አቶ ሃይለማርያም ለአውሮፓ ህብረት የገባውን ቃል አፈረሰ::የወያኔ የፖለቲካ ፍርድ ቤቱ በእነ እስክንድር ነጋ ላይ ፍርዱን አጸና::


አዲስ አበባ ያሉ ዲፕሎማቶች መታገስ ነው ይላሉ:;
ምንሊክ ሳልሳዊ

ባለፈው የአውሮፓን ህብረት ለመጎብኘት ወደ ብራስልስ ያመሩት አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ በህብረቱ በቆዩበት ጊዜ ተደጋግሞ ሲነሳላቸው የነበረው ጉዳይ የእስረኞች ጉዳይ እንደነበር ይታወቃል ::በዚህም መሰረት በሕወሓት መራሽነት የሚተሙት አቶ ሃይለማርያም እጅግ ጥብቅ የሆነ ቃል ገብተው ወደ ሃገር ቤት መመለሳቸውን የትላንት ዜናችን ነበር :; እንዲሁም ከዚህ ቀደም በተለያዩ ወቅቶች ሟቹ ጠ/ሚ የተለያዩ ገንዘቦችን እና መደለያዎችን ከህብረት በልማት ስም በመውሰድ ቃል እየገቡ ነገሩ ጎትተውት አልፈዋል:: ህብረቱ የልማት እርዳት ሲያደርግ የነበረ በዚህ ጉዳይ ዙሪያ ያለውን የተካረረ ነገር ላማላልት እና ወደ ስብኣዊ መብቶች ላይ ለማተኮር መሆኑን በተደጋጋሚ ገልጿል::

ከወደ አዲስ አበባ ዛሬ በፍርድ ቤቱ አሳዛኝ ፖለቲካዊ ውሳኔን ተከትሎ በሃገር ውስጥ ያሉ የተለያዩ ዲፕሎማቶች ሁኔታው ከማስገረምም አልፎ አስደንግጦናል ሲሉ ተደምተዋል:: ሆኖም የመንግስታቹህን ጭራ ለመያዝ ይከብዳል የሚሉ ዲፕሎማቶች ነገሮችን በትእግስት መመልከት እና መጠበቅ ነው ሁኔታዎች ሊቀየሩ ይችላሉ የውስጥ አጣብቂኞች የፈጠሩት ውሳኔ ይሆናል ምናልባት......የጀመርነውን ዲፕሎማሲያዊ ጥረት እንቀጥላልን ብለዋል::

ዛሬ በጠቅላይ ፍርድቤት የዋለው የፍርድ ሂደት በእስንድር ነጋ የ18 አመት እና አንዷለም ላይ የእድሜልክ እስራት ያጸና ሲሆን ዳኛው የወያኔ ጀሌው ዻኜ መላኩ ክሱም ሆነ ውሳኔው ትክክል እና ምንም አስተያየት ሊደረግለት የማይችል ሲል ከታሪክ ተጠያቂነት የማይድንበትን አስተያየት የሰጠ ሲሆን ሌሎች የጠቅላይ ፍ/ቤ ዳኞች አናየውም ብለው እስከ በላይ አካል ክርክር የተኬደበትን ጉዳይ ከምን ሞራል እንዲህ ሊደመድምበት እንደቻል ጊዜ ይጠይቀዋል::
እንደዚህ አይነት በፍትህ ላይ ጠባብ አመለካከታቸውን እና ጸረ ህዝብ አቋማቸውን የሚያራምዱ ዳኞችን መከታተል እና ከየተደበቁበት ጊዜ ጠብቆ መጋለጥ የዜግነት ግዴታ ነው:: ይህ መንግስት ሲወድቅ በተለያዩ የአውሮፓ እና የአሜሪካ ከተሞች ለመመሸግ እያለሙ የሚገኙት የፍትህ አካላትን መከታተል ግዴታችን ነው::

ከፍርዱ በኋላ "እውነት ነጻ ታወጣናለች!!!" ያለው እስክንድር ነጋ "የጊዜ ጉዳይ ነው እንጂ እውነት በራሱ ጊዜ እንደሚወጣ ለኢትዮጵያውያን ማሳወቅ እንፈልጋለን "ብሏል:የተከሰሱበት ጉዳይ በአሸባሪነት እና አሸባሪ ተብሎ በተፈረጀው ከግንቦት ሰባት ጋር ግንኙነት አላቹህ ተብለው ቢሆንም ከዚህ በፊት ጉዳዩን እንዲያዩት ይግባኙ የቀረበላቸው ዳጛ አማረ አሞኘ ይህን ክስ ለማየት የሚያስችል በቂ ማስረጃ ስላሌለ በነጻ እለቃቸዋለሁ በማለታቸው ጉዳዩ ከሳቸው እጅ ተነጥቆ ፖለቲካዊ ዉሳኔ እንዲሰጥበት ተደርጓል::
በኢትዮጵያ እየተፈጸመ ያለው የፍርድ ቤት ስርኣት እና ውሳኔዎች በአለም አቀፍ ደረጃ አነጋጋሪ ከሆነ ረዥም አመታትን ያስቆጠረ ሲሆን የወያኔ ካንጋሮ ፍርድቤት እና ያልሰለጠኑ በፖለቲካ ታማኝነት ዳኛ የሆኑ ያልበሰሉ ካድሬዎች እየወሰዱ ያለው ህገወጥ እርምጃ እና ውሳኔ ነገ እንደማያስጠይቃቸው ሆነው መታየታቸው ሃገር ምን ያህል በፍትህ እጦት ቀውስ ውስጥ እንደሆነች ያሳያል:; ለግል የወያኔ ጥቅማጥቅሞች እና የኑሮ ምጮት እየተገዙ ያሉት የህግን ከለላ እንኳን ምን ያህል ስሜቶችን መረዳት ያልቻሉ ፍርደገምድል ዳኞችን መፋረድ ግዴታችን ነው::
እስክንድር ነጋም ሆኑ ሌሎች እስረኞች ቀን ሳይረዝም በቅርብ ጊዜ እንደሚለቀቁ ባለሙሉ ተስፋ ስሆን ይህ ደሞ ወያኔ እየደረሰ ያለበትን ኪሳራ እያሳየን ነው :: በተለያዩ የአውሮፓ እና የሰሜን አሜሪካ ከተሞች ወያኔ እየደረሰበት ያለውን ውርደት ለማካካስ እየተጠቀመበት ያለው ስልት እንደማያዋጣው ልንነግረው ይገባል::
ዲያስፖራው ትግሉን ያቆማል ብሎ የሚያስብ ከሆነ ዘላለሙን በጫካ ሞኝነት ራሱን የሚነዳው ወያኔ ልክ እያስገባነው መሆኑን አልተረዳውም:; በተከታይነት ደሞ በቀሪ የህሊና እስረኞች ላይ ሊወስን የተዘጋጀውን እየጠበቅን ትግሉ ግን ወያኔ አፈር እስኪገባ እንደሚቀጥል ለመናገር እወዳለሁ :: ትግሉ ይቀጥላል!!!