የአዲስ አበባ ሰው በላ ምድር ቤቶች ክፍል አንድ


የአዲስ አበባ ቆይታዬ ምንሊክ ሳልሳዊ 22/04/13 11:27
ከህዝቡ ፊት ላይ ቁጭት እልህ ስብራት ጉስቁልና.....ታነባለህ አዲሳበቤው መሳቅ በህግ የተከለከለ ይመስል አይስቅም ቢስቅም ለሳቀው ሳቅ ቫት የሚከፍል እየመሰለው ግራ ቀኙን ገላምጦ በሰቀቀን ነው:: ድሮ በራቸውን በርግደው የነበሩ
የቤት እመቤቶች አሁን ገርበብ አድርገው እንዳይገፋ በምናምን ያስደግፉታል ዶሮ ማነቂያ አከባቢ.....በየመንገዱ በሞባይል ከሚያወሩ በተጨማሪ የእነሱን 49 እጥፍ የሚሆነው መንገደኛ ብቻውን እያወራ(THINKING ALOUD)ይተማል::
የታክሲው የአውቶብሱ የዳቦው ...ኑሮ ዉድነቱንም ለማውራት ወረፋ .....የምኑ ሁሉ ነገር ወረፋ አለው ...ፌዴራል ፖሊሱ ራሱ ሊገርፍህ ሲፈልግ በወረፋ ነው የሚያንበረክክህ ::..ያልከፋውን ለማየት አዲስ አበባ ሆነህ አውሮፓ የሚታተሙትን መጽሄቶች ማየት ነው:: አዲስ አበቤዎች ሃብታም እና ባለስልጣን አትለይም ሁሉም ደረቱን ገልብጦ ከአራት ኪሎ ወደ ቦሌ ሲከንፍ ከደንበል ላይ ሆነህ ማነጣተር ነው ..እንደ ደርግ ጊዜ አሁንም በዚህ መስመር ግራና ቀኝ ያሉ ህንጻዎች በደህንነት ቢሮዎች የተሞሉ ናቸው ግንባራቸው ሌላ ከጀርባ ስለላ ....... https://www.facebook.com/photo.php?fbid=10151591885514743&set=pb.639339742.-2207520000.1367156048.&type=3&theater
ጫካ ገብቶ መበርታት ከጀመረበት እና ሱዳን ላይ የተደላደለ የመሸጋገሪያ እርከኖችን ካገኘበት ጊዜ አንስቶ ወያኔ አለማቀፍ አሸባሪ እና ማፊያ ቡድን መሆኑ የታወቀ እና እስካሁንም ከመዝገብ ላይ ያልተፋቀ መሆኑ ይታወቃል::ከሱ ለመስተካከል የሚራወጡ ሆኖም ያልተሳካላቸው ደሞ እየተፈጠሩ እየከሰሙ እየተፈጠሩ ነው....እነሱ ቀድመው ካልተናገሩ በስተቀር ሁሉ ነገር ከወያኔ የሚመጣ የሚመስላቸው ባዶ ካርቶን ዲያስፖራዎች ሰው አናት ላይ ሊሸኑ ይፈልጋሉ::
በእርግጥ አንገብጋቢ የህዝብ ጥያቄዎች ሲበረቱበት ወያኔ የሚፈጥራቸው የሃሰት ተባራሪ የአየር በኣየር ፕሮፓጋንዳዎች ባንድ ጊዜ ተለግተው አለምን ያዳርሳሉ :: ይህ ዛሬ ሳይሆን ከጅምሩ የተረጋገጠ ጉዳይ ሲሆን አልተነቃብኝም የሚለው ወያኔ ይህንን ይዞ እየተመመ ነው:: አንዳንድ ግዜ ደግሞ የዜና ማሰራጫዎች ከወጡት ዜናዎቻቸው ላይ የተወሰዱ ጉዳዮችን እና ሌሎች አላስፈላጊ ነገሮችን በወያኔ ላይ መለጠፍ አንድም የዲያስፖራው