ይህ፡ነው፡፡
ኦርቶዶክስ፡የመናፍቃን፡ስያሜ፡ነው፡እመቤታችንን፡የሰው፡እንጂ፡የአምላክ፡እናት፡አይደለችም፡
በሚለው፡የንስጥሮስ፡የልዮን፡መንገድ፡ክርስቶስ፡ሁለት፡ባህርይ፡ነው፡ብለው፡ክደው፡ንጹሐን፡ኢትዮጵያውያንን፡
እነቅዱስ፡ዲዮስቆሮስን፡ያሳደዱ፡የምስራቅ፡አውሮፓ፡የግሪክ፤የሩስያ፤…መናፍቃን፡ስያሜ፡ነው፡፡
ታዲያ፡ለምን፡ወልደ፡አብ፡ወልደ፡ማርያም፡በተዋህዶ፡ከበረ፡ብለን፡አንዲቷን፡እውነተኛዋን፡ቀጥተኛዋን
፡ክርስትና፡የምናምን፡እኛ፡ኦርቶዶክስ፡የሚል፡ስያሜ፡ሊለጠፍብን፡ቻለ፤ቢሉ፡ጠላታችን፡ዲያብሎስ፡
በአውሬው፡ላይ፡አድሮ፡የቤተ፤ክርስቲያንን፡መሪዎች፡በቁጥጥሩ፡ስር፡ለማድረግ፡የተጠቀመው፡ረቂቅ፡
ተንኮል፡መሆኑን፡
እናስተውላለን፡፡
በትንቢት ተነግሮለት ታላቅ ኃይልና ሥልጣን ተሰጥቶት ከብሔረ ሕያዋን የወረደውን ቅዱስ ኤልስያን
መቃወምም ይሁን ማስቆም አይቻላችሁም ያላችሁ ብቸኛ አማራጭ የዚህን አስፈሪ ቀናኢ ነቢይ
 የሚያዘውን የእግዚአብሔር ቃል መስማት ብቻ ነው፡፡ይህን እሺ በጄ ብላችሁ ብትቀበሉ ባለፉት
ዘመናት ሁሉ በኑፋቄ ሃይማኖታችሁ ተደናግረው ሲዖል የወደቁትን ወገኖቻችሁን ሁሉ ለማስማር
የምህረቱን በር ትከፍቱታላችሁ፡፡እምቢ ብትሉ ግን የቅዱስ ኤልያስን ፈራጅነት መቋቋም አትችሉም፡፡
እንግዲህ ሁላችን በእመቤታችን ርህራሄ አንድ ሆነን፡በንስኀ፡ለኢትዮጵያ፡ትንሳኤ እግዚአብሔር ያብቃን አሜን፡፡
ማኅበረ ሥላሴ ዘደቂቀ ኤልያስ አሐቲ የሰማይ ጉባኤ ዘቅድስት ቤተክርስቲያን ቅድመ መንበሩ
ለእግዚእነ ወእመፍጥረተ ወላዲተ አምላክ፡፡
 ከዚህ በላይ ብሎግ የተደረገው የኔ እምነት ሳይሆን "ማኅበረ ሥላሴ ዘደቂቀ ኤልያስ አሐቲ የሰማይ ጉባኤ ዘቅድስት ቤተክርስቲያን ቅድመ መንበሩ ለእግዚእነ ወእመፍጥረተ ወላዲተ አምላክ" በሚል መጠሪያ የሚታወቀው ወያኔ ወደ አገር ቤት በተዋህዶ እምነት ላይ እንዲያንሰራፋ የጋበዘው ሃራጥቃ መልእክት ነው::እኔን አይወክልም!!!