የግል ኤሌክትሮኒክስ ሚዲያ ለስልጣናችን ያሰጋናል በይፋ....

ይህን ሰሞን የሚገሸለጡ የ2006 የሃገር ሃብቶች በበጀት ስም ተደላድለው ሰማን::አዎ የእኛ ሃገር በጀት መቼም ይመደባል ሪፖርት ኦዲተር መስሪያ ቤት ሲያቀርብበት ደሞ ያሳፍራል:: ተመላሽ የሚሆን በጀት ደሞ ወደ ግል የኪስ አካውንት ይዛወራል::ወደ ኪስ የሚገቡ ገንዘቦች በድልድሉ መሰረት አልበቃ ብሎ በበጀት ጉድለት ስም ሁሉ ከባንክ ለመበደር ለመጪውም እየታቀደልን ነው::
የሚገርመው እኮ በቂ ኢኮኖሚስቶች የሉንም ወይንስ አገር እየተገደለ ነው??? 16 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር ለ2006 በጀት አመት ለበጀት ጉድለት መሙያ/መሸፈኛ ሊበደር ታስቧል::የበጀት ጉድለቶች እንዳይከሰት የሚያጠና ቡድን ወይንም የተማረ የሰው ሃይል የለም ...ግን ሊሆን ይችላል የሃገር ፖሊሲ እኮ የሚነድፉት ኩማ እና በረከት ናቸው ...ኩበት መሃይሞች::

አንድ ደሞ ጉዳይ አለ እንደ ሞሽን የቀረበ ግርምችሆ የመርካቶው እንዳለን የብሮድካስቲንግ መስሪያቤት መፍረስ ...አዎ ይህ መስሪያቤት ስራውን ሃይለማርያም አስረዳን የማህበረሰብ ራዲዮ የመንግስት ቴሌቪዝን ጣቢያዎች መፈብረክ የግል ሚዲያዎችን ማቀጨጭ ፍቃድ መስጠት ወዲያው መንጠቅ...ስለዚህ ለምን ይፍረስ ሃጥያት ነው እኮ ለዚህም በጀት ይመደባል ወይ ጉድ??
ለአፈና ለግድያ ለእስር ለብዝበዛ ህዝብ ለማደሀየት አገር ለማውደም በጀት!!!
የሚገርመው እኮ የባለስልጣናቱ ስልጣናቸውን ለማስረዘም የግል ኤሌክትሮኒክስ ሚዲያ አለመፈለጋቸው ነው::ካሁን ቀደም ክፖሊሲ ነዳፊዎቻችን ቱባዎች አንዱ ንቃተህሊናችሁ ስላላደገ ለናንተ ከኢቲቭ በስተቀር ሌላ ሚዲያ አያስፈልግም አሉን :: አስቡን ምን ያህል የኢትዮጵያ ህዝብን ቢንቁ ነው ንቃተህሊናው ያላደገ ብለው የሚዘልፉት???
ህግ የሚፈበርከው ክፍል አስፈጻሚህ ነን በሚሉት ሰዎች እየተናደ ባለበበት በዚህ ወቅት የታዳጊው እና የ12 አመት የወያኔ ፈልፈላ መስሪያቤት መልካም ይሰራል ብሎ መጠበቅ ቂልነት ነው ስለዚህ የግል ኤሌክትሮኒክስ ሚዲያ ለስልጣናችን ያሰጋናል ብለዋል በይፋ....