የበረሃው ንድፈ-ሀሳብና የኢሕአዴግ መንግስታዊ ቆመጥ ዳንኤል ሺበሺ

በረሃ በነበሩበት ወቅት ከነደፏቸው ንድፈ- ሀሳብ እና ወደ ቤተመንግስት ከገቡ
በኋላ በጎሣ፤ በደምና በአጥንት ቆጠራ፤ በፖለቲካዊ አስተሳሰብ ቅርበት/ርቀት
ወይም ልዩነት ወገንተኝነት እየለዩና ዳግም እንዳያገግም አከርካሪውን እየሰበሩ፤
ዜጎች እንደየፍጥረታቸው ሳይሆን እንደየራሳቸው እንዲያስቡ፤ ካልሆነም
ዳግም እንዳያቆጠቁጥ እንቡጥ እንቡጡን እየቀነጠሱ ቢያንስ ለአንድ ትውልድ
የዘለቁ ሲሆን፤ ጎን ለጎን የራሳቸውን (ከግለሰብ እስከ ፓርቲያቸው ድረስ)
የኢኮኖሚ ጡንቻዎችን በማፈርጠም፤ ቀጥሎም በፖለቲካ ካፕታላይዝ እንዲሆኑ
ከሚያደርጋቸው ዕቅድና ስትራቴጂ አካል ........ብሔርንና የቀበሌ መታወቂያ ደብተርን ምን አገናኘው?
http://minilik-salsawi.blogspot.com/2013/04/blog-post_15.html

 ፍኖተ ነጻነት
የአማራ ብሔር ጉዳይ ከግንቦት 1983 ዓ.ም በፊት ያለቀ ጉዳይ ነው፡፡ የአማራ ብሔር ተወላጆችን አከራካሪ ለመስበርና
ሁለንተናዊ አቅማቸውን (በተለይም የኢኮኖሚያዊና የፖለቲካዊ አቅማቸውን) ለማሽመደመድ ውጥኑንና ንድፈ
ሀሳቡን ከግንቦት 20,1983 ዓ.ም በፊት በረሃ ባሉበት ጊዜ የወሰኑትና አሁን
እየተተገበሩት ነው ባይ ነኝ፡፡
ይህንን ለማረጋገጥ አንድ ምሳሌ ለመጥቀስ ወደድሁ፡፡
ኢህአዴግ አገሪቱን በተቆጣጠረበት ማግሥት ጀምሮ እስከ 1990 መጨረሻዎቹ ድረስ እኔ በነበሪኩበት አከባቢ የሠላምና
መረጋጋት ኮሚቴ አባልነትን ጨምሮ በተለያዩ ፖለቲካዊ መዋቅሮች ውስጥ በተለያየ የኃላፊነት ቦታዎች፤ በሹመት፤
በውክልናና በምርጫ ሁለገብ ሥራዎችን ሰርችያለሁ፡፡ በዚህ ቆይታዬ ውስጥ አንድ ያአጋጠመኝን ነገር ስምና ቦታ ሳልጠቅስ
የድርጊቱን ፍሬ ነገር ላጋራችሁ፡፡ ድርጊቱ የተፈፀመው ህዳር 1985 ዓ.ም ነው፡፡ አከባቢዬ እንደ አሁኑ አጠራር ደቡብ
ክልል ካሉት ዞኖች ውስጥ በአንዱ ሲሆን፤ ከዕለታት አንድ ቀን ሁለት ከፍተኛ የኢህዴግ ባለሥልጣናት ከማዕከልና ክልል ወደ አከባቢዬ መጡ፡፡
የአካባቢዩ የሠላምና መረጋጋት ምክር ቤት አባላትም ነበሩ፡፡ እነዚህ መጤ ባለሥልጣናት የአካባቢ
ባለሥልጣናትን በመያዝ፤ ያኔ ዕድሜያቸው ከ76-ዓመት ወደማያንስ አዛውንት ወይምመኖሪያ ቤት ያመራሉ፡፡
ግለሰቡ ያሉት በመኖሪያ ቤታቸው ሳይሆን አንድ የማር ጠጅ በሚሸጥበት ቤት ከጓደኞቻቸው ጋር
እተዝናኑ ነበር፡፡ የተደገሰላቸውን ነገር አይደለም እርሳቸው፤ ቦንብ ታጥቀው፤ መትረየስ ደግነው፤ ምንነቱ የማይታወቅ
ነገር ሸክፈው፤ በቅጫምና በቅማል ተወሪረው፤ ሸበጥ ተጫምተውና በአጭሩ ለብሰው የገቡትን ዳቦ በመወርወር፤
መንገድ በማሳየት “እንኳን ደህና መጣችሁ!” በማለት የተቀበልንና ከእነርሱ
