የደረቅ ፖለቲካ መርሃግብር የ22 አመት መኮላሸት

ያረጀ ፖለቲካ የወለደው የፖለቲካ ምቀኝነት
ምንሊክ ሳልሳዊ
የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ላልፉት 22 አመታት በትግል ውስጥ ቆይተዋል ሳይሆን ...ተኝተዋል ቢባል የሚቀል አነጋገር ነው::ፖለቲከኞቹ በ1997 የቀስተ ደመና ፓርቲ ባመጣው የንቃተህሊና ስፋት በቅንጅት ውስጥ ከደረቅ ፖለቲካ ለመውጣት አፋፍ ላይ ነበሩ ሆኖም ተኮላሸ::
የ1997 ምርጫ ተከቶሎ ተፈጠረ የተባለው የፖለቲካ መነቃቃት መኮላቸቱ እንደተጠበቀ ሆኖ ባለፉት 22 አመታት ባረጀ ፖለቲካ እና በገረጀፈ አመለካከት የሚጓዘው የተቃዋሚው ቡድን አድሮ ጭቃ ሲሆን እየተመለከትነው ነው::በተለያዩ ጊዜያት ራሱ እየፈጠረ ወይም ገዢው ፓርቲ እየወለደ የሚሰጣቸው ተለጣፊም ይሁኑ ተፈጣሪ የፖለቲካ ስሞች እየከሸፉ ላለንበት ደርሰናል:: እነዚህ ደረቅ የፖለቲካ ጥበቦች አምባገነንነትን ከማስፋፋት ውጭ እና የፈረንጅን ደጅ ከመጽናት ውጭ ያመጡት ምንም ፋይድ የለም::የፖለቲካ ጠቢባን ነን ጭፍን ምሁራን የፖለቲካ ስድብ ስልጡኖች ነን የሚሉ አንዼ ባለስልጣን አንዴ የምክርቤት አባል እየሆኑ ገዢውን ፓርቲ በአፋሽ አጎንባሽነት የሚያገለግሉ የጎሳ ፓርቲ መሪዎች ከፖለቲካው አለም መሰናበት ያለባቸው በዚህ ወሳኝ ወቅት ላይ ነው::
የራሳቸው ማኒፌስቶ እና መስመር ያሌላቸው በጥላቻ እና በዘር ፓርቲ ላይ ተመስርተው የሚዋዥቁ ፖለቲከኛ ነን ባዮች ጠባቦች ከየፖለቲካው መንደር በማቃጠል አመዳቸውን ማስወግድ የግዴታ ዘመን ነው::
ወቅቱ ከደረቅ የፖለቲካ መድረክ ወደ ሰለጠነ የፖለቲካ አደባባይ የሚወጣበት እና ፖለቲካን ምስጢራዊ በሆነ የማፊያዊ ስልት ለነጻነት ማጨት የእያንዳንዱ ፖለቲከኛ ስራ መሆን አለበት :: ማፊያዊ ስራ ማለት በፖለቲካው መስክ ስኬት ሊያስገኙ የሚችሉ አብዮታዊ እድሎችን መጠቀም ማለት ነው:: ደረቅ ፖለቲከኞች በደረቅ አትተርጉሙት::
ያለፉትን 22 አመታት የተቃዋሚፓርቲ ተብለው ስም የተሰጣቸው ስብስቦች ምንም የፈየደዱት ነገር የለም ገዢው ፓርቲ በሃገር እና በህዝብ ላይ እንደፈለገ ሲፈነጭ ያመጡት አንዳችም ለውጥ የለም የወሰዱትም ርምጃ የለም ይህንን የተመለከት ህዝብ ደሞ ገዢውን ፓርቲ በሸሸው እጥፍ እነሱን ሸሽቶ በየቤቱ በዝምታ ራሱን እያስተዳደር መሆኑ የማይካድ እና እያየነው ያለ ነው::
በየሃገሩ እየዞሩ ዲያሶፓራውን በመለመን ዲያስፖራው ደሞ በሃገርቤት ያለውን አምባገነናዊ ስርኣት ተገን በማድረግ የመኖሪያ ፍቃዱን ለማስረዘም በተስፈኝነት ተኮፍሶ ዶላሩን እያፈሰሰ ፓርቲዎቹ ካረጀ ፖለቲካቸው ጋር በህዝብ ላይ እንዲቀብጡ በር ከፍቷል::
