መድረክ ለመጠላለፍ መተነኳኮስ ጀምሯል!የወያኔ ታማኝ ጋዜጣ ሰንደቅ እያሟሟቀች ነው:;

 ምንሊክ ሳልሳዊ
በቅርቡ የአንድነት ፓርት መድረክን ገምግሜለሁ ያለበትን እና ወደ ዉህደት የሚለውን ጥናት የመድረክ አባላት አብጠልጥለውታል:: ዘላለማቸውን የፖለቲካ ግልቢያ በአደባባይ የሚያደርጉት ተቃዋሚዎች ዳግም ራሳቸውን ለመጣል በአደባባይ አንዱ የአንዱን ሃሳብ መዝለፍ ስራዬ ብለው ተያይዘውታል::
ይኸው ሁሌ ከኛ በላይ የለም የሚሉት የአዛውንቶች ክበብ የሆኑ ፓርቲዎጭ አንዱ አንዱን ለማዘዝ አምባገነንነትን ለማስፋፋት በሚል ዘይቤ ይመስላል አንዱ አንዱ ያንተ ስራ የመንገድ ላይ ስራ ነው በማለት መወራረፍ ጀምረዋል:: የአንድነት ብሔራዊ ም/ቤት መድረክ እንዲገመገም ማዘዝም ሆነ በዚህ ላይ ተመስርቶ የሚሰጠው ውሳኔ ተቀባይነት የለውም በማለት አንዱ አንዱን እያጣጣሉት ሲሆን በውስጥ ጉዳያቸውን መጨረስ ሲገባጨው በአደባባይ ለገዢው መደብ ታማኝ በሆኑ ጋዜትኦች ላይ እንዲህ መዘላበዱ የገዢውን ፓርቲ እድሜ ከማስረዘም ዉጪ ትግሉን ማክሰም ነው::
በበጎነት እና በትግል አጋርነት ስሜት የሚቀርቡ ሃሳቦችን በዉስጥ ተወያይቶ ተነጋግሮ መፍትሄ ማስቀመጥ ሲገባ በጠባብነት እና በብሄር ላይ ተመስርተው የተደራጁ ድርጅት መሪዎች የፖለቲካ ቋንቋ የተጠቀሙ እየመሰላቸው በይፋ እየዘለፉ የትግል ጓዶቻቸውን ማጥላላት ተገቢ አይደለም:; አንድነት ለመድረክ በጹሁፍ ባላቀረበው ጉዳይ ላይ መድረክን ማዘዝ አይችልም በሚል ፈጥኖ በአደባባይ አስተያየት መስጠት ሌላ ተእኮ ካልሆነ በስተቀር መድረክን እንደ ቅንጅት ለማድረግ የሚደረግ ሴራ ያስመስላል::
.....ዶ/ር መረራ ጉዲና.... ‘‘የመንገድ ላይ ስራ ነው’’ ሲሉ አጣጥለውታል። ሲል ሰንደቅ የተዘባበተበት መድረክ ነገ ምን ሊሆን ይችላል የሚለውን ካሁኑ መገመት አያቅትም::እርስ በርስ ተወነጃጅሎ መበታተን ነው እጣው??/ፖለቲካ እንሰራለን የሚሉ እንደዚህ አይነት ሰዎች ራሳቸው ፖለቲካዊ ጋር መጋባት ውስጥ እየዋዠቁ ሌላውን ግራ ተጋብቷል ማለት ያጠያይቃል::
የመድረክ የወቅቱ ሊቀመንበር አቶ ጥላሁን እንደሻው አንድነት ፓርቲ መድረክን የመገምገም ስልጣን የለውም ብለዋል። ያለው ወያኔያዊው ሰንደቅ የተቃዋሚ ፓርቲዎች መፈረካከስን የሚፈልግ መሆኑ በገሃድ ተደጋግሞ አይተነዋል ከዚህ ቀደም ኢንጂነር ዘለቀን ይዞ አላዘነ ዛሬ ደሞእነዚህን ...አቶ ጥላሁን የመድረክ ሊቀመንበር ናቸው እስከተባለ ድረስ አንዳንድ ጉዳዮችን በአደባባይ የማይነገሩ ዉስጥ ለውስጥ በንግግር የሚያልቁ የመድረክ አባል ፓርቲዎችን ጉዳይ በይፋ ስልጣን እንዳሌላቸው መናገር እብደት ይመስለኛል:: የአንድነት ብሔራዊ ምክርቤት ግምገማ ሙሉ በሙሉ ህገ-ወጥ ነው ማለታቸው ማንን ለማስደሰት ነው ወይስ እርስ በርሳቸው መባላት ጀመሩ ለማሰኘት???? አቶ ጥላሁን ?????
ዘላለማቸውን ከተኙበት የማይነሱት ተቃዋሚዎች አሁንም ለመጠላለፍ መነቋቆር መጀመራቸው በትግሉ ሂደት ዉስጥ እንቅፋት ለመፍጠር የሚራወጡበት ሁኔታ በስተርጅና እንኳን በፖለቲካ አለመብሰላቸውን ያሳያል:; በፖለቲካ ስድብ የበሰሉት እነዚህ የተቃዋሚ አመራሮች እርስበርሳቸው መጠላለፍን የሚያቆሙት መች እንደሆነ ይናፍቀናል::
እስከዚያ መልካሙን እንመኛለን::