ጋር እየሠራን ያለነውም አናውቅም ነበር፡፡
ሰዓቱ ከምሽቱ ወደ 1ሰዓት ገደማ ሲሆን ከተማው በጩኸት፤ በዋይታና በለቅሶ ይደበላልቃል፡፡ “ይህ የምን ጩኸት
ነው?” እያልኩ በሩጫ እስከ ቦታው ድረስ እየሮጥኩ ምንድው እያልኩ በየመንገዱ
ዳር የቆመውን ህዝብ ማጠያየቅ ጀመርኩኝ፡፡
ሕዝቡም እናንተም እያላችሁ ነው ወይ አቶ እገሌ የሚገደለው በሚል እያለቀሱናእየነፈረቁ ይነግሩኛል፡፡
ከዚያም ከሚዝናኑበት ቦታ በመሬት እየተጎተቱወጥተው ደም እያስመለሳቸው በአውራ
ጎዳና ተዘርረው በተቆራረጠ ትንፋሽ ወደሚተነፈሱ አዛዊንት ዘለቅሁ፡፡ “ምን ሆኑ
አባባ አልኳቸው?” መልስ የለም፡፡ ከዚያም ወደ ባልደረቦቼ ፊቴን አዞርኩኝ፡፡ እነርሱም
“እባክህን ተውው! እኛ የሚናውቀው ነገር የለም” አሉኝ፡፡ “ታዲያ የዚህ ድርጊት
ፈጻሚዎች ማን መርቷቸው ነው እዚህ የደረሱት” የሚል ጥያቄ አስከተልኩኝ፡፡
አንዱ ወዳጄ “ሌላ መዘዝ እንዳታመጣብን” በማለት እንዳርፍ በጽኑ መከረኝ፡፡
አዛውንቱ በደረሰባቸው ጉዳት ለረጅም ጊዜ ከታመሙ በኋላ ሕይወታቸው
አልፏል፡፡ በማግሥቱ ስብሰባ ተጠራንና “በመሥመራችን መሆን ወይም አርፈው
መቀመጥ፤ አለባለዚያ ነፍጠኛ-አማራዎችን ምንጣሮ ይቀጥላል፤ እንደ ትላንትናው
ሰውዬ ደም እናስተፋለን” በሚል ስብሰባው ይቋጫል፡፡ ከስብሰባው በኋላ በምሳ ላይ “...
ግን ግን አዛውንቱ ወንጀለኛ ናቸው ቢባል እንኳ ሳንገል ወይም ሳንደበድብ ጉዳዩን
በሕዝብና በተመረጡ ሰላምና መረጋጋት ኮሚቴ ምክር ቤት እንዲታይ ማድረግና
ውሳኔውን ተግባራዊ ማድረግ አይቻልም
ወይ” ብዬ ጠየኩ አንዱና በጊዜው ትልቁ የፖለቲካ አደራጅ (ባለሥልጣን) የመለሰልኝ
ምላሽ “...ደሞ! ለአማራ ይህንን ያህል ትጨነቃለህ እንዴ!” የሚል ነበር፡፡
እስከ ዛሬ ድረስ ይህ ምላሽ እጅግ እንዳመመኝ ከኔ ጋር የዘልቋል፡፡ ውሎ
አድሮ ጨዋታውና የጨዋታው ሕግ ለእኔ ግልጽ እየሆነ የመጣ ሲሆን፤ ጉዳዩ ያኔ
በረሃ ባሉበት ጊዜ በደርግ ስፍራ ሲተኩ ለማድረግ የወጠኑት ውጥን አካል ሳይሆን
አይቀርም የሚል ጥርጣሪዬ እያየለ መጣ፡፡ አዎን ለእኔ እስከገባኝ ከዛ ጊዜ
ጀምሮ ኢህአዴግ አማራ የሚባለውን ስም እንደሚጠላ፣ እንደሚፈራ ገባኝ፡፡ ኢህአዴግ
የአማራ ተወላጆችን እንደግለሰብም ሆነ እንደ ቡድን ደም እያስተፋቸው፤ የሥራ
ቅጥርና የደረጃ ዕድገት እየከለከላቸው፤ የእርሻ ማሳ እየቀማቸው፤ አስተሳሰባቸውን
እያመከናቸው፤ ሥነ-ልቦናቸውን እያሸበራቸውና ወኔያቸውን እያኮላሻቸው
ይኸው በፍጹም ጥላቻ እያሰቃያቸው ለዛሬ መድረሱን እራሱ ኢሕአዴግ ይክዳል ብዬ
አላምንም፡፡
በረሃ በነበሩበት ወቅት ከነደፏቸው ንድፈ- ሀሳብ እና ወደ ቤተመንግስት ከገቡ
በኋላ በጎሣ፤ በደምና በአጥንት ቆጠራ፤ በፖለቲካዊ አስተሳሰብ ቅርበት/ርቀት