በኢትዮጵያ የፖለቲካ ሂደት ውስጥ እየተሳተፉ የሚገኙት በ60ዎቹ የብሄር ፖለቲካ የተመረዙ የቀድሞ የከተማ ተኳሽ ዲቃሎች የሞተው ደርግ እና ፊውዳል መንግስታት ትርፍራፊ ግለሰቦች እና ጥቂት ከአድሃሪያን እና ከመንግስት ሰዎች የፈለቁ አዛውንቶችን እና እነሱ ያሰለጠኗቸው ኩታራዎች ከፖለቲካው መድረክ ለቀው በተራቸው እደተራው ዜጋ አዳማጭ መሆን ያለባቸው ጊዜ መሆኑን መረዳት አለባቸው :: አለም በፖለቲካ ሰልጥና በተለያዩ መንገዶች ሃገራዊ ብሄራዊ ጥቅሞች በሚከበሩበት ዘመን ባረጃ ፖለቲካ ድርቅ ባለ ቀጥተኛ መንገድ መጓዝ ትግሉን እየጎዳው ስለሆነ በአዲስ ትውልድ በአዲስ የፖለቲካ ስልት ገዢውን ፓርቲ በሚገባው እና እሱ በሚከተለው ሆሪዞንታል ማፊያዊ ፖለቲካ አናቱን ሊባል ይገባዋል:: በተቀየረ የፖለቲካ ስልት ካልሆነ በስተቀረ የተያዘው ደረቅ ፖለቲካ በፍጹም የተንሰራፋውን ጁንታ ማሰወገድ እንደማይቻል የታመነ ነው::
በሃገሪቱ በሚከሰቱ ከባድ ችግሮች ላይ ከማልቀስ ጀምሮ እስከ ፈረንጅ የመለማመጥ ባህሪ የተዋሃዳቸው ተቃዋሚ ነን ባዮች ግለሰቦች የራሳቸውን ጉዳይ ለገዢው ፓርቲ መረጃን በገንዘብ በመለወጥ ፓርቲያቸውን በመሰለል እርስ በርስ በመበላላት እና የሃሳብ ልዩነቶችን ባለማክበር ወዘተ ራሳቸውን ለለውጥ ስላላዘጋጁ ከፖለቲካው አለም ገለል ሊሉ ይገባል::
ያረጀ እና የወረደ ፖለቲካቸው የወለደው የፖለቲካ ምቀኝነት ገዢው ፓርቲ ተቃዋሚዎቹ ራሳቸው በውስጣቸው የሚፈጥሩትን ቅራኔ ተከትሎ የፖለቲካ ምህዳሩ እንዲጠብ እና ጥላቻ እንዲሰፋ ተጠቅሞበታል::የውስጥ ቅራኔያቸውን እና የአስተሳሰብ ልዩነታቸውን በመከባበር የፖለቲካ ስሜት ውጠው ትግሉን ለፍሬ ያላበቁት እነዚህ የፖለቲካ ሹምባሾች በአደባባይ የሚያሳዩት ድርጊት እና የሚያንጸባርቁት አሳብ እጅግ አስደንጋጭ እና አሳፋሪ ነው::እርስ በርስ እየተናከሱ ያሉት ሽማግሌዎች በፖለቲካ ፓርቲዎች መርሃግብር ስኬት ,አንድ ፓርቲ ባለው የገንዘብ መጠን ሌላው ፓርቲ በሚፈጥረው የትግል ስልት እና ስኬት ላይ የፖለቲካ ምቀኝነት ማሳየት የየእለት ተግባራቸው ሆኖ የመጣ ሲሆን በውስጣቸው ያለውን ቅራኔ በማየት ብቻ ለውጥ ማምጣት እንደማይችሉ ስላወቁ እነሱ ብቻ ሳይሆኑ በዙሪያቸው ያለውም ወጣት ተረካቢ ለገዢው ፓርቲ ራሱን አሳልፎ የሸጠ ሲሆን መፍትሄ አልባ የፓርቲ ውጥንቅጥ ሲስተም ውስጥ እየዋዠቁ ይገኛሉ::
ለዚህ ጉዳይ ያለው መፍትሄ በፖለቲካው አለም ባለፈው 22 አመታት በወያኔ ላይ ያላቸውን ጥላቻ ይዘው የተሰባበስቡ እና ምንም ህዝባዊ ማኒፌስቶ ያሌላቸው እነዚህ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች አብዛኛዎቹ በጎሳ ፓርቲ የተደራጁ ከፖለቲካው አለም ራሳቸውን ማሰናበት ግዴታ አለባቸው:: ህዝባዊ ትግል እንዲቀጣጠል ማድረግ ያልቻሉት እና በፍራቻ የሚርዱት ፖለቲከኛ ነን ባዮች ከመድረኩ ተሽቀንጥረው ሊባረሩ ይገባል:: 22 አመት ለውጥ እናገኛለን ብሎ ሲያያቸው የነበረ ህዝብ አንቅሮ የተፋቸው ሃገራዊ ስሜታቸው በብሄርተኝነት የታጠረባቸው ምሁራን ነን ባዮች ይተቃዋሚ አመራሮች ያደራጁትን የብሄር እና የጎሳ ፓርቲ ወደ ሃገራዊ ፓርቲነት በመለወጥ ቦታቸውን ለኣዲሱ ትውልድ አስረክበው መሄድ ግዴታ አለባቸው::