የኢትዮጲያ ሙስሊሞች ትግል ጃዋር ሙሃመድ እና ዘረኝነት

ስራጅ ታንጎ/ምንሊክ ሳልሳዊ ብሎግፖስት
ሁለት ዓመት እየያ'ዘ ባለው የኢትዮጲያ ሙስሊሞች ትግል የዲያስፖራው ድርሻ ቀላል የሚባል' አይደለም ። ሀገር ውስጥ ያለን ሰዎች እንደተከታተልነው እና በአሁኑ ሰዓት እስር ቤት በሚገኙት የሙስሊሙ ማህበረሰብ ችግረ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎች ምስጋና እንደተቸረው ከሆነ በውጭ የሚገኘው የኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ቤ/ን አባላት ጳጳሱን ጨምሮ ይሄን እንቅስቃሴ በቀናነት እና በፍፁም ኢትዮጲያዊነት ሲደግፉ ተስተውሏል። ይህም የሆነበት ዋና ምክኒያት የሙስሊሙ ጥያቄ የፍትህ የህግ መንግስት ይከበር ስለነበር ነው። በእርግጥ እነዚህ ጥያቄዎች ተነስተው ንፅሁ ህሊና እና አስተዋይ አዕምሮ ላለው ሰው ከመደገፍ ውጭ ምን አማራጭ አለው?ኢትዮጲያውያንም የደረጉት ይሄንኑ ነው ለዚህም ሊመሰገኑ ይገባቸዋል። በመቀጠል የጃዋርን ንግግር ከሙስሊሙ ጥያቄ እና ከእስልምና መርህ ጋር ለማየት እንሞክራለን….ምንሊክ ሳልሳዊ ብሎግፖስት
 • #የሙስሊሙ ጥያቄ
  ሙስሊሙ ማህበረሰብ አሁን እያደረገ ያለውን ሠላማዊ የመብት ትግል የጀመረው ሁላችንም እንደምናውቀው ሦስት መሰረታዊ ጥያቄዎችን በማንገብ ነበር። ለማስታዎስ ያክል
  1. የመጂሊሱን(የኢትዮጲያ እስልምን ጉዳዮች ምክር ቤት አመራር) አመራሮች በራሳችን እንምረጥ
  2. አወሊያ በቦርድ ይተዳደር
  3. አህባሽ የተሰኘ ከእስልምን ውጭ የሆነ አስተሳሰብ በሃይል አይጫንብን።
  እነዚህ ጥያቄዎች ሲጠቃለሉ ህገ መንግስቱ ይከበር ወደ ሚል አንድምታ ይወስዱናል በእርግጥ በኋላ ላይ ሌሎች ጥያቄዎች ቢመጡም ልክ የታሰሩትይፈቱ ወንጀለኞች ለፍርድ ይቅረቡ ሁሉም ነገር የሀገሪቱ የህግ የበላይየሆነው ህገ መንግስት ይከበር ከሚል አያልፍም ።
  #ስለጃዋር
  ጋዜጠኛ ፋሲል የኔዓለም ጃዋር ያለው ነገር ሳይሆን የሚያሳስበው ስንትጃዋሮች አሉ የሚለው ነው የሚያስጨንቀን ሲል ጽፏል።
  እኔ ደግሞ እውን ጃዋር የኢትዮጲያ ሙስሊሞችን እና ኦሮሞዎችን ይወክላልን እላለሁ? ወንድም ፋሲል በመላምት ደረጃም ቢሆን ኦሮሞን ጠቅልሎ የጃዋር ሃሳብ አቀንቃኝ አድርጎ የማሰብ ነገር ይታያል(ቢሆን እንኳ ስሌት ይጠቀማል )ይሄ ደግሞ ጨርሶ ስህትት ነው ምክኒያቱም የኦሮሞ ህዝብ የጃዋርን ሃሳብ ከጥንቱም አይደግፍው ቢደግፈው ሃሳቡ እንዲህ ባልተንኮታኮተ ነበር።
  ወደ ጥያቄየ መልስ ስመጣ ጃዋር ሙስሊሙንም ሆነ ኦሮሞውን አይወክልም ባይ ነኝ። እንደ አንድ ግለሰብ የመሰለውን ተናግሯል ። መብቱ ነው። እኛም ተው ይሄ ሃሳብ ትክክል አይደላም እንላለን ። ታዲያሀገር ሲፈርስ ዝም እንበል እንዴ!?