ወይም ልዩነት ወገንተኝነት እየለዩና ዳግም እንዳያገግም አከርካሪውን እየሰበሩ፤
ዜጎች እንደየፍጥረታቸው ሳይሆን እንደየራሳቸው እንዲያስቡ፤ ካልሆነም
ዳግም እንዳያቆጠቁጥ እንቡጥ እንቡጡን እየቀነጠሱ ቢያንስ ለአንድ ትውልድ
የዘለቁ ሲሆን፤ ጎን ለጎን የራሳቸውን (ከግለሰብ እስከ ፓርቲያቸው ድረስ)
የኢኮኖሚ ጡንቻዎችን በማፈርጠም፤ ቀጥሎም በፖለቲካ ካፕታላይዝ እንዲሆኑ
ከሚያደርጋቸው ዕቅድና ስትራቴጂ አካል እንደሆነ ነው የሚገባኝ፡፡
ብሔርንና የቀበሌ መታወቂያ ደብተርን ምን አገናኘው?
እዚህ ላይ ለአማራም እንበል ለሌላ ብሄር የተዘጋጀ አንድ ወጥመድ እንይ፤
በአንድ ወቅት የከተማ ነዋሪዎች መታወቂያ ደብተር ለማውጣት ብዬ
ሄድኩና በመጠይቁ ላይ ያሉ ከ28-ያላነሱ ይያቄዎችን ሞላሁና “ብሔር” ለሚለው
መጠይቅን እንዲሞላ በተተወው ባዶ ቦታ ላይ እኔም በላዩ ላይ መስመር አድርጌ
መለስኩላቸውና በቀጠሮ ቀን እንድመለስ ተነገረኘኝ፡፡ በቀጠሮዬ ቀን ከጧቱ 4 ሰአት
ወደ ቀጠረኝ ቢሮ ከሌሎች ተረኞች ጋር ወረፋዬን እየጠበኩ፤ ከጎኔ ከተቀመጠውና
እዛው ከተዋወኩት አንድ ሰው ጋር የቀበሌ አስተዳደር በአሁኑ ወቅት ምን
ያህል ህዝቡን እያስለቀሰ እንዳለ ሐሜት ብጤ ነገር በሹክሹክታ እያወራን እያለ
ተራዬ ደረሰና ጉዳያችሁ በሥ/ያጅ ቢሮ የሚታይላችሁ በሚለው ዝርዝር ስሜ
ተጠራና ወደዛው አመራሁ፡፡ ሥራ አስኪያጁም ጉዳዬ ምን እንደሆነ ጠየቀኝና
“...አይ የእኔ እንኳ ተራ ነገር ነው፤ መታወቂያ ፈልጌ ነው” በማለት ቀለል
አድርጌ ነገርኳቸው፡፡ ሥራ አስኪያጁም መለሱና “ይህማ ምን ቀላል ነው፤ እጅግ
በጣም ወሳኘኝና መሠረታዊ ነገር ነው” አሉኝና “ለማንኛውም ብሄር የሚለውን
ስላልሞላህ መታወቂያው አይሰጥህም” አሉኝ፡፡ “ጌታዬ ስላልፈለኩ ነው የዘለልኩት”
አልኳቸውና የራሴን መከራከሪያ ነጥቦቼን መተንተን ጀመርኩት፡፡
“እኔ እየጠየኩ ያለሁት የፓርቲ አባልነት ማረጋገጫ
መታወቂያ፤ ወይም ከአንዱ ብሔር ክልል ወደ ሌላ ብሔር ክልል ለመግባት  የይለፍ
ካርድ አይደለምኮ! እየጠየኩ ያለሁት የዚህ ቀበሌ ነዋሪ መሆኔን፤ የሚገልጽ
የቀበሌ ነዋሪዎች መታወቂያ ካርድ ነው” አልኳቸው፡፡
“የነዋሪነት መታወቂያ ደብተር እንዳይሰጥ በሕግ እስካልተገደ ድረስ፤ እንደሚታየኝ
በማንነቴ የሰው ልጅ መምሰል ሳይሆን የሰው ልጅ ነኝ፤ የእኔነቴን መለያ
ፎቶዬን፤ መሸኛ ካስፈለገም የመሸኛዬን ታአማኝነትንና በቅጹ ላይ ስለተሞሉ
መረጃዎች እውነተኝነታቸውን በማረጋገጥ፤ እንዲሁም ተያዥም ካስፈለገ
እነዳቀርብ በማድረግ መስጠት ነው እንጂ ምን ስለታሰበ ነው ወደ ብሔር ጥያቄ
ውስጥ የገባችሁት” እያልኩ ክርክሬን ቀጠልኩትና “... በአጠቃላይ እኔ የዚህ
ቀበሌ ነዋሪ፤ ሰላማዊ ኢትዮጵያዊ ዜጋ መሆኔን ካወቃችሁ ብቻ አይበቃም ወይ?
