የወያኔ ሰው በላ ምድር ቤቶች በአዲስ አበባ ክፍል ሁለት

የምድር ቤቱ ገበና ...አብዛኛው ከጨለማ ክፍሉ ተንቷል የተወሰኑ ሰዎች በትንሿ መስኮት በኩል ግማሽ ፊታቸው ይታያል በኮሪደር እንጅ ለነሱ መብራት የለውም ...አንድ ድምጽ ሰማሁ  ወርኪቾ ነኝ ገደባኖ የሚል ያዝኩት የተናገረውን ...ፊታቸው ቢጫ የሆኑ ሰዎች በአንድነት ለችንት ቤት በሚል ከለሊቱ 9.30 ላይ ወተው እዛው ምድር ቤት ካለ መጸዳጃ ቤት አተርታ ይዘውል 14 መጸዳጃዎች አሉ ...ቆጠርኩ ላያቸው ስጠጋ መለሱኝ ..ያንተ ጉዳይ ገና ነው አለኝ አንዱ መቀላቀልሽ አይቀርም አትቸኩይ ...ነብሲ አለኝ ሌላኛው.....ይቆይ የተባልኩበት ክፍል ሆኔ እንዳለሁ 10.32 ደቂቃ ሲል ተጠራሁ...እስከዛ ጊዜ ድረስ አልፈተሹኝም ....ምንም የመታኝ የተናገረኝ ሰው አልነበረም  .....ሰው ይፈልግሃል ተባልኩ ፊጠ ተሸፈነ  መኪና ላይ ጫኑኝ  ወሰዱኝ..ራሴን ያገኘሁት አዲሱ ገበያ ተብሎ ከሚጠራው አከባቢ ማንጊያው ላይ ነበር...ይቀጥላል....
የወያኔ ሰው በላ ምድር ቤቶች በአዲስ አበባ ክፍል ሁለት
ባለፈው እንዳነበብነው በምድር ቤት ባለው የወያኔ እስር ቤት ያሉ ከተለያዩ ቦታዎች እንዲሁም ከጎረቤት አገራት የታፈኑ እና በወታደሩ ውስጥ ችግር ይፈጥራሉ ተብለው የታሰሩ ሰዎች ሲሆኑ እነዚህ ቤተሰቦቻቸው የት እንዳሉ እንኳን የማያውቁ ታፋኞች በየምድር እስር ቤት ውስጥ ስንቱ እንዳለ ቤት ይቁጠረው ::
በደረስኩበት የምድር እስር ቤት ውስጥ በትግሪኛ ቋንቋ የሚያወሩ ኡዚ የታጠቁት የድህንነት አባላት ፊታቸውን አፍፈው ነው የሚመለከቱት .. ኡቃቤ አምላካቸው ማንንም አይወድም መሰል ወይም እንዴት እንደሰለጠኑ ባይታወቀኝም ለሰዎች ያላቸው አመለካከት ግን ፊታቸው ላይ ይነበባል::አንተ አንቺ....ሁላችን እነሱ ፊት ርካሽ ትንኞች ነን::እጅግ ጨካኝ መሆናቸውን ከግንባራቸው ታውቃለህ :; ርህራሄ የለሾች ካለፍርድ አስፈላጊ በሆነ ሰአት ሰው በመግደል የደም ጥማቸውን የሚወጡ መሆናቸው ያስታውቃሉ:: በምድር ቤቱ በ5 ሜትር ርቀት የሚገኙት እነዚህ ባለኡዚዎች የደንብ ልብስ ሳይሆን የራሳቸውን ነው የለበሱት:: የደንብ ልብስ የላቸውም::ምድር ቤት ቀዝቃዛ በመሆኑ አብዛኛዎቹ ወፈር ያሉ ልብሶችንን እና የቆዳ ጃኬቶችን ለብሰዋል::አስተያየታቸው ለማያውቃቸው ያስፈራል::......ከነሱ ጋር ከተግባባህ ግን እጅግ መልካም ነገሮችን ታገኛለህ ::አንዱን ወዳጅ ካደረከው ከሚቀርብልህ በላይ በድጋሚ ይቀርብልሃል:: ምግብ ሲጋር ዉሃ ....ግርፋት የቀኑ ከ 5 ወደ 3 ይወርድልሃል:: ወገኖቻችን እየተሰቃዩ በሚገኝበት የምድር ቤት እስር በቶች አንዱን ማየቴ ገመናቸውን አደባባይ እንዲወጣ እግዛቤር እንዳዘዘባቸው እንኳን ሊቆጥሩት አልቻሉም :: እንደዚህ አይነት ስንት እስር ቤቶች እንዳሉ እስኪ ራስዎን ይጠይቁ:: በለስላሳ ብዙ በማያሳዩ መብራቶች ቲኒሽ ኮሽታ በሚሰማበት ጸጥረጭ ባለው የምድር ለምድር እስር ቤት ውስጥ ስንቱ ተገረፈ ተገደለ እዛውስ በሰበሰ??/ያልተመለሰ ጥያቄ ነው::