  ይህ ሲባል ግን ጃዋር ለሙስሊሙ ትግል አስተዋጽኦ አላበረከተም ማለቴ አይደለም ብዙ ነገር አድርጓል እናመሰግናለን ደግሞ መታወቅ ያለበት ጃዋር ወይም ሙስሊሙ ዲያስፖራ ብቻ አይደለም እየታገለ ያለው ከነ ታማኝ ጀምሮ ሁሉም የኢሳት ጋዜጠኞች እና ሀገር ወዳድ ኢትዮጲያውያን ዲያስፖራ ተሳትፈዋል ለምን ህገ መንግስት ይከበር ስለነበረ ጥያቄው።
  አሁን አሁን ጃዋር ጥያቄውን ጠቅልሎ ወዴት እየወሰደው ነው ያስብላል እንዲህም ይላል “የኦሮሞ ህዝብ መብት መከበር የሙስሊሙ መብት መከበርነው” ምክኒያቱም አብዛኛው ሙስሊም ኦሮሞ ስለሆነ እንቀጥል….
  የኦሮሞ ትግል Vs የሙስሊሙ ትግል
  እዚህ ላይ ስለ ኦሮሞ ትግል ብዙ ማለት አልፈልግም ግን ትግላቸው እነ ጃዋርም ሆኑ ሌሎች የኦሮሞ ታጋዮች ለፍትህ ለዴሞክራሲ እና ለህግ የበላይነት ከሆነ አዎ ከኢትዮጲያ ሙስሊሞች ትግል ጋር አንድ ነው። ካልሆነ ጃዋር እንደሚለውን የኦሮሞን የበላይነት ለማረጋገጥ ከሆነ የሙስሊሙ ትግል አላማው እሱ አይደለም እንለዋለን። እዚች ላይ የማዲባ ንግግር ትምጣ ታዋቂው የፀረ አፓርታይድ ታጋይ ማዲባ ማንዴላ እንዲህ ይላሉ “ እኛ የምንታገለው የነጭን የበላይነት አስወግደን የጥቁሩን የበላይነት ለማምጣይ አይደለም፤ እኛ የምንታገለው ነጩም ጥቁሩም በእኩል የሚኖርባት ደቡብ አፍሪካን ለመፍጠር ነው” እኛም እንዲህ እንላለል ‘እኛ የምንታገለው የኦሮሞን እና የሙስሊሙን የበላይነት ለማንገስ ሳይሆን በኢትዮጲያ የህግ የበላይነትን ለማስፈን ነው!”