አልኳቸውና አያይዤም ወንጀለኛም ቢሆን እንኳ የነዋሪነት መታወቂያ ቢሰጠው
ተጠቃሚው ከግለሰቡ ይልቅ አስተዳደሩ ነውኮ!” ወ.ዘ.ተ መከራከሪያ ነጥቦቼንለመጥቀስ ሞከርኩ፡፡
ነገር ግን ይኼ እየሠራ ያለውና ስለመታወቂያ አሰጣጥ የወጣው ደንብም
እንበል ህግ እስካልተሸሻለ ድረስ አንተ ስለጨቀጨቅከኝ ብዬ መፈረም አልችልም
ሲለኝ፤ በተራዬ እኔም “በሁለት ምክንያት በቀበሌ መታወቂያዬ ላይ የብሔር ወይም
የጎሣ ስም አልጽፍም እያልኩ ምክንያቶቼን የመጀመሪያ ምክንያቴ ከኢትዮጵያዊነት
ውጭ መጥቆር፤ መቅላት፤ ቋንቋ፤ ወይም አጥንትና በደም አይነት የሚገኝ
ማንነት መለያዬ እንዲሆን ስለማልፈልግ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ እናንተ
እንደሚትሉት እኔ ከተለያዩ ከሁለት በላይ ብሔሮች የተገኘሁ ስለሆነ፤ አንዱን
ከሌላው ማበላለጥ፤ ወይም አንደኛውን ከሌላይኛው በምን እንደሚሻል ደረጃ
ለመስጠት ስለምቸግረኝ ነው” አልኩት፡ ፡ ስለዚህ ከፈለጋችሁ ብሔር የሚለውን
እንዲተካ የጣት አሻራ መውሰድ፤ የዲ.ኤን ምርመራ ማድረግ ትችላላችሁና
በዚህ እርዱኝ አልኩ፡፡ በመጨረሻም በዚህ አይነት አስተሳሰብ መታወቂያ
መቼም አታገኝምና ከቢሮዬ ውጣልኝ ሲለኝ እኔም አደራችሁን ዜግነቴን
እንዳትከለክሉኝ ብዬ ወጣሁ፡፡ እንግዲህ ከዚህ ጋር በተያያዘ አንድ ነገር
ማገናዘብ ይቻላል፡፡ ብሔርንና የነዋሪነት መታወቂያ ደብተርን ማቆራኘታቸው
ዓላማው ምን እንደሆነ፤ መቼ ማንን ምን ለማድረግ እነዳሰቡና ለምን አንድን ቀበሌ/
መንደር ሕዝብን በብሄር እየከፋፈሉ እንደሚመዘገቡ ማሰብ የሚችል ሁሉ
በቀላሉ ሊደርስበት የሚቻል ጉዳይ መሆኑ አንድ ነገር ሆኖ ለክፉ ቀን ያስቀመጠው
ወንፊት ብለን ብንጠራጠር ምኑ ላይ ነው ስህተታችን? እንዲሁም ለወደፊቱስ
ከብሔር ጥያቄ ጋር አይይዘው የየትኛው ፖለቲካ ፓርቲ አባል እንደሆንን
የሚጠይቅ ደብተር እንደማያዘጋጁ ምንም ዋስትና ያለ አይመስለኝም፡፡
ይህንን ገጠመኝ እዚህ ላይ እንድጠቅስ ምክንያት የሆነው ኢሕአዴግ በተለያዩ
ጊዜያት አማርኛ ተናጋሪ በሆኑ ዜጎች ላይ የሕግና የፖለቲካ ባለሙያዎች
“ዘር የማፅዳት ዘመቻ” ያሉትን ድርጊት በትውልድ ክልሌ(ደቡብ) ውስጥ በቤንች
ማጅ ዞን በተለይም በጉራፈርዳ ወረዳ፤ እንዲሁም በዛው ዞን ውስጥ ሜኒት
ወልድያ ወረዳ በተለይም ዘንባብና አርፋጅ ቀበሌ ነዋሪዎችን፤ በተመሳሳይ