ስንፍና ነው ሌላም የትግል ድቀት ውጤት ነው:: ይህን አጋጣሚ ተጠቅሞ እንዴት እንደተሰራጬ ማጋለጥ እንጂ ሁሉንም የወያኔ ቋንቋ ማድረግ የዋህነት አይመስልም:: አብዛኛው ተቃዋሚ ነን የሚሉ ፓርቲዎች እና ግለሰቦች ካለምንም አላማ በጥላቻ እና በስድብ ላይ ተመስርተው በእጅ ቅሰራ ላይ ስለተመረኮዙ ሁሌ እንዳወሩ ይኖራሉ::April 24 2013

....አዲስ አበባ ለሊት 8 ሰአት አከባቢ......ደቡብ አፍሪካ ኤምባሲ መዳረሻ ወደ ሳር ቤት የሚወስደውን መንገድ እንደያዘን የስራ ቋንቋቸውን ትግሪኛ ያደረጉ የፌደራል ደህንነት አባላት ፊቴን በጥቁር ከረጢት መሰል ጨርቅ ሸፈኑት ...ወደየት መስመር እንደወሰዱን ባይታወቀኝም .....መድረሻው ግን ከአዲስ አበባ ደህነነት አፋኞች በአንዱ የሆነው የምድር እስር ቤት ቅርንጫፍ ውስጥ ነው...በተለያዩ ጊዜያት የታፈኑ እና ቤተሰቦቻቸው የት እንዳሉ የማያውቋቸው መልካቸው በጸሃይ እጥረት የገረጣ ቢጫ የሆኑ ሰዎች በጨለማው እስር ቤት አሉ ...አንዱ ካንዱ ማውራት አይችልም ...ለማውራት ከተፈለገ የግዴታ ኡዚ የታጠቁ የውስጥ ሲቭል የለበስኡ የደህንነት ሃይሎችን ማባበል አለብህ ... በግምት ወድ 60 የሚጠጉ ሰዎች በዚህ የምድር ውስጥ እስር ቤት አሉ ::.....
ሰውነተህን የሚረብሹ ራስህን እንዳትቆጣጠር የሚያደርጉ ጨካኝ የትግራይ ተወላጆች በቁጣ በጥያቄ አጣደፉኝ ...ፍርሃትን ሳይሆን ድፍረትን መላበስ እንዳለብህ ፊታቸውን ማንበብ ያንተ ድርሻ ነው......በተሰቦቼ ቀድመው ለባለቤቴ የቅርብ ቤተሰብ የሆነ አንድ ከፍተኛ ባለስልጣን እና ለምዕራባዊ ዲፕሎማት ለሆን የደህንነት አታቼ የዜግነት ፓስፖርቴን አያይዘው ባቀረቡት መሰረት ...ከእንግልት ውጥቼ በ24 ሰአት ከሃገር እንድወጣ ታዘዘ....ዝርዝሩን ይጠብቁ.........April 27 2013

እያንዳንዱ የሰው ልጅ ባለንበት ምድር በዚህ ስልጣኔ በተተኮሰበት ዘመን ነጻነቱን ይፈልጋል:: ነጻነቱን እና መብቱን የማይፈልግ ሰው አለ ማለት መዘባበት ሲሆን እንሰሳት እንኳን ስልጣኔ ገብቷቸው በአሁኑ ጊዜ እያንዳንዱን እንቅስቃሴያቸውን  በሚገርም ሁኔታ ቀይረውታል::በአላማችን የሰው ልጆች ነጻነታቸውን ተነፍገው በእስር እና በዱላ እየተገዙ ያሉባት አፍሪካ በተለይ ምስራቅ አፍሪካ አነጋጋሪ ከሆነች ቆይቷል:;በአከባቢዋ የሚነሱት መሪዎች የራሳቸውን የስልጣን ጊዜ ለማስረዘም የምእራባውያንን ብሄራዊ ጥቅም በማስከበር በዙሪያቸው በሰበሰቡት ድጋፍ ህዝብን በሰቆቃ ውስጥ እያሰቃዩት ሲሆን የሚበላው ያጣ ህዝብ አንድ ቐን መሪውን ይበላል የሚለው አባባል በፍጹም ሊገባላቸው አልቻለም::

