አዲስ ፍጥጫ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢሮበጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢሮ ውስጥ የፖለቲካ ፍጥጫ እና የስልጣን ሽኩቻ እየታየ መሆኑን መረጃዎች ጠቁመዋል:: በሁለት ወገን በሕቡእ እንደተሰለፉ የሚታሙት እንዲሁም ለሕወሓት መረጃ ያቀብላሉ በሚባሉ አመራሮች መካከል ከፍተኛ የሆነ የፖለቲካ ግብግብ መፈጠሩን የውስጥ አዋቂ ምንጮች ለምንሊክ ሳልሳዊ ጠቁመዋል::
ምንጮቹ እንደጠቆሙት ከሆን በረከት ስምኦን የራሱን ቡድን አደራጅቶ ሕወሃቶችን በማለሳለስ ሃይለማርያምን እየመራው እንደሚገኝ የገለጡ ሲሆን ለላኛው ቡድን ደሞ ለሃይለማርያም ድፍረት ለመስጠት እየሰራ የሚገኝ እና የሕወሃት ደህንነቶችን በጥገኝነት የተጠጋ መሆኑን ገልጸዋል::
በረከት ስምኦን በተለያዩ ጊዜያት ከሃይለማርያም ጋር ስምምነት እንዳሌለው ያዩ እና በመካከላቸው አለመግባባት መኖሩን የተመለከቱ የወያኔ የበላይ አመራሮች እስከመቼ ተመሪ ሆነህ ትቀጥላልህ በማለት ሃይለማርያምን የሚያደፋፍሩ ሲሆን በተዘዋዋሪ ባለቤታቸው ወይዘሮ ሮማንን ባልሽ እንዲደፍር አበረታችው በማለት የሚጠዘጥዙ ወገኖች እንደተፈጠሩ ምንጮቹ አክለው አስረድተዋል::
በረከት የራሱን ርእዮት አለም የሚደግፉለትን  ከተለያዩ ክልሎች ያሉ የኢህኣዴግ ካድሬዎችን በማደራጀት ላይ ሲሆን ብኣዴንን በተመለከተ ምንም የሚሰራው ድርጅታዊ ስራ እንደሌለ የተጠቆመ ሲሆን ከስልጣኑ ውጭ የሆኑ ስራዎችን ለመስራት በተለያየ ጊዜ የሞከራቸው ሙከራዎች በአቶ ሃይለማርያም የተደናቀፉ መሆኑን እና ከተደናቀፉ ጉዳዮችም አንዱ ኤርትራውያንን በወያኔ ስር የማደራጀት እንዲሁም ኢትዮጵያዊ ዜግነት የመስጠት በማለት ወደ ወያኔ/ኢህኣዴግ ይበልጥ ሰርገው እንዲገቡ ለመመልመል ያደረገው ሙከራ እና ቀጣዩን የወያኔ የስልጣን ርክክብ ለእነዚህ ላሰባቸው የኤርትራውያን ህዋሶች ለመስጠት ያሰበው ተደናቅፎበታል::
ይህንን እና ሌሎች ጉዳዮችን ተከትሎ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢሮ አከባቢ ፍጥጫ መኖሩን እና እንዳይካረር ያሰጋል ሲሉ ምንጮቹ ለምንሊክ ሳልሳዊ ጠቁመዋል::