መልኩ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ያሶ ወረዳ፤ እንዲሁም በዚሁ ክልል ውስጥ
ከማይ ዞን ወ.ዘ.ተ የመንግሥትን ግዴታ እየተወጡ፤ ግብርንና ቀረጥን እየከፈሉ፤
በብዙ ድካም ካለሙበት ቄዬ በባዶ እጃቸው እንዲወጡ መደረጋቸው ነው፡፡
ከላይ ከተጠቀሰው ታሪክና ከሌሎች ማለትም በየስብሰባዎቹ ከሚወረወሩ
አስተያየቶች፣ ምላሾችና በተለያየ አጋጣሚ ካነበብኳቸው ድርጅታዊ የሕትመት
ውጤቶች ወ.ዘ.ተ እንደተከታተልኩት ከሆነ፤ ኢሕአዴግ በተለይ አማራውን
የሚያጠቃበት ልዩ ስትራቴጂክ ፕላን እንዳለው ነው፡፡ በአጠቃላይ ከ3ኛው
ዘር ግንድ የሚዘል የአማርኛ ትርጉም የሚሰጥ ስም የተሰየመ ግለሰብ ካለ እና
ከአማራ ክልል ውጭ ኑሯቸውን በአንድ አካባቢ በማድረግና እጅብ ብለው የሚኖሩ
ከሆነ፤ ነፍሳቸውን ለማዳን ሲሉ፤ አንድም ብአዴንን ማፈላለግና መቀላቀል፤ አልያም
መሰደድ (የውስጥና የባህር ማዶ ስዴት) ወይም በገዛ ሀገራቸው ድምጻቸውን
አጥፍተው፤ አንገታቸውን ቀብረውና ተገልለው መኖር የሚጠበቅባቸው
ሲሆን፤ ለዚህ ደግሞ ሥውርና ግልጽ ፖለቲካዊ፤ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ደባ ይሠራባቸዋል፡፡
በአጠቃላይ ግን ለቻይናዊያንና ለህዳዊያን ውቅያኖስ ያህል የሰፋችው ኢትዮጵያችን
ለአማራ ከተባለው ብሔር ለተገኙት ኢትዮጵያውያን ደግሞ የበሬ ግንባር
ሆናለች፡፡ ሀሳቤን ሰብሰብ ላደርገውና ልቋጨው አይጦች-የአይጥር ዘር፤ ድመት
-የድመትዘር፤ውሻ-የውሻ ዘር፤ ዛፍ ደግሞ የዛፍ ዘር... ሲባሉ እኛ ደግሞ የሰው ዘር
መሆናችንን፤ አትዮጵያዊ መሆናችን ተገፎብን የአማራ ዘር፤ የኦሮሞ ዘር፤
የጉራጌ፤ የጋሞ፤ የትግሬ፤ የወላይታ ዘር ወ.ዘ.ተ. እየተባባልን ልቦናችን
እያወቀው ገዥዎች በሚፈጥሩት ድርና ማግ ተጠላልፈን ወገን ወገኑን፤ ዘመድ
ዘመዱን እንደ ባዕድ በመቁጠር፤ እየፈጀ ነው፡፡ እርስ በራሳችን እየተባላን ልናልቅ
ነው (ፈጣሪ ካልደረሰልን በስተቀር)፡ ፡ በተለይም ገዥዎች ተገዥዎችን፤
አውራው መንጋውን፡፡ ከላይም ለመጥቀስ እንደተሞከረው ኢትዮጵያዊያን ለዘመናት
በሀዘን በደስታ አብሮ ከኖሩበት ህዝብ፤ በጋብቻ፤ በባህል፤ በቋንቋ፤ ከተዋሄዱበት
በማህበራዊ ውሏቸው የተሳሰሩትን፤ ከለመዱበት ሕዝብና አኗኗር በመነጠል
በኃይል እንዲፈናቀሉ እየተደረገ ነው፡ ፡ ይህ ድርጊት የበረሃው ንድፈ-ሀሳብ
ቀጣይ ምዕራፍ ነው እንጂ አዲስ ስትራቴጂ ያለመሆኑን የኢትዮጵያ