  #ኢትዮጲያችን ወዴት ወዴት
  የሰው ልጆች ታሪክ እንደሚያስረዳው የጭቆናና የበደል መዓት አንደኛው በአንደኛው ላይ ሲጭን እንደነበረ ነው። ነጩ በጥቁሩ፤ብዝሃው በዓናሳው፤ካቶሊኩ በፕሮቴስታንቱ(በአውሮፓ የሆነ ነው) ግልባጩም ሰርቷል አጼዎቹ በሙስሊሙ እና በሌሎች ብሄር ብሄረሰቦች (በኛ ሀገር) ይሄ ግን በህዝቦች እና ጨቋኞች በሚከተሉት እምነት ቡራኬ የተሰጠው አልነበረም በትቂት ግለሰቦች እና ለሆዳቸው ባደሩ የእምነቱ መሪዎች እንጂ። እነደዚህ አይነት የታሪክ ጠባሳ ያረፈባቸው የዓለማችን ህዝቦች ችግሩን የፈቱት በእርቅ እና በሰላም እንጂ ታሪኩን እየመዘዙ ለበቀል በመነሳሳት አይደለም። ከእርቅ እና ይቅር ከመባባል የተሻለም ትክክልኛ መንገድ ሊኖር አይችልም ምክኒያቱም በጊዜው የነበሩትን ጨቋኞች በአሁኑ ዘመን አግኝቶ መጠየቅ እና ለፍርድ ማቅረብ ሰለማይቻል። አክቲቪስት ታማኝ በየነ በአንድ ንግግሩ (ሁሉም ማህበረሰብ የትም ሃገር በአንድም ሆነ በሌላ መልኩ ተጨቁኗል እኛም ሀገር እንዲሁ በጊዜው ብንኖር እና ብናስተካክለው ደስ ባለን ግን አልሆነም እኛም አልነበርነም )ብሏል ስለዚህ ፍቅር ይሻለናል። የሁለቱም እምነቶች መጽሃፍ ይህንኑ ሃሳብ ያጠናክሩልናል።
  ቅዱስ ቁርዓን በምዕራፍ 17፤15 “….Nor can the bearer of a burden bear the burden of another… “ (ተሸካሚም ነፍስ የሌላኛውን ሃጢያት አትሸከምም)
  መፅሃፍ ቅዱስ በዘዳግም 24፤16” The fathers shall not be put to death for the children neither shall the children be put to death for the fathers every man shall be put to death for his own sin” (አባቶች ስለ ልጆች አይገደሉ ልጆችም ስለ አባቶች aይገደ..  • ለኔ ይሄ ትግላችን ለማደናቀፍ የሚደረግ ጥረት ነውና ድምጻችን ይሰማ (አሚራችን) ተገቢወን መግለጫ መስጠት አለበት ብዬ አምናለው ፡፡ እንተስ??
   #የጃዋር ሞሀመድ እብደት "እኔ ባለሁበት 99% ሙስሊም ነው ማንም ሰው ደፍሮ ቀና አይልም #በሜንጫ ነው አንገቱን የምንለው " በአሜሪካ በተደረገ ስብሰባ ላይ ከተናገረው(ሜንጫ የማጭድ ቅርፅ ያለው ረዘም ያለ ባለስለት የቁጥቋጦ መቁረጫ መሳሪያ ነው)
   እንደ አባባሉ ከሆነ ሆድ ያባውን ብቅል ነበር የሚያወጣው የጃዋር ነገር ግን ግራ የሚያጋባው አድማጭ እና መድረክ ባገኘ ቁጥር ነው ከውስጡ ደብቆ የኖረውን ለማንም የማይጠቅም መርዘኛ አስተሳሰብ አደባባይ እያወጣ ያለው።የነ ኢሳያስ አፈወርቂና የሟች መለስ ዜናዊ የመንፈስ ልጅ ለመሆን እየተንደረደረ የሚገኘው ጃዋር የጎሳና የዘር ፖለቲካ ኋላቀርና ተቀባይነቱ እጅግ እየደከመ መሆኑን ሲረዳ ብዙ ለውጥ ናፋቂ ኢትዮጵያውያን በሙሉ ልቡ ሲደግፈው የነበረውን እንዲሁም ዘረኝነት የሌለበትን በኢትዮጵያዊነት መንፈስ የተቃኘውን የሙስሊሞች ትግል ላይ ተፈናጦና አቅጣጫውን አስቶ ፀሐይ የጠለቀችበትን የወረደ የፖለቲካ አስተሳሰቡን በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ ለመጫን እይተፍጨረጨረ ይገኛል በስመ መሐል ሰፋሪነት የጃዋርን ደም አፋሳሽ እብደት መታገስ ግብዝነት ነው ብዙሀን ሙስሊሙም ጃዋርን በስማችን አትነግድ ሊለው ግድ ይላል።እኔ በበኩሌ እንደ ጃዋር ያሉ ግልገል መለስ ዜናዊና ኢሳያስ አፈወርቂ ኢትዮጵያችንን በደም ለማጨቅየት ሲቋምጡ እያየሁ ዝም አልልም።እውነትም ትምህርት ቀናን እንጅ ጠማማን እንደማያቀና ጃዋር አብይ ምስክር ነው።