ድሬቲዩብ(deretube)የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን አሯሯጭ


ላለፉት አመታት በወያኔ የሚሰሩ ወንጀሎችን በመደበቅ እና እንደፈለገ በመሆን የውሸት ሃጢያትን በመሸከም ሰይጣናዊ መርሁን እያራመደብን ያለው አንዱ የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን መሆኑ የማይካድ ሃቅ ነው ጎን ለጎን ከዛው ከመዲናችን የስልጣን ማስረዘሚያ ከሆኑት ከፋና እንዲሁም ከዋልታ በተጨማሪ የድህረ ገጽ የውሸት ባንኮች እንደ ትግራይ ኦንላየን እና አይጋፎረም የመሳሰሉት ሲገኙ የድሬ ቲዩብ ደሞ እንዲሁ የኢቲቭ ን ግልባጭ በመያዝ አሯሯጭ መሆኑ ሲታወቅ ባለፈው ሰሞን የለቀቀልንን ጸረ ኢትዮጵያውያንን አቋሙ የማን እንደሆን ይፋ አድርጎታል::
በተለያዩ ጊዜያት አረብ አገር ያሉ ውድ እህቶቻችንን በተመለከተ የሚወጡ ዘገባዎችን ለመስራት የሚያፈገፍገው ድሬቱብ ግን ከሚያስጠላ የምስል አቅርቦት ጋር የኢትዮጵያውያኑን እህቶቻችንን ወንጀል በአደባባይ ያውም በሰው ቋንቋ ሊነግረን ዳድቶታል:;
እንደሚዲያ ማጣራት ሲገባው የኣረብ ጋዜጦች ያሰፈሩትን "ለምን ?"ብሎ ሳይጠይቅ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችንን እንደ ወንጀለኛ ለማስቆጠል ልፋቱን አንበልብሎታል::
ድሬቲዩብ በተለያየ ጊዜያን ቆሽታችንን ቢያሳርረንም ዝምታን መርጠን ነበር ሆኖም አሁን የተለያዩ ኢትዮጵያውያን ይህ ማነው እያሉ ጥያቄዎችን ማንሳት ስለጀመሩ ማስጠንቀቂያ ሊሰጠው ይገባል ድሬቲዩብ::
በኣረብ አገር እህቶቻችን ላይ የሚደርሰውን ግፍ አንድም ቀን ለመተንፈስ የማይፈቅደው የኢቲቭ አሯሯጭ ይህ ሚዲያ ኢትዮጵያዊትዋ የ3 አመት የአረብ ልጅ በጩቤ እንደወጋች እና ወንጀለኛ እንደሆነች ሊነግረን ፈለገ ( http://www.diretube.com/articles/read-kid-stabbed-by-ethiopian-maid-in-saudi_2750.html )ሆኖም ለማጣራት ባደረግነው ሙከራ ይህንን ወንጀል ኢትዮጵያዊቷ አለመፈጸሟን እና አሰሪዎቿ ያለባቸውን ገንዘብ ላለመክፈል ብለው ያደረጉት እንደሆነ ፍርድ ቤቱ የተረዳ ሲሆን ከዚህ ቀደም እንደዚህ አይነት ወንጀል በፊሊፒኖች ተፈጽሞ በፍርድ ሂደት ላይ ያለ መሆኑ ታውቋል::
 በተለያዩ አረብ አገራት ያሉ እህቶቻችንን የሚደርስባቸውን ግፍ ለመዘገብ የሚልፈሰፈሰው ይህ ሚዲያ በአለም አደባባይ በራሱ ዜጎች ላይ ይህን አይነቱን ዜና መስራቱ ኢትዮጵያውያንን አስገርሟል::ስለዚህ እንደነዚህ አይነቶቹን የወያኔ ሚዲያ ሰጋጆችን ተባብረን ልናስወግድ ይገባል::