ሕዝብ፤ የኢትዮጵያ መንግሥት፤ የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በቅጡ ይረዳሉ የሚል
እምነት አለኝ፡፡
በመጨረሻም በይዞታችን ላይ እንሞታለን ላሉት፡- ከላይ በተጠቀሰው ቀበሌያትም
ሆነ በሌሎች አከባቢዎች ተመሳሳይ ዕጣ የገጠማቸው፤ እንዲሁም ገና ለገና መች
ተመሳሳይ ነገር ይደርስብኛል በሚል ፍርሃት ውስጥ ገብታቸው የስጋት እንጀራ
የምትበሉ እንድትጠነክሩ ላበረታታችሁ እወዳለሁ፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ “ዛሬውኑ
ውጡ!” ስትባሉ “አንወጣም”፤ “ሂዱ!” ስትባሉ “ወደት? ...እንደትና በምን
ምክንያት እንለቃለን? ይህንን ያህል ዘመን ኖረን ዛሬ ምን ተዓምር ተፈጠረ?
ሀገራችን የት ነው? ወ.ዘ.ተ” በሚል ክርክር፣ ጭቅጭቅና ግጭት ውስጥ
በመግባት ለራሳችሁና ለጎረበቶቻችሁ እየታገላችሁ ከአቅማችሁ በላይ ከሆነው
ኃይል ጋር ተላትማችሁ፤ የአልሞ ተኳሾች ባሩድ ራት በመሆን ውድና
መቀየሪያ የሌለውን ሕይወታችሁን ላጣችሁት ለእነ አስቻለው ፋንታ፤ አቶ
ቤዛ ታደሰ፤ አቶ ዋና የኔዓለም፤ አቶ ስራው አሰፋ፤ እንዲሁም ለከባድ የአካል
ጉዳት ለተዳረጉት ለእነ አቶ አልማው ገበየሁ፤ እንዲሁም ከሁለት ወራት በፊት
በተመሳሳይ ሁኔታ ሕይወታቸውን ላአጡ ለ7ቱ ሰዎች ቤተሰቦቻቸው እግዚአብሔር
መጽናናቱን እንዲሰጥ እየፀልይኩ ለእኛ የተጠላችሁ ብሔርም አይደላችሁም፤
ትርፍ ዜጎችም አይደላችሁም ስለዚህ እንወዳችኋለን፡፡ በአንድ ወቅት ልክ እንደ
አሁኑ ኢህአዴግ በገዥው መደብ ላይ የተቀመጡ ጥቂት የአማራ ተወላጆች
በሠሩት ግፍ እናንተ የአሁኑ ዘመን ዜጎች አትኮነኑም፡፡ ዕዳ ካፋይም አይደላችሁም፡፡
ለአሳዳጁ ፈርኦንም አንድ ነገር ለማለት እወዳለሁ አማራዎች ብቻቸውን
አይሰደዱም! ብቻቸውን አይሞቱም! ሀዘናቸው ሀዘናችን፤ መከራቸው
መከራችን ነው!! በጨለማውም ሆነ በብርሃን አብረን እንደኖርን ሁሉ
መከራውንም አብረን ለመቀበል መቁረጣችንን ልትረዱ ይገባል፡፡ “ነገ በኔ”
በሚል ስሜት ብቻም ሳይሆን ዘመናትን ከተሻገረው ቤተሰባዊነት፤ በመንፈስ
አንድነት፤ በደም፤ በቋንቋ፤ በሃማኖት፤ በጋቢቻ ትስስር፤ ምክንያት አብረን
እንሞታለን፣ ብሶታችው ብሶታችን፤ ጉዳታችው ጉዳታችን፤ ሞታችው
ሞታችን፤ ጉዳያቸው ጉዳያችን መሆኑን ደግመን ደጋግመን ማረጋገጣችን እንዲታውቁልን እንወዳለን፡፡
ኢትዮጵያችን ፈጣሪ ከኢሕአዴግ ይጠብቃት!!