ከነዚህ የምስራቅ አፍሪካ ተጠቃሽ አገሮች አንዷ አገራችን ኢትዮጵያ ስትሆን ላለፉት 2 አስርተ አመታት ከፍ ባለ መልኩ የተለያዩ ህዝባዊ ሰቆቃዎችን ስናስተናግድ የኖርን ሲሆን በአሁኑ ወቅት በፖለቲካ በኢኮኖሚ እና በማህበራዊ መስክ ያሉት ሁነታዎች ከአቅም በላይ በመበላሸታቸው ተቆጣጣሪ እና እርስ በርሱ የሚደማመጥ መንግስት አለመኖሩ እንዲሁም አመራሮች አይናቸውን በሙስና በጨፈኑ ባለስልጣናት መሞላቱ ህዝቦች ለመከራ ሃገርም ለመሞት ቋፍ ውስት ናቸው ::የድረሱልኝ ጥሪም እያሰሙ ነው::
ከላይ እንደተጠቀሰው ሰዉ በከፍተኛ የኑሮ ድቀት ውስጥ ሆኖ ለኣእምሮ በሽታ የተዳረገ መሆኑ የአደባባይ ምስጢር ነው::ያም አልበቃ ያለው ህዝብ ነጻነቱን ተነፍጎ መብቱን ተገፎ አንገቱን ሰብሮ እንዲሄድ እየተደረገ መሆኑን መደጋገም የማያሻው ሃቅ ነው::
ራሱን ኢሕኣዴግ ብሎ የሚጠራው ሆኖም በጥቂት በጣት በሚቆጠሩ የሕወሓት ታጋይዮች የሚመራው መንግስት የፈጠረው የወያኔ ጁንታ ሳይሆን በዘረኝነት ላይ የተመረኮዞ የትግሬ ጁንታ መሆኑን ላረጋግጥላቹህ እወዳለሁ:: ለናሙና ያህል በስልጣን ላይ የተቀመጡ ዜጋ ነን ባዮች በተለጣፊነት ተጠፍጥፈው የተሰሩ ባዶነት በውስጣቸው ያለ የፈሪ ልባሞች እየተገዙ ያሉት ለጥቂት የትግሬ ጄኔራሎች ሲሆን በፍጹም ስልጣን እንዳሌላቸው እና በሃገሪቷ ውስጥ እየተፈጸመ ስላለው ሁኔታም መረጃ እንዳሌላቸው በራሳቸው አንደበት መስክረውልኛል::
በሃገሪቱ በተለያዩ አከባቢዎች የተከፈቱ የደህንነት ማፈኛ ቤቶች እና የምድር ለምድር እስር ቤቶች ከተወሰኑ የትግሬ ጁንታዎች በስተቀር በትግል ሜዳ ነበርን የሚሉ ተብኣዴን ታጋዮች እንኳን አያቋቸውም :: ይህንን ጉዳይ አስመልክቼ የጠየቋቸው በኢሚግሬሽን እና ደህንነት ቢሮ የሚሰሩ አንድ ከፍተኛ የብኣዴን ባለስልጣን እና ታጋይ የነበሩ ግለሰብ እንደ ወዳጅነታቸው የሚደብቁኝ ነገር ባይኖርም ይህንን ጉዳይ ግን በፍጹም እንደማያቁ ነግረውኛል::
ወደ ኢትዮጵያ ውስጥ የገባሁት ማንኛውም ሰው እንደሚገባው ባይሆንም ...አዳማ ለተወሰኑ ቀናቶች በመቆየት አስፈላጊውን መረጃዎች በመሰብሰብ ወደ አዲስ አበባ አቀናሁ አዲስ አበባ እንደወትሮ እየዘለቁ መውጣት እንደለመድኩት መስሎኝ ነበር ሆኖም በአሁኑ ጥብቅ የሆነ አጋጣሚዎች አጋጠሙኝ:: ከድሮዎቹ ወዳጆቼ አብዛኛዎቹ በሃገር ቤት የሉም .....የደህንነት አባላት የነበሩ ለትምህርት ወደታላኩበት ሄደው በዛው ወያኔ ደህና ሰንብት ብለዋል:: አሁን የቀሩት ለስርኣቱ ታማኝ የሆኑና ባቋራጭ የቶጀሩ የትግራይ ተወላጆች  ናቸው ...መረጃ ለመለዋወጥ እና አስቀድሞ አንዳንድ እርምጃዎች ለመውሰድ ከቀድሞ በተለየ ሁኔታ አዳጋች ነበር::
