አደገኛ የሕወሓት የሙስና ሰደዶች ከነውርንጭሎቻቸው ሲጋለጡ !!!


አሃዞቹ ምን ያህል የወያኔ ባለስልጣናት 10 መንግስታዊ ድርጅቶችን ተገን በማድረግ በሙስና እንደተዘፈቁ እና ሊዘፈቁ እንዳሰቡ ያመለክታሉ::
እጅ ከፍንጅ ተይዘው በ....ትእዛዝ ተመልሰው ገቢ የሆኑ ወጪዎች... ሆኖም ሙሰኞቹ ስራቸውን ቀጥለዋል::

-የአዲስ አባባ መስተዳድር የመሬት ስራ አመራር ፕሮጀክት ቢሮ በሃሰት ማስረጃ ከመንግስት የእቃ ግዢ መመሪያ በተቃረነ መልኩ ህገወጥ ግዢ ሊፈጸም ሲል ተገኝቶ የ20 ሚሊዮን ብር ፕሮጀችት ተሰርዟል::
-የኢትዮጵያ እህል ንግድ ኢንተርፕራይዝ በህገወጥ መልኩ የቡና መፍጫ ማሽኖች በ5 ሚሊዮን ለመግዛት ሲሞከር ተደርሶበት  ገንዘቡን ተነጥቋል::
-የአዲስ አበባ ስፖርት ኮሚሽን የመሮጫ ካንቫስ በሚል ስም ግልጽ ባልሆነ መንገድ ያወጣው 25 ሚሊዮን ብር ተይዟል::
-ደብረማርቆስ ዩንቨርስቲ በተማሪዎች የምግብ ማሻሻያ ሰበብ ህገወጥ ግዢ ሊፈጽም ሲል ተደርሶበት 291,566 ሺህ ብር ተመላሽ አድርጓል::
-የውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ባለስልጣን በማይጠበቅ እጅግ ከፍተኛ በሆነ ወጪ በስሩ ለሚገኝ የፕሮጀችት ቢሮ በሚል ስም የመስመር ዝርጋታ እና አቅርቦት በማለት 292 ሚሊዮን ብር በህገወጥ መልኩ ሲያወጣ ተደርሶበት ተመላሽ ሆኗል::
-የግብርና ሚኒስቴር በ36.6 ሚሊዮን ብር ህገወጥ የዘር መፍጫ ማሽን ሊገዛ ሲል ተደርሶበታል::
-ዝቋላ ብረታ ብረት ማቅለጫ ፋብሪካ በ25 ሚሊዮን ኢሮ እጅግ የወደቀ እና ደረጃውን ያልጠበቀ ማሽን የገዛ ሲሆን ይህ ማሽን የስራ ጊዜን እና የሰው ጉልበትን የሚጨርስ መሆኑ የተረጋገጠ ሲሆን ማሽኑም ተችኖ ያልመጣ ሲሆን ይህ ማሽን እንዲቀይእር ተሞክሮ እስካሁን ተመላሽ አልሆነም::ምንም ውጤትም የለም::
-የመሬት አስተዳደር ባለስልጣን/እጅግ አደገኛ የመሬት ሙስኝነት/
ሃሰተኛ እና ህገወጥ ሰነዶችን በማዘጋጀት
1- 3,226 ስ.ሜ. መሬት ..21.1 ሚሊዮን ብር የሚገመት ጉዳዩ በፍርድ ሂድት ላይ ያለ
2- 3,837 ስ.ሜ. መሬት ...25.1 ሚሊዮን ብር የሚገመት ጉዳዩ ለህግ ውሳኔ የተላከ
3- 128,000 ስ.ሜ መሬት ...842 ሚሊዮን ብር የሚገመት ጉዳዩ በምርመራ ላይ ያለ..
-የገቢዎች አስተዳደር
47.9 ሚሊዮን ብር የገቢ ታክስ በማጭበርበር ጉዳዩን በማድበስበስ በመሞከር ሲባል የተያዘ ሰነድ ጉዳዩ ለህግ የቀረበ
10.7 ሚሊዮን ብር ለአፋር መስተዳደር ለማስተላለፍ ታስቦ ገንዘቡ በባለስልጣናት የተሰረቀ ሲሆን ባለስልጣኖቹ በቅርቡ ለመክሰስ ዝግጅቱ ተጠናቋል::
-ወያኔ የዘረፋቸው የህዝብ ሃብቶች
146.6 ሚሊዮን ብር + 2.9 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላርስ  በተለያዩ የግዥ እና ከጨረታ ጋር በተያያዙ ጉዳዮች በባለስልጣናት ተዘርፏል::
75.3 ሚሊዮን ብር ለፊንጫ ስኳር ፋብሪካን ለማስፋፋት የደን ምንጠራ የሸንኮራ አገዳ መትከያ እና የመኪና መከራያ በሚል ሰበብ ተዘርፏል::
-ሁለት ዳኞች እና ሁለት ጠበቆች የእጅ በእጅ ሙስና ሲፈጽሙ ተይዘው ጉዳያቸው ለህግ ሊቀርብ ነው::
-የተለያዩ ወንጀሎች
10 ሚሊዮን ብር +200,000 የአሜሪካ ዶላር በመንግስት ከፍተጛ ባለስልጣኖች ተዘርፏል::ገንዘቡን በግል እና በቼክ ማጭበርበር ፈጽመውታል::
6.2 ሚሊዮን ብር ከኢትዮያ አየር መንገድ ተጓዦች የተነጠቀ..ምርመራ ላይ ያለ:;
ምንጩ ያልታወቀ 7.4 ሚሊዮን ብር በባለስልጣናት ዘንት የተገኘ...
3.8 ሚሊዮን ብር  በጉቦ የተገኘ ህጉ በተሻረው የፍራንኮ ቫሉታ ስም እቃዎችን በማስገባት በመፍቀድ ...ህገወትጥ ለሆኑ የውጭ ሰዎች የመግቢያ እና የመውጫ ቭዛ በመስጠት የተገኘ የሙስና ገንዘብ

እስካሁን የዚህ የሙስና ተጠቂ የሆኑ ባለስልጣናት እና ተባባሪዎቻቸው የታገደባቸው/የተያዘባቸው ንብረት እና ገንዘብ
128,709.3 ስ.ሜ.መሬቶች.......28 ዘመናዊ የግል መኪኖች....64 ዘመናዊ መኖሪያ ቤቶች ....11 ድርጅቶች....2.8ሚሊዮን ብር .....15.1 ሚሊዮን ዶላር የተያዘ ሲሆን
አራት ህንጻዎች እና , 1,945 ስ.ሜ መሬት እና 21.1 ሚሊዮን ብር ወያኔዎች ከወያኔዎች ወርሰዋል::