ከካርቱም እና ከሪያድ ከመጡ ግለሰቦች ጋር ኮሚቴዎቹ የሚፈቱበትን ድርድር ወያኔ እያደረገ ነው::

ኮሚቴዎቹ ንጹህ እንደሆኑ ሙስሊሙ አይደለም ክርስቲያኑም ህብረተሰብ ያምናል::

የሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ነጻ የሚያወጣቸው ንጽህናቸው እንጂ ድርድር አይደለም::
የወያኔ ጁንታ አምባገነን መሪዎች በህጋዊነታቸው የሃገር አደባባይ ያወቃቸውን እና በሙስሊሙ የተመረጡ ኮሚቴዎችን ካለምንም ወንጀል በማሰር በወህኒ የህሊና እስረኛ አድርጎ አስቀምጧቸዋል የተመሰረተባቸውም ክስ ማስረጃ አይደለም የክሱ ሂደት እንኳን የህግ ቅድመተከተል የሌለው እንደሆነ በኣለማቀፍ የህግ ባለሙያዎች የተረጋገጠ መሆኑ እሙን ነው::

ይህን ተከትሎ ፍትህ በራቀችበት አገር እነዚህ ኢትዮጵያውያን በወህኒ አጉሮ በዝግ ችሎት ለመዳኘት በሚደረገው ንጥር ሃስት ዉስጥ ወያኔን አስቀምጠን ሁኔታዎችን መከታተል በያዝንበት ሰኣት ማንነታቸው ከማይታወቁ ከካርቱም እና ከሪያድ ከመጡ ግለሰቦች ጋር ኮሚቴዎቹ የሚፈቱበትን ድርድር ወያኔ እያደረገ መሆኑን የራሱ ዲፕሎማቶች መረጃውን አድርሰውናል::

ማለት የምንፈልገው ጉዳይ ቢኖር ተደራዳሪዎቹን ማን እንደወከላቸው እንደት እንደተወከሉ ምንም መረጃ የሙስሊሙ ህብረተሰብ የሌለው ሲሆን ከድርደሩ አንዱ አካል የሆነ ታሳሪዎችህ ኮሚቴዎች ከተፈቱ በኋላ ከሃገር እንዲወጡ ግፊት ማድረግ የሚለው ዜጋ በሃገሩ እንዳይኖር በአለማቀፍ ደረጃ የተደነገጉ ህጎችን የሚጥስ ተግባር መሆኑን ለማረጋገጥ እንፈልጋለን::ይልቁኑ : "ኮሚቴዎቻችንን በአስቸኳይ ፍቱልን!!!"ምንሊክ ሳልሳዊ

ከዚህ ቀደም የኦጋዴን ነጻነት ታጋዮችን አስሮ የነበረው ወያኔ በተደረገበት ግፊት የተነሳ የታጋዮቹ የክስ ሂደት በዝግ ችሎት ስም የተካሄደ ያለ በማስመሰል ከኦብነግ ጋር ተደራድሮ የታሰሩ ታጋዮችን በኬንያ በኩል ካገር እንዲወጡ ያደረገበት የፖለቲካ ንግድ የሚታወስ ነው::
ይህን ድርድር ተከትሎ በዚህ ሰሞን ባለ33 ገጽ እና ባለ 46 ገጽ የትግል ይቁም ማኒፌስቶዎች ታትመው እየተበተኑ ነው::
አሁንም ይህንን ለመጠቀም እና የተሳሳተ መረጃ ለህዝብ ለማድረስ ቢሞከር ማንም የሚሰማ ጆሮ የሌለው መሆኑን ጠንቅቃችሁ ታውቃላቹህ :: እናንተ ወያኔዎች ሳትነሱ ቀድመን ለሙስሊሙ ህብረተሰብ ማስጠንቀቂያ ሰተናል እናም ኮሚቴዎቹ ንጹህ እንደሆኑ ሙስሊሙ አይደለም ክርስቲያኑም ህብረተሰብ ያምናል ስለዚህ የምንለው ነገር ቢኖር ኮሚቴዎቹ ንጽህናቸው እንጂ ድርድር ነጻ የሚያወጣቸው መሆኑ ሁላችንም የምናውቀው ሃቅ ነው:: "ኮሚቴዎቻችንን በአስቸኳይ ፍቱልን!!!"