.....አፕሪል 25 ሃሙስ ማምሻውን ከአንድ ወዳጄ ጋር አምሽቼ ወደ አረፍኩበት አከባቢ ከመሄዴ በፊት መጠየቅ የነበረበት ሰው ስለነበር አብረውኝ ካሉ ሰዎች ጋር ወደ እሱ መኖሪያ ጎራ ብየ ካመሸው በኋላ እኩለ ለሊት ቢይልፍም ወደ ማደራዬ አዘገምኩ:: በማደራዬ ሳልደርስ ግን ያጋጠመኝ ለኔ አዲስ ነገር ነው:አዳዲስ 6 ፊቶች.....ከፊት ለፊት ካቆሙት እና ታርጋ ካሌለው መኪናቸው /እንደማስበው ይህ መኪና በቀን አገልግሎት ላይ አይውልም/ ወርደው በትግሪኛ ወሬያቸውን ቀጠሉ....  እኔን ግን አልነኩኝም ነበር ....አላማቸው እኔኑ መክበብ ስለነበር መሃል አስገቡኝ ...አብረውኝ የነበሩት ቤተሰቦቼ እና አንድ ምእራባዊ ሰው ተደናግጠዋል...ሞባይሌን እና የኪስ ቦርሳዬን በተቀመጥኩበት ወንበር ሰር አስገባሁት....አንደኛው አፌን አሸተተው አልጠጣሁም...ወንደሜ ትፈለጋለህ ውረድና ከእኛ ጋር እንሄዳለን አሉኝ ..ኦኬ  አልኳቸው አላቅማማሁም የተለመዱ ድርጊቶችን አውቃቸዋለሁ...ለእኔ አዲስ ነገር አይደለም.....እንዴ አትፈራም አታንገራግርም እንዴ አለኝ አንደኛው ፈታ ባለ አማርኛ ወደ ዘመናዊ ቶዮታ ላንድክሩዘራቸው ላይ እየተሰቀልኩ ከኋላ መቀመጫ በመሃል አስገብተውኝ ሁለት ከፊት ሁለት ከጀርባጭን ተጭነን በረርን ..በወሎ ሰፈር አድርገን በጎተራ ወደ ቄራ.....
ለሊት 8 ሰአት አከባቢ......ደቡብ አፍሪካ ኤምባሲ መዳረሻ ወደ ሳር ቤት የሚወስደውን መንገድ እንደያዘን የስራ ቋንቋቸውን ትግሪኛ ያደረጉ የፌደራል ደህንነት አባላት ፊቴን በጥቁር ከረጢት መሰል ጨርቅ ሸፈኑት ...ወደየት መስመር እንደወሰዱን ባይታወቀኝም .....መድረሻው ግን ከአዲስ አበባ ደህነነት አፋኞች በአንዱ የሆነው የምድር እስር ቤት ቅርንጫፍ ውስጥ ነው...በተለያዩ ጊዜያት የታፈኑ እና ቤተሰቦቻቸው የት እንዳሉ የማያውቋቸው መልካቸው በጸሃይ እጥረት የገረጣ ቢጫ የሆኑ ሰዎች በጨለማው እስር ቤት አሉ ...አንዱ ካንዱ ማውራት አይችልም ...ለማውራት ከተፈለገ የግዴታ ኡዚ የታጠቁ የውስጥ ሲቭል የለበስኡ የደህንነት ሃይሎችን ማባበል አለብህ ... በግምት ወድ 60 የሚጠጉ ሰዎች በዚህ የምድር ውስጥ እስር ቤት አሉ ::.....
