መንግስቱ ሃይለማርያም ምስራቃዊትዋ የድንበር ከተማ ቩምባ ከነቤተሰቡ በህይወት አለ::

የመንግስቱ ሃይለማርያም ሞት እያነጋገረ መጥቷል ሆኖም ግን በዚምባብዌ ታዋቂ የሆነው ድረገጽ ወሬውን አስተባበለ። ዜናውን አሰራጨ የተባለው ሚዲያ ኒው ዚምባብዌ   http://www.newzimbabwe.com የተባለ የሃራሬ የዜና አውታር ነው።

 የቀድሞው የኢትዮጵያ ወታደራዊ መሪ የነበሩት ኮ/ል መንግስቱ ሃይለማሪያም ከነበሩበት ሃራሬ ጋንሂል ገስት ህውስ ተነስተው ወደ ምስራቃዊትዋ የድንበር ከተማ ቩምባ አከባቢ መሄዳቸው ከ 6 ወራት በፊት ሰምተናል ::
በጥቅምት 2007  ኮሎነል መንግስቱ መሞታቸውን የሚናገሩ ዜናዎች ተሰምተው ነበር አንዲሁም ባለቤታቸው ው/ሮ ዉባንች  አንደሞቱ ተሰምቶ ነበር ::
ሆኖም ሁሉም ስህተት አንደነበር የምናስታውሰው ጉዳይ ነው::
አሁንም በዚህ ሰሞን የተለቀቁ ዜናዎች አንደ ሚያመለክቱት ኮሎኔሉ እንደሞቱ የሃገሪቱን ቴለቭዥን ጣቢያ ጠቅሰው ዘግበዋል::      

ዛሬ ማምሻውን የወጡ መረጀዎች እንደጠቆሙት ኮሎነሉ በእርግጥ ወደ ሆስፒታል የገቡ ቢሆንም የህን ያህል የሞትአደgaእንዳላጋጠማቸው እና የሚዲያ ስህተቶች የፈጠሩትነውሲሉ ለቤተሰባቸው ቕርብ የሆኑ ምንጮች ተናግረዋል:: በልብ በሽታ የሚሰቃዩት ኮሎኔሉ በተለያዩ ጊዜያት ወደ ህክምና አከባቢ እንደሚሄዱም ምንጮቹ አልሸሸጉም::