የኢትዮጵያ አየር መንገድ ኪሳራ ያሰጋዋል;ወያኔ ሊሸጠው አሰፍስፏል::በቅርብ ጊዜ ጀምሮ በዘረኞቹ መዳፍ ስር የወደቀው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ማኔጅመንት ከፍተኛ የሆነ ኪሳራ ሊያጋጥመው ይችላል ሲሉ የውስጥ አዋቂ ምንጮች ሲገልጹ ኪሳራውን ተከትለው ከወያኔ  ጋር በመቧደን አየር መንገዱን ለመግዛት የመካከለኛው ምስራቅ ቱጃር አየር መንገዶች አሰፍስፈው እየጠበቁ መሆኑን እነዚሁ ምንጮች ጠቁመዋል::

ባለፈው ሰሞን የኢማራትያ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ጉብኝት ተከትሎ በአየር መንገዱ የስራ ሂድት ላይ ወከባ እየፈጠሩ የሚገኙት የማኔጅመት አባላቱ በዘረኝነት በታወረው አመራራቸው የተለያዩ አስተዳደራዊ በደሎችን እየፈጸሙ እንደሚገኙም እነዚሁ ምንጮች ተናግረዋል::አየር መንገዱ የተለያዩ የሰለጠኑ ባለሙያዎቹ በፖለቲካ በተከበበው አየር ላለመስራት ፍላጎት አለማሳየታቸው እንዲሁም አገር እየጣሉ በሌሎች አየር መንገዶች መቀጠራቸው ሌሎችም አገር ጥለው በመኮብለላቸው በተጨማሪም በፖለቲካ እምነት እና በሃይማኖት ሰበቦች የተባረሩ ስልጡኖች መበራከታቸውን ጨምሮ የወያኔ የዘር ፖለቲካ ምህዳር በመስሪያ ቤቱ መስፋቱ እና የደህንነት ሃይሎች የዘረጉት የስለላ መዋቅር እንዲሁም ባለስልጣናት ከማኔጅመንቱ ጋር በጋር የሚፈትሉት የሙስና ዘይቤ አየር መንገዱን ለኪሳራ እንደዳረገው እየተነገረ ነው::
በዚህ ሰሞን እንኳን አየር መንገዱ ለማስገባት ካቀደው 27 ፐርሰንቱን በኪሳራ እንዳጣ ታውቋል:: የማንጅመንቱ በፖለቲካ መዘውር ውስጥ በዘረኝነት ታጥሮ ሌላውን ኢትዮጵያዊ ሃገሩ እንዳይመስለው እና እንዲሰደድ እያደረገ መሆኑን ምንጮጫችን ተናግረውል:: አየር መንገዱን በኪሳራ ሰበብ እና በአክሲዮን ባማመካኘት ለአረብ ባለሃብቶች ለመሸጥ እና ገንዘቡን ለመቀራመት አሰፍስፈው ያሉትን የወያኔ ባለስልጣናት መዋጋት ያስፈልጋል::