ሰውነተህን የሚረብሹ ራስህን እንዳትቆጣጠር የሚያደርጉ ጨካኝ የትግራይ ተወላጆች በቁጣ በጥያቄ አጣደፉኝ ...ፍርሃትን ሳይሆን ድፍረትን መላበስ እንዳለብህ ፊታቸውን ማንበብ ያንተ ድርሻ ነው......
የሄድኩበት አከባቢ ይህ ነው በዬ መናገር ባልችልም በመካኒሳ በሳር በት እንዲሁም ምናልባት ከ አሮጌው አይር ማረፊያ ጀርባ ይሆናል በዬ እገምታለሁ::.......በደህነነት ማፈኛው የምድር ውስጥ ክፍል ፊቴን እንደገለጡኝ 3በ4 በሆነች ውስጥ 4 ወንበር እና ጠረጰዛ አለ:: አንድ ተብታባ ትግሬ በወጉ አማርኛ የማይናገር ፊቱ ላይ ጭካኔ የሚነበብበት ሰው አንዱን ጓዱን አስከትሎ መጣ ... ሰላምታ የለም  ....ከዱላ በፊት መናገር ያለብህን ትናገራለህ አለኝ...ስለምን ነበር የመለስኩለት  ስለምትተየቀው ....መጀመሪያ የባለስልጣናትን ስም ታጠፋለህ መረጃ ከየት አመጣህ .....መረጃውን የሚሰጠኝን ማወቅ ከፈለክ አሁን ይደውልልሃል ከዛ ታውቀዋለህ  እናንተው ታወጡት እና እናንተው ትጠይቃላቹ ..ይህ ደሞ እናንተንም እኔንም ከተጠያቂነት አያድንም ... ቆይ ግን ድፍረትህ ማንን ተማምነህ ነው?  ወንድምህን ብየ መለስኩለት ....ምንም ማውራት አልፈለገም....ውሰደው አለኝ.... ወሰዱኝ
የምድር ቤቱ ገበና ...አብዛኛው ከጨለማ ክፍሉ ተንቷል የተወሰኑ ሰዎች በትንሿ መስኮት በኩል ግማሽ ፊታቸው ይታያል በኮሪደር እንጅ ለነሱ መብራት የለውም ...አንድ ድምጽ ሰማሁ  ወርኪቾ ነኝ ገደባኖ የሚል ያዝኩት የተናገረውን ...ፊታቸው ቢጫ የሆኑ ሰዎች በአንድነት ለችንት ቤት በሚል ከለሊቱ 9.30 ላይ ወተው እዛው ምድር ቤት ካለ መጸዳጃ ቤት አተርታ ይዘውል 14 መጸዳጃዎች አሉ ...ቆጠርኩ ላያቸው ስጠጋ መለሱኝ ..ያንተ ጉዳይ ገና ነው አለኝ አንዱ መቀላቀልሽ አይቀርም አትቸኩይ ...ነብሲ አለኝ ሌላኛው.....ይቆይ የተባልኩበት ክፍል ሆኔ እንዳለሁ 10.32 ደቂቃ ሲል ተጠራሁ...እስከዛ ጊዜ ድረስ አልፈተሹኝም ....ምንም የመታኝ የተናገረኝ ሰው አልነበረም  .....ሰው ይፈልግሃል ተባልኩ ፊጠ ተሸፈነ  መኪና ላይ ጫኑኝ  ወሰዱኝ..ራሴን ያገኘሁት አዲሱ ገበያ ተብሎ ከሚጠራው አከባቢ ማንጊያው ላይ ነበር...ይቀጥላል....