ለሰአታት በቆየሁበት የሕወሓት ከፍተኛ ሰዎች ብቻ በምስጢር ይቅኦጣጠሩታል በተባለው በዚህ የምድር እስር ቤት ውስጥ ከ60 ሰዎች በላይ ታስረዋል :: ካስፈቱኝ አካላት ለማረጋገጥ እንደቻልኩት ከነዚ ሰዎች 30ፐርሰንቱ የቀድሞ የደርግ መኮንነች የነበሩ እና ከወያኔ የጫካ ትግል ጋር ተቀላቅለው የነበሩ ሲሆን አካሄዳቸው እጅግ የሚያሰጋ እና በወታደራዊ ሳይንስ በምስራቅ አውሮፓ የሰለጠኑ ናቸው...ቀሪዎቹ ደሞ ታጋዮች የነበሩ ሲሆኑ ከባድ የሆነ የሕወሃት ሚስጥሮች በጃቸው ያለ ቢለቀቁ ሕወሓትን ለመጨረሻ ጊዜ መሞቱን የሚያበስሩለት ናቸው ተብለው የተፈሩ ሲሆን እንዲሁም ፓርቲው አዲስ አበባ ውስጥ በሰራቸው ወንጀሎች የተሳተፉ ሰዎችም.... በዚሁ ምድር ቤት ውስጥ ታስረው ይገኛሉ::
በአንድ የስራ ወቅት ያየሁት በሰሜን ሸዋ መውጫ መንገድ ያለው የአለባቸው ጫካ እንዲሁ በደን የተከበበ ሲሆን አሁን ወያኔ ወደ መቀሌ አዘዋውሮቸዋል ተብሎ የሚገመቱት የቀድሞ የኢሕኣፓ አባላት እና ኢትዮጵያውያን ምሁራን ታፍነው ተወስደው የታሰሩበት ቦታ ነበር በአሁን ሰኣት የተወሰኑ የቀድሞ ታጋዮች እና ሻእቢያ በአደራ ያስቀመጠቻቸው ታሳሪዎች ይገኛሉ::
በአዲስ አበባ ታስረው በምድር እስር ቤት ውስጥ የሚገኙ ሰዎች የስርኣት ለውጥ ሳይሆን የሚሹት አዲስ ኢትዮጵያን እና አዲስ ህሳቤን ነው ምክንያቱን ከቀድሞው የስርኣት ለውጥ እንዳየነው ወያኔ ደርግን ሲደመስስ በተለያዩ አከባቢዎች ያገኛቸውን ታሳሪዎች የፈታቸው የተወሰኑትን ሲሆን ሌሎችን እዛው አስሮ አስቀርቷቸዋል::እስካሁንም ያሉ አሉ የሞቱም በምስጢር ተቀብረዋል:: በተለያዩ ዘመናዊ የማሰቃያ ማሽኖች የተደራጁት እነዚህ የምድር ቤት የወያኔ እስር ቤቶች በብዛት የሚገኙት ከአሮገው አይሮፕላን ማረፊያ ጀርባ እና ከብስራተ ገብሬል አከባቢ መሆኑን ውስጥ አዋቂው ሲጠቁሙኝ እንዲሁም በፈረንሳይ ሌጋሲዮን በቦሌቡልቡላ በገርጂ  በካራ በአያት መንደር ውስጥ በገፈርሳ አከባቢዎች በተንጣለሉ ቭኢላዎች ስር በተገነቡ ምድር ቤቶች እየተሰቃየ ያለውን ቤቱ ይቁጠረው::ለሊቱን በአፈና ስራ ላይ የሚሰማሩት ሃይሎቻቸው እንዲሁ አስፈላጊም ከሆን ቀን ለቀን ከፌዴራል ፖሊሶች ጋር በጋራ እንደሚሰማሩ ታውቋል:: ስራቸው ማፈን ብቻ ሳይሆን መግደልም እንደሆነ የተነገረላቸው የጁንታው ጃይንቶች በአዲስ አበባ መኖሪያቤት የላቸውም:; አብዛኛዎቹ የመጡት ከትግራይ እና ከኤርትራ ሲሆን አስፈላጊው ነገር ሁሉ እንደሚሟላላቸው እና ለቤተሰባቸውም እንዲሁ ሁሉም ነገር እንደሚደረግ ሲረጋገጥ ምንም አይነት ምስጢር እንዳያወጡ ከፍተኛ ክትትል አንዱ ባንዱ ላይ ያደርጋል ትንሽ ፍንጭ የተገኘበት መታሰር ሳይሆን ይረሸናል:: አንዱ አንዱን በሚከታተልበት የምድር እስር ቤት ውስጥ የዋህ ሆኖ መገኘት ሳይቀር ያስቀጣል::
ለማጠቃለል ያህል በእነዚህ የወያኔ እስር ቤቶች ውስጥ ስንት የታፈኑ የተገደሉ የሞቱ ኢትዮጵያውያን እንዳሉ ማሰብ የእያንዳንዱ ሰው ግዴታ ነው:: የወያኔው ጁንታ ማንም በማያውቀው ሁኔታ ለሃገር የሚያስቡ እና የሚጭነቁ ወገኖችን በጠላትነት በማየት በማፈን ደብዛቸውን የሚያጠፋባቸው እነዚህን ሰው በላ ምድር ቤቶች ማጋለጥ የእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ግዴታ ነው::ሻሎም