ወያኔ ኤርትራዊ ስደተኛ የሳዋ ሰልጣኞችን ለማስታጠቅ እየመለመለ ነው::

ከወያኔው የጁንታ ዋና መዘውር መለስ ዜናዊ ሞት በኋላ ተደናግጦ የሚገኘው የወያኔዎች
ስብስብ በቅርቡ እየተደረገ ያለውን የዲያስፖራውያን እንቅስቃሴ እና በምርጫ ወቅት
የተደረጉትን ህዝባዊ መልሶች በመፍራት ባለው ሰራዊት እና በፖሊስ ሃይሉ
በተጨማሪ በተለያዩ ጥቅማጥቅሞች በመደለል  ተስፋ የቆረጡ ኤርትራውያን ስደተኞችን
ለስልጣኑ ማስረዘሚያ ይሆነው ዘንድ ለማስታጠቅ እየመለመለ መሆኑን የውስጥ አዋቂ
ምንጮች ለምንሊክ ሳልሳዊ ጠቁመዋል::

በአዲስ አበባ እና በትግራይ እንዲሁንም በጎንደር አከባቢ እየተበራከቱ የመጡትን እነዚሁ
 ስደተኞች በመጀመሪያ ዙር ፈቃደኛ የሆኑ የሳዋ ሰልጣኞችን በመለየት እና አንዳንድ
ፖለቲካዊ የሆኑ ኦረንቴሽኖች በመስጠት አባላት እንዲሰበስቡ እና አማርኛ መናገር
የሚችሉትንም ለየተው እንዲመለምሉ መመሪያ ተሰጥቷቸው እየሰሩ መሆኑን ታውቋል::
ኦረንቴሽኑን ያጠናቀቁና ስራቸውን የጀመሩት ኤርትራውያኑ በመጀመሪያ ያተኮሩት የውጭ
 እድላቸው የሞተባቸውን;ገንዘብ ላኪ ዘመድ የሌላቸውን ኤርትራ ውስጥ ቤተሰቦቻቸው
በዝቅተኛ ደረጃ የሚኖሩትን;ተስፋቸው የመነመነውን ሲሆን አስፈላጊውን የጥቅማጥቅም
መደለያዎችን በመንገር እና ገንዘብ በመስጠት እንዲሁም የሳዋ የተማሩን የጸረ ኢትዮጵያ
ትምህርት በማስታወስ መሆኑን ምንጮቹ ለምንሊክ ሳልሳዊ ጠቅሰው አማርኛ የሚናገሩ
 ኤርትራውያን ስደተኞችን ደሞ በደህንነት ትምህርት አሰልጥኖ ጆሮ ጠቢ እና ነብሰገዳይ
 ለማድረግ እየተንቀሳቀሱ ነው ብለዋል::