የኢትዮጵያውያን ስቃይ በርትቷል!!!በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ከየመን ሊባረሩ ነው::

የኢትዮጵያውያን ስቃይ በርትቷል!!!በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ከየመን ሊባረሩ ነው::


በበጎ ፍቃድ ተመልሰዋል በሚል ሽፋን ህገወጥ ናቸው የተባሉ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ከየመን እንደሚባረሩ ተሰማ::የአለማቀፉ ስደተኞች ድርጅት በበኩሉ ከፍተኛ የሆነ የእርዳታ እጥረት እንደገጠመው እና ለሚቀጥሉት ወራቶች እንኳን ሊያቆይ የሚችል ፈንድ ስለሌለ ወደ ሃገራቸው እንዲመለሱ ግፊት እያደረገ ነው::
በየመን የሚገኙ በሺዎች የሚቆጠሩ ስደተኞች አስከፊ ሁኔታ ውስጥ እንዳሉ የሚታወቅ ሲሆን የወያኔ ጁንታ በፈጠረባቸው የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ችግር ምክንያት ለስደት የበቁ ዜጎች ናቸው:: እነዚሁ ዜጎቻችን ካለምንም መቋቋሚያ እና እርዳታ በባዶ ወደ አገራቸው እንዲመለሱ እና ሜዳ ላይ እንዲፈሱ የተፈረደባቸው እንደሆነ መረጃዎች ያመለክታሉ::

የወያኔ መንግስት አሰፍስፎ የሚጠብቃቸው የኦነግ እና የኦብነግ አባላት ከነዚሁ ስደተጞች ጋር ያሉ ሲሆን እስካሁን የተባበሩት መንግስታት ላመለከቱት ጉዳይ መልስ እንዳልሰጣቸው ታውቋል:: የወያኔ ጁንታ አስፈላጊውን በሙሉ እንደሚያሟላ እና ስደተኞቹ ወደ አገር ቤት እንዲመለሱ እንደሚፈልግ በተደጋጋሚ የስደተኛ ድርጅቶችን እየወተወተ ይገኛል:: ይህን ወያኔ በአሸባሪነት ስም ፈርጆ ሊከሳቸው የሚፈልጋቸው ዜጎች እንዳሉ የሚጠቁም ሲሆን እስካሁን በስደተኛው እና በኣይ.ኦ.ኤም መካከል የመመለስ ስምምነት ስላልተደረሰ ለአዛውንቶች እና ለህጻናት እርዳት እየቀረበ ቢሆንም በቂ አለመሆኑ እየተነገረ ነው::